TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ኦነግ 600 የሚሆኑ አባላቶቹ በመንግስት እንደታሰሩበት አስታወቀ! የኦሮሞ ነፃነት ግንባር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ እየሰጠ ይገኛል፤ ኦነግ በመግለጫው 600 የሚሆኑ አባላቶቹ በመንግስት መታሰራቸውን አስታውቋል። ኦነግ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ብንወስንም የድርጅታችን አመራሮች እና አባላትን ማሰር እና ማጠልሸት እየተሰራ ነው ብሏል። በኦነግ እና በሕወሓት መካከል አለ እየተባለ የሚወራው ግንኙነት…
#UPDATE

የኦነግ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ዛሬ የተሰጠው መግለጫ የፓርቲያቸው እውቅና እንደሌለውና እርሳቸውም ስለ መግለጫው መረጃ እንደሌላቸው #ለቢቢሲ ተናግረዋል።

አቶ ዳውድ ፥ ስለዚህ መግለጫ ምንም የማውቀው ነገር የለም ፤ አንጀንዳውም ሆነ አላማው ምን እንደሆነ አይገባኝም፤ ምክትሌም ስለ መግለጫው አላውቅም ብሎ ዛሬ ግን በመግለጫው ላይ ተገኝቷል፤ በአጠቃላይ የማምታት ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።

የኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በቅርቡ ከመኖሪያ ቤታቸው እንዳይወጡ በተደረጉበት ሰዓት በምክትላቸው አቶ አራርሶ ቢቂላ የተመራው ስብሰባ ብዙ የተምታታ ነገር አለበት ብለዋል፤ ጉዳዩን የፓርቲው የህግና ቁጥጥር ኮሚቴ እያጣራ እንደሆነም ተናግረዋል።

አቶ ዳውድ በፓርቲያቸው ውስጥ እየተፈጠረ ላለው ልዩነት ኦነግ በመንግስት ኢላማ ተደርጓል በሚል መንግስትን ተጠያቂ አድርገዋል ሲል ቢቢሲ በዛሬ ምሽት ስርጭቱ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia