TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
218 files
4.4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 73 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 2,844 የላብራቶሪ ምርመራ ሰባ ሶስት (73) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 655 ደርሷል፡፡

ቫይረሱ የተገኘባቸው 49 ወንድ እና 24 ሴት ሲሆን የዕድሜ ክልላቸው ከ6 እስከ 75 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት 67 ሰዎች ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ቀሪዎቹ የተለያዩ 6 ሀገራት ዜጎች ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 56 ሰዎች ከአዲስ አበባ (13 ሰዎች በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው፣ 12 ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው እና 31 ሰዎች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው) ፣ 4 ሰዎች ከትግራይ ክልል (ሁሉም የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው)፣ 2 ሰዎች ከአማራ ክልል (በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው)፣ 8 ሰዎች ከሶማሌ ክልል (የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው) እንዲሁም 3 ሰዎች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ድንበር ተሻጋሪ መኪና አሽከርካሪዎች ናቸው።

የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት ፦

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው - 27

• በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው - 15

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር #የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው - 31

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላንትናው ዕለት ሰባት ( 7) ሰዎች (4 ከደቡብ ክልል፣ 2 ከትግራይ ክልልና 1 ሰው ከአዲስ አበባ) ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 159 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia