TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#EHRC

" ቀድሞውኑ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ለዓመታት በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ አስቸጋሪ ሕይወት ይመሩ የነበሩ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች #ለሞት እና #ለአካል_ጉዳት መዳረጋቸው አሳሳቢ ነው " - ራኬብ መሰለ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በሶማሊ እና በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ አካባቢ፣ በሁለቱ ክልሎች የጸጥታ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ የተኩስ ልውውጥ ምክንያት በአካባቢው የተጠለሉ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና የአካባቢው ነዋሪዎች መጎዳታቸው ዛሬ ባወጣው መግለጫ ይፋ አድርጓል።

ኮሚሽኑ ፤ መስከረም 7 ቀን 2016 ዓ.ም. በባቢሌ አቅራቢያ በኦሮሚያ እና በሶማሊ ክልል የጸጥታ ኃይሎች መካከል የተፈጠረውን የተኩስ ልውውጥ በተመለከተ ተጎጂዎችን፣ የኦሮሚያ እና የሶማሊ ክልል የጸጥታ አካላትን፣ የቆሎጂ መጠለያ ሠራተኞችን እና የሆስፒታል ባለሞያዎችን አነጋግሯል።

በአሁኑ ወቅት ግጭቱ የቆመ ቢሆንም፤ በተኩስ ልውውጡ ወቅት " ቆሎጂ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ " የሚኖሩ ቢያንስ 6 ተፈናቃዮች ተገድለዋል፣ በርካታ ሰዎች ቆስለዋል እንዲሁም በሌሎች የአካባቢው ሲቪል ሰዎች ላይ የሞት እና የአካል ጉዳት ደርሷል ብሏል።

ስለዚህም ሁለቱ ክልሎች በቅንጅት በመሥራት በአካባቢው ለተከሰተው ግጭት ምክንያት ለሆኑ ጉዳዮች ሰላማዊ መፍትሔ በመስጠት የነዋሪዎችን እና የተፈናቃዮችን ደኅንነት በዘላቂነት የማረጋገጥ ሥራ እንዲሠሩ፣ ለደረሰው ጉዳት ተጎጂዎች እንዲካሱ እና ተገቢ የሆነ ጥንቃቄ ባለማድረግ በሲቪል ሰዎች ላይ ጉዳት እንዲደርስ ባደረጉ የጸጥታ ኃይሎች አባላት ላይ አስፈላጊው ምርመራ ተደርጎ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ ያስፈልጋል ሲል አሳስቧል።

የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተፈጠረው ግጭት ወቅት በሲቪል ሰዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ የነበረባቸው መሆኑን ጠቅሰው “በተለይም ቀድሞውኑ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ለዓመታት በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ አስቸጋሪ ሕይወት ይመሩ የነበሩ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ለሞት እና ለአካል ጉዳት መዳረጋቸው አሳሳቢ ነው " በማለት ገልጸዋል።

ምክትል ዋና ኮሚሽነሯ አክለውም " በአፍሪካ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ጥበቃ እና እገዛን አስመልክቶ የተደረገው የአፍሪካ ሕብረት ስምምነት (ካምፓላ ስምምነት) መሠረት የመንግሥት የጸጥታ አካላት የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሚገኙባቸውን የመጠለያ ጣቢያዎች ደኅንነት አደጋ ላይ ሊጥሉ ከሚችሉ ተግባራት ሊቆጠቡ ይገባል " ብለዋል፡፡

@tikvahethiopia
😢22569🕊36🙏24😡21😱9🥰3
TIKVAH-ETHIOPIA
" የተስፋፋዉ የሙስና ሰንሰለት ሙሉ በሙሉ የሀብታም ልጅ በገንዘቡ ፤ የባለስልጣንም ልጅ በስልጣኑ ስራ እንዲቀጠር ሲያደርገው ሌላው የድሀ ልጅ ከስራ ውጭ አድርጎታል ! " - ነዋሪዎች (ከሰሞኑን በሚዛን አማን በነበረ ህዝባዊ ውይይት ላይ የተነሳ) #ቲክቫህኢትዮጵያ @tikvahethiopia
" የሀብታም ልጅ #በገንዘቡ የባለስልጣን ልጅ #በስልጣኑ ስራ እንዲቀጠር ሲያደርገዉ ሌላዉን የድሀ ልጅ ከስራ ውጭ አድርጎታል " - ነዋሪዎች

ሰሞኑን በሚዛን አማን ከተማ ህዝባዊ የውይይት መድረክ ተካሂዶ ነበር።

ይኸው ውይይት በደቡብ ኢትዮጵያዊ ህዝቦች ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደና በቤኒሻንጉል ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ የተመራ ነበር።

በህዝብ ወይይቱ በርካታ ጥያቄዎች ቀርበዋል።

ከነዚህ መካከል ፦

እንደካሮት ቁልቁል የሚሄደዉ የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ለምን ባለቤት አጣ ? ተመዘበረበት የተባለዉን ገንዘብ ጉዳይ የያዘዉ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ወዴት አደረሰው ?

ያለብን የመንገድ ችግር አሁንም እናቶች በህክምና እጦት #ለሞት እየዳረገ ነው። መፍትሄ ለምን አይሰጥም ? የሚሉት ይገኙበታል።

ሌላው የተስፋፋዉ የሙስና ሰንሰለት ሙሉ በሙሉ የሀብታም ልጅ በገንዘቡ ፤ የባለስልጣን ልጅ በስልጣኑ ስራ እንዲቀጠር ሲያደርገዉ ሌላዉን የድሀ ልጅ ከስራ ዉጭ አድርጎታል ሲሉ የውይይቱ ተሳታፊዎች ያላቸውን ከፍተኛ ቅሬታ አሰምተዋል።

ተሳታፊዎቹ መንግስት ቁርጠኛ አመራር በመስጠት ስርአቱን ሊያስተካክለዉ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በእለቱ መድረኩን የመሩት የደቡብ ኢትዮጵያዊ ህዝቦች ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ፤ ፣ ሌብነትና ብልሹ አሰራር በመንግሥት በኩል ቀይ መስመር በማለት ያስቀመጠዉ ጉዳይ ነው " ሲሉ  ገልጸው ችግሩን በመቅረፉ ሂደት ህዝቡ ከመንግስት ጎን ሊቆምና ሊታገል ይገባል ብለዋል።

መረጃው በሀዋሳው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የተዘጋጀ ነው።

@tikvahethiopia
🥰22291😭69🙏43👏34😡14😢11😱5🕊2