TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.61K videos
217 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update 🔹" ችግር ላይ ላለዉ መምህር ተገቢ ያልሆነ መልስ ነው የተሰጠን " - መምህራን 🔸 " ችግሩን ለመፍታት መግባባት ላይ ተደርሶ ወደስራ የሚያስገቡ እንቅስቃሴዎች አሉ ፤  ከሰኞ ጀምሮ ወደአካባቢዉ እናቀናለን " - የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ በማዕከላዊ ኢትዮጰያ ክልል ሃዲያ ዞን የባዳዋቾ ወረዳና የሾኔ ከተማ ትምህርት ቤቶች አሁንም አለመከፈታቸዉ ተሰምቷል። በባዳቾች ወረዳና ሾኔ ከተማ…
" ቃል የተገባልን ውዝፍ ደመወዛችን ስላልተከፈለን እዳችን መክፈል አልቻልንም " -  የባድዋቾ ወረዳና የሾኔ  መምህራንና የጤና ባለሙያዎች

በሀድያ ዞን ባድዋቾ ወረዳና ሾኔ ከተማ በደሞዝ ምክኒያት ተቋርጦ የነበረዉ የትምህርትና ህክምና አገልግሎት ቢጀምርም መንግስት ቃል የገባልን ውዝፍ የደሞዝና የዱቲ ክፍያዎች አልተከፈለንም ሲሉ ቅሬታ አቅርበዋል።

በመምህራን በኩል " ከዞኑ የትምህርት አመራሮች ጋር በተደረሰ መግባባት ያልተከፈሉ ወራቶች ቀስ በቀስ ሊከፈለን ተስማምተን ብንጀምርም እየተከፈለን ያለዉ ስራ ከጀመርንበት ወዲህ ያለዉ ብቻ  በመሆኑ ደሞዝ በቆመባቸው ወራት የገባነዉን እዳ መክፈል አልቻልነም " ሲሉ መምህራን ያለቸውን ቅሬታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበዋል።

በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየታቸዉን ለቲኪቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት የሾኔ ከተማ መምህራን ማህበር ሊቀመንበር አቶ ከበደ መሊሶ የመማር ማስተማር ስራዉ አሁን ላይ #በአግባቡ እየተካሄደና ደሞዝ እየተከፈለ ቢሆንም የመምህራን የተጠራቀመ ደሞዝ ከተለያዩ ገቢዎች ተሰብስቦ እንደሚከፈል ቃል በተገባዉ መሰረት አልተከፈለም በማለት የመምህራኑ ቅሬታ ትክክል መሆኑን አረጋግጠዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የዞኑን ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ለማነጋገር ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርግም አልተሳካም።

በሌላ በኩል " ቀሪ ደሞዛችንና የዲውቲ ክፍያዎች አልተከፈለንም  " ያሉ የሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሰራተኞች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

" መንግስት ቀሪ ያልተከፈለ ደመወዛችንን ከ2012 ዓ/ም  ጀምሮ የተሰበሰቡ ዱቲዎች ድረስ ሊከፍለን ይገባል " ሲሉም ጠይቀዋል።

በዚህም ጉዳይ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሾኔ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ተድላ አካሉን ጠይቋን።

ዶክተር ተድላ ፤ የህክምና ባለሙያዎች ቅሬታ ተገቢ መሆኑንና ችግሩ መኖሩን አረጋግጠዋል።

በበኩላቸዉ ከ2012 ጀምሮ የተጓተተ የዱቲ ክፍያን ጨምሮ የሰራተኛ ማትጊያ ተጨማሪ ክፍያዎችን ለመክፈል ከሀድያ ልማት ማህበር ጋር እየተመካከሩ መሆኑን ገልጸዉ የዘገየዉ የዚህ ወር ደሞዝም በፍጥነት እንዲከፈል ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸዉን ገልጸዋል።

መረጃው ተዘጋጅቶ የተላከው በሀዋሳ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
😡279124😢56🕊28🙏26🥰17👏10😭9