TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#PressBriefing

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ መግለጫ ሰጥተው ነበር ፤ በመግለጫቸው ያነሷቸው ነጥቦች እና ተጠይቀው ከመለሷቸው ዋና ዋና ጉዳዮች ጥቂቶቹ ፦

- በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ተፈጸሙ በተባሉ ጥሰቶች ላይ ተመድ [UN] ሊያደርገው ያቀደው ተጨማሪ ምርመራ ተቀባይነት የለውም ብለዋል። በኢሰማኮ እና በተመድ የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር የጋራ ሪፖርት ላይ የተመላከቱ ምክረ ሀሳቦችን ለመተግበር መንግስት ዝግጁ ነው ብለዋል። ነገር ግን በተመድ በኩል ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ የሚደረገው አካሄድ ተቀባይነት የለውም ብለዋል።

- ያልተገደበ የሰብአዊ ድጋፍ ተደራሽነት ተጠናክሮ መቀጠሉን፣ አገራዊ ምክክሩ በሂደት ላይ መሆኑ እና ሰላምን የማስፈን ጥረቶች ተጠናክረው መቀጠላቸውንም ተናግረዋል።

- ኢትዮጵያ በበርበራ ወደብ 19 በመቶ ድርሻዋን እንዳጣች በሚመለከት ይፋ የሆነውን መረጃ በተመለከተ መንግስት መረጃውን እያጣራ ይገኛል ብለዋል።

- መንግስት ሱዳን የያዘችው የኢትዮጰያ መሬት በሌሎች የኢትዮጰያን መረጋጋት በማይፈልጉ አገራት ግፊት የወሰነችው ውሳኔ አድርጎ እንደሚወስደው ገልፀዋል። አሁንም ቢሆን መንግስት ሱዳን ከያዘችው የኢትዮጵያ ግዛት ያለ ግጭት ለቃ እንደምትወጣ ተስፋ አለው ብለዋል።

- ከሰሞኑ ገንዘብ ሚኒስቴር የ2015 ዓ.ም በጀትን ለክልሎች ሲደለድል #የትግራይ_ክልልንም አካቷል ፤ የበጀት ድልድሉ #ድርድር ስለመጀመሩ አመላካች ነው ወይ ? ተብሎ ለተነሳ ጥያቄ አምባዳደር ዲና ሙፍቲ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

Credit ፦ #ኤፍቢሲ #አሀዱሬድዮ #ኢትዮኤፍኤም

@tikvahethiopia
👍2
#AddisAbaba

ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ አሰቃቂ የግድያ ወንጀል መፈፀሙን ፖሊስ ገልጿል።

በአዲስ አበባ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ቦሌ አራብሳ ኮምዶሚኒየም በሁለት ህፃናት ላይ እጅግ አሰቃቂ ግድያ መፈፀሙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።

የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው ከጠዋቱ አራት ሰዓት ላይ ሲሆን ፤ በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ የምትሰራ አንዲት ግለሰብ ክርስቲያን መላኩና ወንጌላዊት መላኩ የተባሉ የሁለት ዓመትና የሶስት አመት ህፃናትን ህይወት አጥፍታለች።

የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮምሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ም/ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ፦

" ቦታው ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ነው፤ ወረዳ አራት አራብሳ ኮንዶሚኒየም እዛ አካባቢ ነው።

ወንጀሉ ተፈፀመው አራት ሰዓት አካባቢ ነው። ግለሰቧ እጅግ ዘግናኝ የሆነ ወንጀል ነው የፈፀመችው።

የሁለት ዓመት እና የሶስት ዓመት (ክርስቲያን መላኩ እና ጊዮናዊት መላኩ) ህፃናትን ነፍስ ነው ያጠፋችው።

ምክንያቱ ገና እየተጣራ ነው ወንጀል ፈፃሚዋ ግን በቁጥጥር ስር ውላለች። እስካሁን ባለን መረጃ ከአሰሪዎቿ ጋር በተፈጠረ ፀብ ነው የሚባለው።

የአገዳደል ሁኔታው እየተጣራ ነው። በምንድነው የገደለችው እንዴት ነው የገደለችው የሚለው ነገር ... ግማሹ አርዳነው ያላል ግማሹ አንቃ ነው ይላል እየተጣራ ነው ዞሮ ዞሮ ግን የህፃናቱ ህይወት አልፏል ይሄ ነው አሁን ላይ በተጨባጭ ሊገለፅ የሚገባው።

ወንጀሉ እጅግ ዘግናኝ ስለሆነ ፖሊስ መስራት የሚገባውን ሰርቶ ለሚመለከተው የፍትህ አካል ያቀርባል ህብረተሰቡ መረጋጋት አለበት። "

#ኢትዮኤፍኤም

@tikvahethiopia
😢2.19K😱224👍1709🙏6🥰4