TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.61K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ማስታወቂያ!

ዩኒቨርሲቲያችን የ2012 የትምህርት ዘመንን ለመጀመር ቅደመ ዝግጅቱን አጠናቆ አዲስና ነባር ተማሪዎች ለመቀበል ዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ሁላችሁም የዩኒቨርሲቲያችን መምህራን መስከረም 05/2012 ዓ/ም በየኢንስትቲዩቱ፣ ኮሌጆችና ትምህርት ቤቶች በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ ዩኒቨርሲቲው በጥብቅ ያሳስባል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

TIKVAH MAGAZINE የትምህርት ተቋማት ጉዳዮች በስፋት ያገኙበታል👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ
1
የዲላ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ መስከረም 5-6⬆️

ጉዳዩ የሚመለከታችሁ የጤናና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎችን ብቻ ነው!

የ2012 ዓ/ም የትምህርት ዘመን መግቢያ ቀን መስከረም 5-6 ሲሆን መስከረም 7 የዐመቱ የወሰነ ትምህርት/DOCO/ ይጀምራል።
.
.
.
በTIKVAH-ETH በርከት ያሉ የዩኒቨርሲቲ መረጃዎች ጫና እየፈጠሩ ስለሆን በዚህ ገፃችን አስተማማኝ መረጃዎችን እንደልባችሁ ታገኛላችሁ TIKVAH - MAGAZINE👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ
በተጨማሪ...

የዲላ ዩኒቨርሲቲ የነባር ተማሪዎች የመግቢያ ቀን መስከረም 21 ነው። ይህ ቀን /TENTATIVE/ ወይም ሊቀየር የሚችል የመግቢያ ጊዜያዊ ጥሪ ነው።

Via Y/ከዲላ ዩኒቨርሲቲ/

በTIKVAH-ETH በርከት ያሉ የዩኒቨርሲቲ መረጃዎች ጫና እየፈጠሩ ስለሆን በዚህ ገፃችን አስተማማኝ መረጃዎችን እንደልባችሁ ታገኛላችሁ TIKVAH - MAGAZINE👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ
#አዲስ_አበባ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በአዲስ አበባ ለመንግስት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ለመስጠት ቃል የገባችውን 1 ሚሊየን ደብተር ዛሬ አስረከበች። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የቤተ ክርስቲያኗ ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በተገኘበት ዛሬ ለአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ 1 ሚሊየን ደብተር አስረክበዋል። በዚህም ወቅት ብፁእነታቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ “ለተማሪዎቻችን መልካም አዲስ ዓመት እና መልካም የትምህርት ዘመንን እንመኛለን” ብለዋል። ኢንጂነር ታከለ ኡማ በበኩላቸው “ቤተ ክርስቲያኗ ስንሳሳት ስታርመን፤ ጥሩ ስንሰራም ስታበረታታን መጥታለች ለዚህም እናመሰግናለን” ብለዋል። አሁን ላይ ቤተክርስቲያኗ ባጋጠማት ነገር ሳትሸነፍ አቃፊ እንደመሆኗ በዚሁ ይህንን ጊዜ እንደምታልፍ እምነታቸው መሆኑን እና የከተማ አስተዳደሩም ከጎኗ መሆኑን ነው የተናገሩት።

Via #FBC

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#KENYA🇰🇪

የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ዛሬ ያረፉትን የቀድሞው የዚምባቡዌ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤን ለማሰብ የሀገራቸው ሰንደቅ ዓላማ ለሦስት ቀናት ዝቅ ብሎ እንዲውለበልብ ትዕዛዝ ሰጡ። ኡሁሩ ትዕዛዙን ያስተላለፉት ለሙጋቤ የሚደረገው ሀገር አቀፍ የሀዘን መግለጫ ስነ ስርዓት አካል እንዲሆን ነው። በኬንያ ከነገ ቅዳሜ ንጋት እስከ ሰኞ ምሽት በሚዘልቁት ሦስት የሀዘን ቀናት በሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እና ወታደራዊ ሰፈሮች ያሉ የኬንያ ሰንደቅ ዓላማዎች ዝቅ ብለው ይውለበለባሉ። ኡሁሩ ውሳኔውን «ለእኚህ የአፍሪካ ጀግና እና የሀገራችን ወዳጅ ያለንን ክብር ለመግለጽ» የሚደረግ ነው ብለውታል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
😢1
#HappeningNow

የ2011 ዓ/ም "የመልካም ወጣት ለኢትዮጵያ አንድነት" የመዝጊያ ስነ ስርዓት በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል። በዚህ የመዝጊያ ስነ ስርዓት ላይ የኢፌዴሪ ጠ/ሚ አብይ አህመድ ተገኝተው ንግግር እያደረጉ ይገኛል።

አዳራሹ ውስጥ የሚገኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ይህንን አጋርተዋል👇
👍1
ጠቅላይ ሚኒስትሩ 25,000 ዩሮ ለመልካም ወጣት ግንባታ ማዕከል አበረከቱ!

ጠ/ሚ ዶ/ር #አብይ_አህመድ ከሰሞኑን በሰላም ሽልማት ያገኙትን 25,000 ዩሮ ለመልካም ወጣት የማዕከል ግንባታ እንዲውል አበርክተዋል።

በአሁን ሰዓት በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ በሚገኘው "#የመልካም ወጣት ለኢትዮጵያ አንድነት" የመዝጊያ ዝግጅት ላይ ምክትል ጠ/ሚ ክቡር አቶ ደመቀ መኮንንም ተገኝተዋል።

#TIKVAH_ETHIOPIA

ፎቶ📸#SignorinaSolomon
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአርቲስት ተዘራ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ!

የአርቲስት ተዘራ ለማ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ፡፡ በበርካታ ፊልሞች ላይ በትወና የሚታወቀው አርቲስት ተዘራ ለማ የቀብር ስነ ስርዓት በዛሬው ዕለት ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል።

አርቲስት ተዘራ ለማ ትናንት ምሽት ቤቱ ውስጥ እያለ በድንገት ህመም ካጋጠመው በኋላ በአካባቢው ወደሚገኝ የህክምና ማዕከል ቢወሰድም ህይወቱ አልፏል። “ውሳኔ ፊልም” ላይ መጀመሪያ የትወና ስራውን የሰራው አርቲስት ተዘራ ከዚያን ጊዜ ወዲህም ከ20 በላይ ፊልሞች ላይ የተለያዩ ገፀ ባህሪያትን ተጫውቷል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ፥ ፍቅር ባጋጣሚ ፣ ታስጨርሽኛለሽ፣ ፍቅር በይሉኝታ፣ አልወድሽም፣ ወንድሜ ያቆብ፣ ኢንጂነሩ እና ጥቁር እና ነጭ ተጠቃሽ ናቸው። አርቲስት ተዘራ ባለትዳር እና የአራት ልጆች አባት ነበር።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
25 ዩሮ🤔 25,000 ዩሮ ተብሎ ቢታረም!
የአምባሳደሩ አስክሬን ተሸኘ!

ከአንድ ወር በፊት በመኖሪያ ቤታቸው ሞተው የተገኙት በኢትዮጵያ የካሜሩን አምባሳደር አስከሬን ተሸኘ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሂሩት ዘመነ በአፍሪካ ሕብረት ዋና አዳራሽ በተደረገው የቀድሞው በኢትዮጵያ የካሜሩን አምባሳደር ጃኩዌስ አልፍረድ አስከሬን ሽኝት ፕሮግራም ተገኝተው ነበር፡፡

ምንጭ፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ልጃችንን አፋልጉን!

በምስሉ የምትመለከቱ ዛኪር ኢብራሂም በቀን 24/12/2011 ልዩ ቦታው ደብረ አባይ አግማስ ዉሀ አካባቢ ከቀኑ በ4:00 ቀይ ሱሪ እርሳስ ከለር ሹራብ ለብሶ እንደወጣ አልተመለሰም ይህንን ልጅ ያየ ወይም ያለበትን ቦታ የሚያቅ ካለ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ስልክ ቁጥሮች ደውለው ቢያሳውቁን ወረታ ከፋይ ነን ይላሉ ቤተሰቦቹ።
09-20-59-43-00
09-12-05-86-60
ልጃችንን አፋልጉን!

ተማሪ ኦብሴ ካሳ ነሐሴ 27 ቀን 9:30 2011 ዓ.ም ከቤት አንደወጣኝ አልተመለሰችም። ተማሪ ኦብሴ ያለችበትን ያሚየእቅ በስልከ ቁጥር 0911944549 -- 0915794729 ደውለችሁ ብታሳውቁን ወራታውን በእግዚአብሔር ስም እንከፍላለን። ቤተሰቦቿ!
ልጃችንን አፋልጉን!

ይህች ህፃን ከሞጣ አካባቢ ተነስታ ወደ አዲስ አበባ ዘመድ ጋር ብላ ጠፍታብናለች እድሜዋ 12 ነው እባካችሁ ተባበሩን። ስሟ ባንቺግዜ ባዬ ትባላለች ቤተሰቦቿ በጭንቀት ላይ ናቸው ፡፡ አጋጣሚ ያየ ካለ በዚ ቁጥር ያሳውቀን
0912222823
0910737379 ደውላቹ ልታሳውቁን ትችላላቹ ፈላጊ ቤተሰቦቿ
ADDIS HOLIDAY IS BACK!!!

ዘጠኝ አመታትን ያስቆጠረው Addis holiday lunch ካለፉት አመታት በተጠናከርረ ሁኔታ እንደገና ተመልሷል !

በትልልቅ የኢትዮጲያን በአል ላይ ( በአዲስ አመት፣በገና እና ፋሲካ) የሚደረገው Addis Holiday Lunch ወጣት በጎ ፍቃደኞችን በማስተባበር ከ 1000 በላይ ለሆኑ ጎዳና ተዳዳሪ ልጆች ፣ ወጣቶች እና አዛውንቶችን ተደራሽ ያደረገ ነው::
ይሄ መልካም ተግባር በዋናነት የበአሉ እለት የምሳ ፕሮግራም በማድረግ በበአሉ ቀን ምንም ሳይሰማቸው ደስተኛ ሆነው እንደማንኛውም የኢትዮጲያ ህብረተሰብ በአሉን እያከበርን እንድንውል እና ከዛም በተጨማሪ የልብስ ድጋፍ ምናረግላቸው ይሆናል:: እኛም ይሄን ሃላፊነት ስንወስድ በጣም በደስታ በመሄኑ እናንተም በዚሁ መልካም ስራ ላይ እንድትሳተፉ ስንል በአክብሮት እንጠይቃለን::

እንዴት መርዳት እንችላለን?????

ያገለገሉ ፣ ያጠርዎት ወይም በዚህ ሰአት የማይለብሱት ልብስ ለነሱ በጣም ይጠቅማል እና እነዚህን ልብሶች ከ እርስዎ ፣ ከ ቤተሰብ፣ ከ ጓደኛዎት፣ ከ ጎረቤት ፣ ከስራ ቦታ እና ከመሳሰሉት በመሰብሰብ እና ለኛ በመስጠት በአሉን በጣም ደስተኛ ሆነው እንዲውሉ እናርጋቸው::

እናም እነዚህን ድጋፍ ለማድረግ ያሰበ ማንኛውንም ሰው ለመቀበል ደስተኛ ሆነን እየጠበቅንዎት ስለሆነ እና ሌላ ጥያቄ እና አስተያየቶች ካላቹ ከዚህ በታች ባሉት ስልቅ ቁጥሮች ይደውሉልን እና ያነጋግሩን ስንል በአክብሮት እንጠይቃለን::

Rotaract club of Atrons President Yeabsera --- +251922175164. (Or Natnael -@Natysf +251923594536, Sofonias - @SophoDarik +251 92 453 9140
👍1