#ኮማንድ_ፖስት
በቡኢ የኮማንድ ፖስት ግብረኃይል መቋቋሙ ተሰማ።
የቡኢ ከተማ አስተዳደር ፤ " ከክልል አደረጃጀት ጋር ተያይዞ መንግስት ካስቀመጠው አቅጣጫ ውጭ ግጭት ቀስቃሽ የሆኑ ተግባራትን መፈጸም ወይም ይዞ መንቀሳቀስ አይቻልም " ሲል አሣውቋል።
በከተማ አስተዳደሩም የኮማንድ ፖስት ግብረ ሀይል በዛሬው ዕለት መቋቋሙን ገልጿል።
" አብዛኛው ማህበረሰብ መንግስት ያስቀመጠውን አቅጣጫ ተቀብሎ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል " ያለው የቡኢ ከተማ " " ነገር ግን አንዳንድ ሠርጎ ገቦች ሊኖሩ ስለሚችሉ ህብረተሰቡ የእነዚህ አፍራሽ አካላት ሴራ ሰለባ እንዳይሆን እራሱን መጠበቅ ይኖርበታል " ብሏል።
ከዛሬ 29/2014 ዓ.ም ጀምሮም በከተማው ውስጥ " ጉራጌ ክልል ወይም ክላስተር አንቀበልም " የሚሉ ተሸርቶችን ፣ኮፊያዎችን እና ባነሮችን ይዞ ወይም ለብሶ መውጣት እንደማይቻል አሳስቧል።
ከሰሞኑን የደቡብ ክልል ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ለሁለት ተከፍለው ክልል ለመመስረት በምክር ቤቶቻቸው ውሳኔ አሳልፈው ትላንት ለፌዴሬሽን ም/ቤት አቅርበዋል በዝርዝሩ ውስጥ የጉራጌ ዞን የለበትም።
በሁለት ተከፍሎ ከአጎራባች ዞኖች ጋር አንድ ክልል ይመሰርታል ከተባሉት ውስጥ አንዱ የጉራጌ ዞን ሲሆን ዞኑ በአዲሱ ክልል አደረጃጀት ዙሪያ እስካሁን በምክር ቤት ተሰብስቦ አልወሰነም / አላፀደቀም።
የዞኑ የኮሚኒኬሽን እና ሚዲያ ቡድን መሪ አቶ ፈቃዱ ዘለቀ ከቀናት በፊት ፤ " የህዝቡ ጥያቄ በክልልነት ለመዋቀር ነዉ ይሄንንም ለፌደሬሽን ምክር ቤት አቅርበናል ምላሹን እየጠበቅን ነው " ሲሉ ገልፀው ፤ የዞኑ ም/ቤት እስካሁን በአዲሱ አደረጃጀት ዙሪያ እንዳልተወያየትና በቀጣይ በጉዳዩ መቼ ውይይት እንደሚደግ እንደማይታወቅ ገልፀው ነበር።
@tikvahethiopia

👍733👎252❤29😢22🙏20🥰17👏9
#ኮማንድ_ፖስት
በጉራጌ ዞን በማንኛውም ቦታ ማንኛውም አይነት መንግስታዊም ይሁን መንግስታዊ ያልሆነ ስብሰባ፣ ውይይት ማካሄድ ተከለከለ።
በተጨማሪ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ላይ ገደብ ተጥሏል።
ውሳኔው የተላለፈው በዞኑ የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት አስቸኳይ ስብሰባውን ካካሄደ በኃላ መሆኑን ከወልቂጤ ከተማ ኮሚኒኬሽን ያወጣው መረጃ ያሳያል።
በዚህም ኮማንድ ፖስቱ ፦
- ከዛሬ ነሀሴ 12 ጀምጎ በዞኑ በማንኛውም ቦታ ማንኛውም አይነት መንግስታዊም ይሁን መንግስታዊ ያልሆነ ስብሰባ፣ ውይይት ማካሄድ ከልክሏል።
- በመንግሥት የስራ ሰአት የቢሮ ሀላፊም ይሁን ባለሙያ በቢሮ አለመገኘት እንደማይችል አሳስቧል።
- የንግድ ሱቆችና ተቋማትን ያለምንም ምክንያት መዝጋትም ከልክሏል።
- ማንኛውም ሰልፍና መሰል እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ከልክሏል።
- የሞተር ሳይክል እንቅክቃሴ እስከ ምሽት 1 ሰአት ብቻ እንዲሁም የባጃጅ እንቅስቃሴ እስከ ምሽት 2 ሰአት ድረስ ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ አዟል።
ኮማንድ ፖስቱ የተላለፉትን ትእዛዛት በሚተላለፉ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ ማስጠንቀቁን በወልቂጤ ከተማ ኮሚኒኬሽን ገፅ ላይ የሰፈረው መረጃ ያሳያል።

👎839👍597👏24😱22😢17❤14🥰10🙏1