TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update 🧕" የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የፍርድ ቤት የእግድ ትእዛዝ በመጣስ አሁንም ሴት ሙስሊም ተማሪዎች / ልጆቻችን ወደ ትምህርት ገበታ እንዳይገቡ ከልክሏል "  - የተማሪዎች ቤተሰቦች 👉 " የተጣሰ የፍርድ ቤት የእግድ ትእዛዝ የለም ፤ የትምህርት ህግ እና ደንብ ያከበሩ ተማሪዎች ወደ ክፍል ገብተው መማር ጀምረዋል ፤ ቀሪዎቹ እንዲመለሱ ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ ነን " -  የአክሱም…
#ሂጃብ #ሰልፍ

በሂጃብ ጉዳይ ነገ መቐለ ላይ ሰላማዊ
ሰልፍ ሊደረግ ነው።

የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከሂጃብ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ የፍርድ ቤት እና የትምህርት ቢሮ ወሳኔና ትእዛዝ እንዲተገበር የሚጠይቅ ሰላማዊ
ሰልፍ እንደሚያካሄድ አስታውቋል።

ምክር ቤቱ ፥ የአክሱም ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ ለብሰው ትምህርታቸውን እንዳይከታተሉ መደረጋቸውና ከትምህርት ገበታ መራቃቸው መግለጹ ይታወሳል።

በአክሱም የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ከሂጃብ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ባለፉት ሁለት ወራት የክልሉ ትምህርት ቢሮ ለሦሥት ጊዜ ደብዳቤ የፃፈው እንዲሁም የፍርድ ቤት ትእዛዝ አልቀበልም በማለታቸው ሰላማዊ
ሰልፍ ለማካሄድ መገደዱን ገልጿል።

በዚህም ነገ ጥዋት 1 ሰዓት በመቐለ ከተማ ሮማናት አደባባይ ሰላማዊ
ሰልፍ እንደሚደረግ አሳውቋል።

ሁሉም ፍትህ ፈላጊ የሰልፉ ተሳታፊ እንዲሆንም ጥሪ አቅርቧል።

ሰልፉ ከቀናት በፊት ዓርብ ጥር 9 ሊደረግ የነበረ ቢሆንም የጥምቀት በዓል ዋዜማ በመሆኑ ምክንያት ነው ለነገ የተዘዋወረው።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ከአክሱም ከተማ ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ ክልከላ ጋር ተያይዞ ተከታታይ መረጃዎችን ሲያቀርብ ቆይቷል ፤ ነገ ማክሰኞ ጥር 13/2017 በመቐለ ከተማ የሚካሄደውን ስልፍም ተከታትሎ ያቀርባል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
5👏1.95K😡256232🙏84🕊60🤔33🥰22😢21😭20😱10