ሹፌሩን እና ረዳቱን #በመግደል 100 ኩንታል ሰሊጥ የጫነን " FSR መኪና " ይዘው ከተሰወሩ ተጠርጣሪ ወንጀለኞች አንዱ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ ገለፀ።
እንደ ደብረወርቅ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መረጃ ፤ ድርጊቱ የተፈጸመው በምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረወርቅ ከተማ አስተዳደር ፤ አባጀምበር ቀበሌ ፤ " የጨረቃን ጎጥ " ነው።
ከ " ገንዳ ውሃ " ከተማ ወደ " አዲስ አበባ " አንድ መቶ ኩንታል ሰሊጥ ጭነው ሲጓዙ የነበሩ ሾፌርና ረዳቱን ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች ሰኔ 28/2015 ዓ/ም ሰዓቱ በትክክል ባልታወቀበት ሁኔታ ገድለው በመጣል መኪናውን ይዘው ይሰወራሉ፡፡
የደብረወርቅ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ከአካባቢው ነዋሪዎች የደረሰውን መረጃ መሰረት በማድረግ በሰራው ክትትል ተጠርጣሪ ወንጀለኛቹ መኪናውን ወደኋላ በመመለስ በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ዲቦ ከተማ ማሳደራቸው መረጃ ይደርሰዋል፡፡
ፖሊስ ተጠርጣሪ ወንጀለኞቹን ክትትል በማድረግ ላይ እያለ ሰኔ 29 ቀን 2015 ዓ/ም መኪናውን ይዘው ወደ ግንደወይን ከተማ በመመለስ ላይ ሳሉ ግንደወይን ከተማ አካባቢ ሲደርሱ በጎንቻ ሲሶ እነሴና በግንደወይን ከተማ አንዱ ተጠርጣሪ ወንጀለኛ #ከመኪናው ጋር በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።
ሌሎች ተጠርጣሪ ወንጀለኞችን ለመያዝ ርብርብ እየተደረገ ነው ሲል የደብረወርቅ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አስታወቋል።
የጎንቻ ሲሶ እነሴና ግንደወይን ከተማ ነዋሪዎች፣ የጸጥታ አካላት ላደረጉት ከፍተኛ ርብርብ ልዩ ምስጋና ቀርቦላቸዋል።
መረጃው የምስራቅ ጎጃም ፖሊስ ነው።
@tikvahethiopia

👍2.08K😢634❤230😱90👎64🙏55🕊54🥰23
#AddisAbaba
ጓደኛቸውን #በመግደል ሲያሽከረክረው የነበረውን መኪና ወስደው ተሰውረዋል የተባሉ ሁለት ግለሰቦች ተያዙ።
የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው ግንቦት 8 ቀን 2016 ዓ/ም በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሰሜን ማዘጋጃ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡
ገ/ሚካኤል ሰይፉ የተባለው ሟች የወንጀል ፈፃሚዎቹ የቅርብ ጓደኛ ነው።
ጓደኛማቻቾቹ በየዕለቱ እየተገናኙ አብረው የሚውሉ፣ የሚዝናኑ እና በእጅጉ የጠነከረ የጓደኝነት ግንኙነት ያላቸው የሱሉልታ ከተማ ነዋሪዎች እንደሆኑ ተጠርጣሪዎቹ ለፖሊስ በሰጡት ቃል አረጋግጠዋል።
በዕለቱ ሟች በወንጀሉ ከተጠረጠሩት ከሁለቱ ጓደኞቹ ጋር አብሮ ሲዝናና እንዳመሸ ታውቋል።
ተጠርጣሪዎቹ ቴዎድሮስ ታከለ እና ሲሳይ ጥላሁን ከምሽቱ 5 ስዓት ገደማ የጓደኛቸውን አንገት በማነቅ ህይወቱ እንዲያልፍ ካደረጉ በኋላ አስክሬኑን መንገድ ላይ በመጣል ሞባይል ስልኩንና መታወቂያውን ጨምሮ በወቅቱ ሲያሽከረክረው የነበረውን የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 4-15624 ኢት መኪና ወስደው ተሰውረዋል።
ፖሊስ የወንጀሉ ሪፖርት ከደረሰው በኋላ ባደረገው ያልተቋረጠ ክትትል ወንጀሉን ፈፅመዋል ተብለው የተጠረጠሩትን ግለሰቦች ለይቶ በማወቅ በ24 ሰዓታት ውስጥ በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል፡፡
አንደኛው ተጠርጣሪ ከአየር ጤና አካባቢ የተያዘ ሲሆን ሁለተኛው ተጠርጣሪ ደግሞ ሱሉልታ ከተማ ውስጥ ሊገኝ ችሏል፡፡
ፖሊስ ግለሰቦቹን በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ ካበናወነው ምርመራ የማስፋት ስራ የሰረቁትን ተሽከርካሪ በሸገር ከተማ " ወለቴ " ተብሎ ወደሚጠራው አካባቢ በመውሰድ እንዲሸጥላቸው ለአንድ ግለሰብ እንደሰጡት አረጋግጧል።
መኪናውም ከቆመበት በምሪት እንዲመለስ ተደርጓል፡፡
ተሽከርካሪውን ለመሸጥ ተስማምቶ ከተጠርጣሪዎቹ የተቀበለውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ለማወል ክትትል እየተደረገ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
#AddisAbabaPolice

😭1.91K❤206👏125😡112😱102🙏60😢58🕊51🤔33🥰20