ምስራቃዊ ሶሪያ ውስጥ በተፈፀመ ጥቃት የሰዎች ህይወት አለፈ!
በምሥራቃዊ ሶሪያ ውስጥ በአውቶብሶች ላይ በተፈጸመ ድንገተኛ ጥቃት ቢያንስ 28 ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረና ሁሉም ወታደሮች ሊሆኑ እንደሚችሉ ተገለጸ።
የሶሪያ ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ እንደገለጸው አውቶብሶቹ ዴር አል ዘር ተብሎ በሚታወቀው ግዛት ረቡዕ እለት ነው ኢላማ የተደረጉት።
በጥቃቱም በርካታ ዜጎች ተገድለዋል ብሏል ጣቢያው።
ነገር ግን አንዳንድ ምንጮችና ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ አውቶብሱ ውስጥ ወታደሮች እንደነበሩ እና የሟቾች ቁጥር ከዚህም በላይ ከፍ ሊል እንደሚችል አስታውቀዋል።
ከጥቃቱ በኋላ ወዲያው ኃላፊነቱን የወሰደ ቡድን አልነበረም።
መቀመጫውን UK ያደረገው የሶሪያ ሰብአዊ መብቶች ተቆጣጣሪ ድርጅት ጥቃቱን የፈጸመው #አይኤስ እንደሆነ በመግለጽ የሟቾች ቁጥር ደግሞ 37 ነው ብሏል።
ድርጅቱ በቦታው ላይ የነበሩ ምንጮችን በመጥቀስ ''ጥቃቱ በተቀናጀ መልኩ በአይኤስ አባላት የተካሄደ ነው ብሏል።
መንግስትን የሚደግፉ ታጣቂዎችና ወታደሮችን የጫኑ ሶስት አውቶብሶች ላይ ጥቃት ተፈጽሟል'' ሲል ነው መግለጫ ያወጣው። ~ BBC
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

❤1👍1