TIKVAH-ETHIOPIA
ℹ የግብፁ መሪ የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ግብፅን እንዲጎበኙ ግብዣ አደረጉ። ከቀናት በፊት ለሶማሊያው ፕሬዜዳንት ተመሳሳይ መልዕክት መላካቸው ይታወሳል። የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሽኩሪ በኤርትራ ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በአስመራ ቆይታቸው ከፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ተገናኝተው ነበር። በዚህም ወቅት ከፕሬዜዳንት አልሲሲ የተላከ መልዕክት አድርሰዋል…
የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ዛሬ ግብፅ ካይሮ ገብተዋል።
ካይሮ ሲደርሱ የግብፁ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ሁለቱ አካላት በሁለትዮሽ እና በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሏል።
ከወራት በፊት የግብፁ መሪ የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ግብፅን እንዲጎበኙ ግብዣ ማድረጋቸው ይታወሳል።
ግብፅ ግብዣውን አቅርባ የነበረው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ሳሜህ ሽኩሪ በኤርትራ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ነው።
ሚኒስትሩ ወደ ኤርትራ ለጉብኝት የሄዱት የኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ የመግባቢያ ስምምነት ከተፈረመና ከማንም ቀድማ ስምምነቱን #በመቃወም አቋሟን ካሳወቀች በኃላ ነው።
ለኤርትራው መሪ ግብዣ ከመቅረቡ ቀደም ብሎ የሶማሊያው ፕሬዜዳንት በኤርትራ ጉብኝት እያደረጉ በነበረበት ወቅት የግብፁ ፕሬዜዳንት አብዱልፈታህ አል ሲሲ ተመሳሳይ ግብፅን ይጎብኙ የሚል መልዕክት ማድረሳቸው አይዘነጋም።
@tikvahethiopia

😡458👏249❤88🕊41😱27😢13🥰9🙏9