TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኡቡንቱ #አርባምንጭ #ቲክቫህ #ፒስሞዴል

በዛሬው የውይይት ዝግጅት ላይ በስፋት ከተነሱት ሀሳቦች መካከል ሰው በሰውነቱ፡ብቻ ሊከበር እንደሚገባውና ሰላምን የሚያስቀድም ትውልድ ለመገንባት ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡ በውይይቱ የተሳተፉ ወጣቶች ደግሞ የጋሞ አባቶች ሰላም ወዳድነት ከአንድም ሁለት ጊዜ በተግባር የተገለጠ መሆኑን ጠቅሰው እንዲህ በአንድ መድረክ ስለ ሰላም አብረው መምከራቸው ትልቅ ትምህርት እንደሚሰጣቸው አንስተዋል፡፡ በአጠቃላይ ከውይይቱ በኀላ ሁሉም እጅ ለእጅ ተያይዘው ስለ ሁሉም ሰው ልጆች ክብር የድርሻቸውን ለመወጣትና ይህን ለማድረግ እድሜ እንደማይገድበው በማመን የሚጠበቅባቸውን ሀላፊነት ሁሉ ለመወጣት ቃል ገብተዋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በዛሬው መርኃ ግብራችን ላይ ታዳጊ ህጻናት እንዲህ በማለት መልዕክታቸውን አቅርበዋል፡-

"እኛ ህጻናት የእናንተው ልጆች ነን ለሀገራችንም ተምረን ተስፋ የምንሆናት ትውልዶች እኛ ነን፡፡ በፍቅር አድገን ወላጆቻችንንና ሀገራችንን ማገዝ እንመኛለን፡፡"

"እኛ ህጻናት ፍቅር ያስፈልገናል፡፡ የወደፊት የሀገራችን ተስፋዎች እኛ ነንና ታላላቆቻችን ፍቅር ልታስተምሩን ይገባል"

"መልካምነትን የምንማረው ከታላላቆቻችን ነውና እባካችሁ መልካምነትን በተግባር አስተምሩን"

"አባቶቻችን ትላንት እርጥብ ሳር ይዘው ለሰው ልጅ እንዴት ክብር መስጠት እንዳለብን አስተምረውናልና እኛ ህጻናት ከልባችን እናመሰግናቸዋለን"

ይህንን መልዕክት በኮልታፋ አንደበታቸው ካቀረቡ በኀላ በትህትና ዝቅ ብለው የአባቶችን ጉልበት ስመዋል አባቶችም ህጻናቱን መርቀው የሰላም ምልክት የሆነውን ነጭ ባንዲራ አበርክተውላቸው ልጆቻቸው በሰላም እንዲኖሩ በሙሉ አቅማቸው ለሰው ልጅ ክብርና ለሰላም እንደሚተጉ ቃል ገብተውላቸዋል፡፡

#ጋሞዞን #አርባምንጭ #ቲክቫህ #ፒስሞዴል #ሃይሌሪዞርት

@tikvahethiopia @tsegabwolde
#እናመሰግናለን!

ጥሪያችንን አክብራችሁ የተገኛችሁ የሃይማኖት አባቶች፣ የጋሞ አባቶች፣ የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎች እና የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ ላቅ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

ለዚህ መርኃግብር መሳካት የድርሻችሁን ለተወጣችሁ ለመልካሙ ሀሳብ መልካምነታችሁን ለገለጻችሁ በሙሉ የዚህ ዝግጅት መሳካት ክብሩ የእናንተ ነውና ክብር ይገባችኀል፡፡

በተለይ ባስፈላጊው ነገር ሁሉ ላልተለየው ድጋፋቸው የጋሞ ዞን አስተዳደርን ከልብ እናመሰግናለን፡፡ ለዚህ ስራ ብዙ ድጋፍ ያደረጉ አካላትንም ሳናመሰግን አናልፍም፡፡ በተለይም ኃይሌ ሪዞርት፣ ኦሞቲክ ጀነራል ትሬዲንግና ዊዝደም አካዳሚ ከልብ እናመሰግናለን፡፡

ዲዛይነሮቻችን፦
•ፌቨን ደረጀ
•በረከት መንግስቱ
•ሂሩት ታዬ
•ሄርሜላ ተሾመ
•ቅዱስ ዮሐንስ

ሳውንድ ሲስተምና ዲኮር፦
•ሙሉቀን መሉ የሳውንድ ሲስተምና ዲኮር ስራ

#ኡቡንቱ #አርባምንጭ #ቲክቫህኢትዮጵያ #ፒስሞዴል

በቀጣይ በሌሎች የሀገራችን ከተሞች ከሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች (ከወጣቶች፣ ከሃይማኖት አባቶች፣ ከሃገር ሽማግሌዎች፣ ከአባ ገዳዎች ጋር ተመሳሳይ መድረኮችን እያዘጋጀን የምንመክር ይሆናል። እንዲሁም በዩኒቨርሲቲዎች፣ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ጋር ተመሳሳይ ዝግጅቶችን ይኖሩናል።

"በምክንያት የሚያምን ሚዛናዊ በሆነ ትውልድ መካከል የሚፈጠር የሃሳብ ልዩነት የጥንካሬ ምንጭ እንጂ የጠብ መነሻ አይሆንም!"

"እኛ ወንድምና እህት ነን፤ እዚህ ምድር ላይ አብረን እንጓዛለን!"

ቲክቫህ ቤተሰቦች!

@tsegabwolde @tikvahethiopia