TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.61K videos
217 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ የትግራይ ተወላጅ የንግድ ማህበረሰብ አባላት ከጸጥታ አካላት እና ከአዲስ አበባ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ጋር ተወያዩ።

ውይይቱ ትኩረቱ የነበረው በአ/አ ከተፈጠረው ክስተትና ከንግድ ቤት መታሸግ ጋር በተያያዘ ነበር።

የትግራይ ተወላጅ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት የንግድ ቤቶቹ መታሸግ ከማንነት ጋር የተያያዘ አንድምታ እየፈጠረባቸው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

መከላከያ ሰራዊቱ መቐለ ከተማን ሰኔ 21 ቀን 2013 ለቅቆ መውጣቱን ተከትሎ በአዲስ አበባ በሚገኙ ፣ ሆቴሎች ፣ መጠጥ ቤቶች እና ምሽት ቤቶች ብጥብጥ ለማስነሳት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦችን በመደገፍ የተጠረጠሩ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገልጿል።

እርምጃ የተወሰደባቸው ቤቶች በከተማዋ የዘር ፍጅት እንዲከሰት ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች በሆቴል ቤታቸው በማስቀመጥ ድጋፍ አድርገዋል በሚል ሲሆን ከነበረው ክስተት ጋር በተያያዘ መንግስት ከ8 በላይ ባለ ኮከብ ሆቴሎች እና በርካታ ቁጥር ያላቸው ክለቦች እንደዚሁም ምግብ ቤቶችን ጨምሮ በድርጊቱ ተሳትፎ የነበራቸው ከረንቦላ ቤቶች ታሽገዋል።

ከትግራይ ተወላጅ የንግድ ማህበረሰብ አባላት ጋር በተካሄደው ውይይት የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ የሴክተር ተቋማት ዘርፍ ሀላፊ የሆኑት ሰለሞን ኃይሌ ፥ ሰላማዊ የሆነው የንግዱ ማህበረሰብ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ መብቱ ይጠበቃል ፤ ከንግዱ ማህበረሰብ የሚጠበቀው እራሱን ከህወሓት ቡድን ማራቅ ብቻ ነው ብለዋል፡፡

"የትግራይ ተወላጅ የሆነ በሙሉ በሀገር የተከሰተውን ህመም ሊጋራ ይገባል" ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ያንብቡ : telegra.ph/Addis-Ababa-07-28

Credit : #ETHIO_FM

@tikvahethiopia