TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" የእኛን ምሩቃን ለመቅጠር ስትፈልጉ የትምህርት ማስረጃቸውን #ለማረጋገጥ ጠይቁን ፤ ትክክለኛውን ማስረጃ በአንድ ቀን ውስጥ እንሰጣችኃለን " - ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ

ዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ ፤ በተለያዩ ጊዜያት በተደረገው የትምህርት ማስረጃ ማጣራት በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ስም የተሠሩ #የሀሰት የትምህርት ማስረጃዎች መገኘታቸውን አሳወቀ።

ተቋሙ ፤ ህገወጥ የሀሰት የትምህርት ማስረጃ ለማጣራት በተሰራው ስራ የቀድሞ የዩኒቨርሲቲ ምሩቃን ትክክለኛ ያልሆነውን ውጤት በራሳቸው ጊዜ የራሳቸው አድርገው ውጤት ማሻሸል እንደቻሉ ተደርሶባቸዋል ብሏል።

" ይህ አሳፋሪ ወንጀል ነው " ያለው ዩኒቨርሲቲው ግለሰቦቹ ይህን በመፈፀም በአቋራጭ መንገድ ስራ የመቀጠር እና የሌሎች ሰዎች የስራ እድል ጭምር በማጥፋት ድርጊት መሰማራታቸውን አመልክቷል።

በተጨማሪም የዩኒቨርሲቲውን ስም ለመጥፋት እንደሞከሩ ገልጿል።

በእንደዚህ ዓይነት የሀሰት የትምህርት ማስረጃ ላይ መሳተፍ ከዜጎች የማይጠበቅ ተግባር ነው ያለው ዩኒቨርሲቲው በሀሰት የትምህርት ማስረጃ ማጣራት የተደረሰባቸው የቀድሞ የዩኒቨርሲቲውን ተማሪዎች ዝርዝር ይፋ አድርጓል።

ከዚህ ባለፈ ማንኛውም መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ እንዲሁም የግል ተቋማትና ድርጅቶች ከዛሬ ህዳር 01/2016 ዓ.ም ጀምሮ ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በሁሉም የትምህርት ፕሮግራሞች የተመረቁ ምሩቃንን ለመቅጠር ሲፈልጉ የተቀጣሪዎችን መረጃ በፖስታ ቁጥር P.O.Box 667 እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው ኢሜይል email address: info@wcu.edu.et በመላክ ማረጋገጥ እንደሚችሉ ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው የምሩቃንን ትክክለኛውን የትምህርት ማስረጃ በአንድ ቀን ውስጥ ሰጣለሁኝ ብሏል።

* ከላይ የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በሀሰት የትምህርት ማስረጃ ማጣራት የተደረሰባቸው የቀድሞ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ስም የተያያዘ ሲሆን አብዛኞቹ በተለያዩ የሀገሪቱ #ባንኮች ውስጥ እንዲሁም በመንግሥት መ/ቤት ውስጥ ተቀጥረው ሲሰሩ የተገኙ ናቸው።

@tikvahethiopia
👏929219😭93😡77😱54🙏48🕊32😢31🥰29