TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወ/ሮ አያንቱ ሙስጠፋ ላይ የተፈፀመው ምንድነው ?

ወ/ሮ አያንቱ ሙስጠፋ ነዋሪነቷ በምስራቅ ሀረጌ ዞን ኮምቦልቻ ወረዳ ቀበሌ 02 ነው።

በ2008 ዓ/ም ነው ከባለቤቷ አቶ አሪፍ አልዬ ጋር በጋብቻ የተሳሰረችው።

ላለፉት 8 ዓመታት በትዳር ስትቆይ 2 ወንድ ልጆችን አፍርተዋል።

ጥር 15 ቀን 2016 ዓ/ም ፍፁም ባልጠበቀችው ሁኔታ በገዛ ባለቤቷ እና የልጆቿ አባት ዘግናኝ በሆነ መንገድ በአሲድ ተቃጥላለች። አንድ አይኗንም አጥታለች።

ከባለቤቷ ጋር በተደጋጋሚ አለመግባባቶች ቢፈጠሩም ይህን ያደርግብኛል ብላ በፍፁም አልጠበቀችም።

ወ/ሮ አያንቱ ሙስጠፋ ፦

" በዕለቱ (ጥር 15  ቀን 2016) ቀን ስራ ውዬ ልጆቼን ከቤተሰቦቼ ጋር ይዤ ወደ ቤት ገባሁ።

ማታ ተሰብስበን እራታችንን በላን እጅግ ደክሞኝ ስለነበር ልጆቼን በግራ እና በቀኝ አስተኝቼ እኔም ተኛው።

በዛ ቀን ምን ክፉ ደግ አልተነገርንም። ከለሊቱ 9 ሰዓት ተኩል አካባቢ #አሲድ በማስታጠቢያ አድርጎ በተኛሁበት በጭንቅላቴ አፈሰሰብኝ።

ወይኔ ጭንቅላቴን ተቃጠልኩ ! ብዬ ከተኛሁበት ተነስቼ እጁን ልይዘው ስሞክር ' ገና መቼ ተቃጠልሽ ' ብሎ አሲዱን አይኔ ውስጥ ጨመረው።

ያኔ አንዱ አይኔን ለማትረፍ በእጄ ሸፍኜ በሩን ለመክፈት ስሞክር የተረፈውን አሲድ ጀርባዬ ላይ ረጨብኝ።

ለረጅም ጊዜ #በቅናት ምክንያት ያስቸግረኝ ነበር። ከዛሬ ነገ ይሻለዋል እያልኩኝ አብሬው ቆየሁ። በዚህ ውስጥ ነው 2 ልጆች የወለድነው።

በተደጋጋሚ ይዝትብኝ የነበረ ቢሆንም እንዲህ ይጨክናል ብዬ አላሰብኩም። "

እንደ ሀረማያ የሕይወት ፋና ሆስፒታል መረጃ ከሆነ በወ/ሮ አያንቱ ላይ የደረሰው ቃጠሎ 3ኛ ደረጃ የሚባለው ነው። የአሲድ ጥቃቱ በአይኗ፣ በጭንቅላቷ፣ ፊቷ ላይ ፣ ደረቷ ፊት ፣ እጇ ላይ ጉዳት ደርሷል።

የቀኝ አይኗ ላይ በአሲድ ቃጠሎው ምክንያት የብሌን ጉዳት ስላጋጠመ ማየት አትችልም። የግራውን ግን በህክምና ማትረፍ ተችሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመረጃው ባለቤት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ (ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ታደሰ) እውቅና ይሰጣል።

@tikvahethiopia
😭1.9K😡295128😢66😱22🥰10🙏8🤔6👏4