#Hawassa
ከሰሞኑ በሀዋሳ ከተማ የሚከሰተዉን የዋይፋይ (WiFi) አገልግሎት መቋረጥ ተከትሎ በርካቶች ስራችን ላይ እንቅፋት እየተፈጠረ ነው ሲሉ ቅሬታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
እየተፈጠረ ላለው ችግር ኢትዮ ቴሌኮም አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት ሲያስተካክለዉ ቢታይም አገልግሎቱ 24 ሰአት እንኳን ሳይቆይ መልሶ ሲቋረጥ ይስተዋላል።
በዚህም ተገልጋዮች ላልተገባ ወጭ እና እንግልት እየተዳረጉ መሆኑን ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም የደረሱትን ቅሬታዎች ይዞ የሚመለከተውን አካል አነጋግሯል።
በጉዳዩ ላይ ጥያቄ ያቀረብንላቸው በኢትዮ ቴሎኮም ፤ የደቡብ ሪጅን ዳይሬክተሩ አቶ ጁነዲን አብዱልቃድር " ችግሩ መኖሩ ግልጽ ነው " በማለት አሁን ላይ እንዲህ ያለው የስርቆት ሁኔታ በሁሉም አካባቢ አሳሳቢ መሆኑን ያነሳሉ።
አቶ ጁነዲን አክለዉም ፤ ኬብሉ ከውጭ በውድ ገንዘብ ተገዝቶ ለማህበረሰቡ አገልግሎት የሚውል በመሆኑ ችግሩን ለመቅረፍ ማህበረሰቡ ከፖሊስ ጋር ተጣምሮ ሊጠብቀው ይገባል ብለዋል።
በዚህ በኩል በሀዋሳም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች ትልቅ እንቅስቃሴ መኖሩን የገለፁት ደግሞ በሪጅኑ የህግ ጉዳይ ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ተድላመድህን ቀለመወርቅ ፤ " እስካሁን በተደረጉ እንቅስቃሴዎችም በርካታ ተጠርጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።
ስርቆቱ #በሀዋሳ እና #ሻሸመኔ ከፍ ያለ መሆኑን የሚገልጹት አቶ ተድላመድህን ካለፈዉ ሀምሌ 1 እስከ ታህሳስ 30 እንኳን በሀዋሳ ከተማ ብቻ 4 መዝገብ ላይ ውሳኔ ተሰጥቶ ከስድስት እስከ ሁለት አመት እስራት መፈረዱን አንስተዋል።
በሀገር ደረጃ የመሰረተልማት እንቅስቃሴዎችን ለመጠበቅ ታስቦ የወጣዉን 464/67 የተባለ አዋጅ መሰረት አድርጎ ያለመክሰስ ያለመመርመርና ውሳኔ አለመስጠት ችግር ፈተና እንደሆነባቸው ገልጸዋል።
የሚሰጡ ውሳኔዎች እስከ 20 አመት የሚዘልቁ ቢሆኑም ያ እየሆነ አለመሆኑን የሚገልጹት ስራ አስኪያጁ " በዚህ ቻሌንጅ ውስጥ ሆነንም ቢሆን አስተማሪ የሆኑ ውሳኔዎች እንዲሰጡ እየሰራን ነው " ብለዋል።
መረጃው ተዘጋጅቶ የተላከው በሀዋሳዉ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
@tikvahethiopia

😡112❤75👏11🕊10😢7😭7😱6🙏6🥰4