TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
216 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ቲክቶክ ወደ ፍርድ ቤት አመራ። ቲክቶክ የተሰኘው የቪድዮ ማጋሪያ የማህበራዊ ሚዲያ ለአሜሪካ ኩባንያ የማይሸጥ ከሆነ በመላ አሜሪካ ለመታገድ ተቃርቧል። እግዱ ተግባራዊ እንዳይደረግ ወይም ውድቅ እንዲሆን ቲክቶክ ወደ አሜሪካ ፍርድ ቤት አምርቷል፤ ሙግትም ከፍቷል። መተግበሪያው ለፍ/ቤት ባቀረበው የአቤቱታ መዝገብ " ከ9 ወር - 1 ዓመት ባለው ጊዜ ቲክቶክ ካልተሸጠ #ይታገድ " የሚለው ሕግ ኢ-ሕገመንግስታዊ…
'ቲክቶክ' ን ሙሉ በሙሉ / በከፊል ያገዱ ሀገራት የትኞቹ ናቸው ?

1ኛ. ህንድ

ቲክቶክን ያገደችው በ2020 ላይ ነው። በድንበር አካባቢ ከቻይና ጋር የተፈጠረው #ግጭትን ተከትሎ ነው ለደህንነት በሚል ቲክቶክን እና ሌሎች ከቻይና ጋር የተገናኙ መተገበሪያዎችን ያገደችው።

በወቅቱ በሀገሪቱ 200 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ነበሩ።

2. አፍጋኒስታን

ቲክቶክን በ2022 ያገደች ሲሆን ምክንያቷ ደግሞ ወጣቱ ትውልድ በተሳሳተ አቅጣጫ እንዳይሄድ ለመከላከል ነበር።

3.  አውስትራሊያ

በፌዴራል መንግሥት ማንኛውም ኤሌክትሮኒክስ ማሳሪያ ላይ እንዳይሰራ ተደርጓል። ከደህንነት ጋር በተያያዘ

4. ቤልጂየም

ከደህንነት ስጋት ጋር በተያያዘ ቲክቶክን በፌደራል የህዝብ አገልግሎት መሳሪያዎች ላይ እንዳይሰራ ጊዜያዊ እገዳ ጥላለች።

5. ካናዳ

ከደህንነት ጋር በተያያዘ የፌዴራል መንግሥት መሳሪያዎች ላይ ታግዷል።

6. ዴንማርክ

የሀገር መከላከያው ሚኒስቴር ማንኛውም ሰራተኛ በስራ ስልኩ ቲክቶክ እንዳይጠቀመ ያገደ ሲሆን ሁሉም ሰራተኛ ጭኖት የነበረውን መተግበሪያ እንዲያጠፋ አስደርጓል።

7. የአውሮፓ ህብረት

ሰራተኞች ሚጠቀሙበት መሳሪያ ላይ ታግዷል። የፓርላማው ህግ አውጭዎች እና ሰራተኞችም ከኤሌክትሮኒክ መሳሪያቸው ላይ እንዲያስወግዱ ተደርጓል።

8. ፈረንሳይ

ከደህንነት ጋር በተያያዘ ቲክቶክና ሌሎች እንደ X ፣ ኢንስታግራም ያሉ መተግበሪያዎችን የመንግስት ሰራተኞች ስልካቸው ላይ ለ 'መዝናኛ' በሚል እንዳይጠቀሙ ታግደዋል።

9. ላቲቪያ

ከደህንነት ጋር ተያይዞ በሁሉም የላቲቪያ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት ኤሌክትሮኒክስ እንዳይሰራ ታግዷል።

10. ኔዘርላንድስ

ማዕከላዊ መንግሥት ቲክቶክ ጨምሮ ሌሎችንም መተግበሪያዎች ከደህንነት ጋር በተያያዘ ከሰራተኞች ስልክ ላይ እንዲታገዱ አድርጓል።

11. ኔፓል

ማህበራዊ መስተጋብር በመሸርሸር፣ ወጣቶችን ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ በመውሰድ በሚል ሙሉ በሙሉ ነው ያገደችው።

12. ኒውዚለንድ

የፓርላማው ህግ አውጪዎችና ሰራተኞች በሙሉ ስልካቸው ላይ ቲክቶክ እንዳይኖር ታግደዋል፤ ይህ ከደህንነት ጋር በተያያዘ ነው።

13. ኖርዌይ

ከመላው የኖርዌይ ፓርላማ የስራ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ላይ እንዲታገድ ተደርጓል። የመንግስት ሰራተኞች ስልካቸው ላይ እንዳይጭኑ ታዟል።

14. ፓኪስታን

ከ2020 ጀምሮ ቢያንስ ለአራት ጊዜ በጊዜያዊነት አግዳለች ይህም ከስነ ምግባር ያፈነገጠ ይዘትን ያስተዋውቃል በሚል ነው።

15. ሶማሊያ

መንግሥት ቲክቶክ፣ ቴሌግራምና 1 የቁማር ድረገጽ እንዳይሰሩ እንዲያደርጉ አዟል። መተግበሪያዎቹ የጽንፈኝነት መፈንጫ ሆነዋል በሚል ነው።

16. ታይዋን

ከደህንነት ጋር ተያይዞ ከሁሉም መንግሥታዊ መሳሪያዎች ከስልክ ፣ ታብሌት ፣ ኮምፒዩተር ፣ እንዳይሰራ ተደርጓል።

17. ዩናይትድ ኪንግደም

የመንግስት ሚኒስትሮችና የመንግስት ሰራተኞች ከሚጠቀሙባቸው የሞባይል ስልኮች እንዳይሰራ ታግዷል። ፓርላማው ከኦፊሴላዊ መሳሪያዎችና ኔትዎትክ ላይ አግዷል። ይህ ከደህንነት ጥንቃቄ ጋር በተያያዘ ነው።

18. ኪርጊስታን

የልጆች አእምሯዊ፣ መንፈሳዊ እና ሥነምግባራዊ እድገትን ለመጠበቅ በህግ የተዘረዘሩ ህጋዊ መስፈርቶችን ማክበር አልቻለም በሚል ቲክቶክን በሙሉ አግዳለች።

19. አሜሪካ

ከደህንነት ጋር በተያያዘ ከፌደራል ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች እንዲታገድ ተድርጓል። ከ50 ግዛቶች ከግማሽ በላይ የሚሆኑት መተግበሪያውን ከይፋዊ የመንግስት መሳሪያዎች ላይ አግደዋል።

አሁን ሙሉ በሙሉ ልታግድ ጫፍ ደርሳለች።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፤ መረጃውን ያሰባሰበው ከዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ነው።

@tikvahethiopia
👏1.41K278😡94🙏58😭40😱27🤔24🕊23😢20🥰19