TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ደቡብ_አፍሪካ

• " የመንግሥት ለውጥ በምርጫ እንጂ በግርግር  አይመጣም " - ፕሬዜዳንት ሲሪል ራማፎሳ

• " መንግሥት እየተንቀጠቀጠ ነው ፤ ፈርቷል " - የራማፎሳ ተቃዋሚ ጁሊየስ ማሌማ (የኤኮኖሚ ነጻ አውጪዎች ፓርቲ)

• በተቃውሞው ሳቢያ የንግድ መደብሮች ገና ካሁኑ ሥጋት አድሮባቸዋል።

#በመጪው_ሳምንት በደቡብ አፍሪካ የተቃውሞ ሰልፍ ይካሄዳል ተብሎ ታቅዷል።

በዚህም ሳቢያ የአገሪቱ መንግሥት ቁልፍ የሚባሉ መሠረተ-ልማቶችን ለመጠበቅ እና የጸጥታ ጥበቃውን ለማጠናከር የሀገሪቱን ጦር (ወታደሮች) እንዳሰማራ ዶቼ ቨለ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎትን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።

ጁሊየስ ማሌማ የሚመሩት ግራ ዘመም የኤኮኖሚ ነጻ አውጪዎች ፓርቲ በመጪው ሰኞ በመላ ደቡብ አፍሪካ የሥራ ማቆም አድማ መጥራቱ ተነግሯል።

ፓርቲው ፕሬዝደንት ሲሪል ራማፖሳ የደቡብ አፍሪቃን ኤኮኖሚ በመሩበት ስልት፣ በመብራት እጥረት እና እየበረታ በሚሔደው የሥራ አጥነት ሳቢያ ከሥልጣን መልቀቅ አለባቸው የሚል አቋም አለው።

የደ/አፍሪቃ ጦር ለአገሪቱ ፖሊስ እገዛ እንዲያደርግ መታዘዙን አስታውቋል።

ጦሩ በእጁ በሚገኙ የስለላ መረጃዎች መሠረት ሥጋት አለባቸው የተባሉ ቁልፍ ቦታዎችን ለመጠበቅ ከትላንት አርብ ጀምሮ ለአንድ ወር ወታደሮች አሰማርቷል።

ከዚህ በተጨማሪ ከጸጥታ አስከባሪ ተቋማት አቅም በላይ ለሚፈጠሩ ኩነቶች ወታደሮች ምላሽ ይሰጣሉ ተብሏል።

የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ አንድ ዓመት የቀረው ሲሆን ፕሬዜዳንት ራማፎሳ የታቀደው ሰልፍ " ፖለቲካዊ ሴራ ነው "  የሚል አቋም አላቸው።

ፕሬዜዳንቱ ባለፈው ሐሙስ " ሥርዓተ-አልበኝነት እና ግርግር እንደማይፈቀድ " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ራማፎሳ የመንግሥት ለውጥ " በምርጫ እንጂ በግርግር " እንደማይመጣም ገልጸዋል።

የኤኮኖሚ ነጻ አውጪዎች ፓርቲ መሪ ጁሊየስ ማሌማ ትላንት በስዌቶ ለደጋፊዎቻቸው " ማንም አብዮትን ሊያስቆም አይችልም " ሲሉ ተናግረዋል።

" መንግሥት እየተንቀጠቀጠ ነው፤ ፈርቷል " ያሉት ማሌማ ራማፎሳ ከሥልጣን እንዲወርዱ ጠይቀዋል።

በተቃውሞው ሳቢያ የንግድ መደብሮች ገና ካሁኑ ሥጋት እንደገባቸው የፈረንሳይ ዜና አገልግሎትን ዋቢ በማድረግ ዶቼ ቨለ ዘግቧል።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
👍1.12K127👎89🕊82😢36🤔21🙏16😱15🥰10