TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
217 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ከ90 በመቶ በላይ ተማሪዎች ወደ መፈተኛ ማዕከላት ገብተዋል " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ ከ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ጋር በተያያዘ እስካሁን ባለው አፈፃፀም ይህ ነው የሚባል ችግር እንዳልገጠመና አብዛኛው / ከ90 በመቶ በላይ ተፈታኝ ተማሪ / ወደ ዩኒቨርሲቲ መግባቱን ተናግረዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ይህን የተነገሩት ትላንትና ምሽት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የገቡትን ተፈታኝ ተማሪዎችን እና እየቀረበላቸው ያለውን መስተንግዶ በአካል ተገኝተው በተመለከቱበት ወቅት ለብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ቃላቸው ነው።

ከ90 በመቶ በላይ ተማሪ ወደ መፈተኛ ተቋሙ መግባቱን የተገለፁት ሚኒስትሩ ሙስሊሞች እና የ7ኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን አማኞች #ዛሬ እሁድ ጥዋት እንደሚገቡ ፤ ከዚህ በኃላ ሁሉም ተማሪ ገብቶ #እንደሚጠናቀቅ ገልፀዋል።

በሌላ በኩል፤ ነገ ሰኞ ከሚጀምረው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ጋር በተያያዘ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ባስተላለፉት መልዕክት ፤ " ኢትዮጵያ እናንተን ስታይ ተስፋ ነው የሚታያት። " ያሉ ሲሆን " ይህ የምትፈተኑት የ12ኛ ክፍል ፈተና ለኢትዮጵያ እውነተኛ ተስፋዎች መሆናችሁን የምታረጋግጡበት እንደሚሆን አምናለሁ። " ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ " እናንተን እዚህ ለማድረስ ወላጆች፣ መምህራን እና መላው ማኅበረሰብ ለዓመታት ለፍቷል። ውጤቱን የምታሳዩት ከኩረጃና ከስርቆት ነጻ ሆናችሁ፣ በራሳችሁ ተማምናችሁ፣ ፈተናውን ስትፈተኑ ነው። " ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ተማሪዎች የተሰጣቸውን መመሪያ አክብረው ፤ ተረጋግተው ፈተናቸውን እንዲሰሩ እንዲሁም በምንም ነገር እንዳይሸበሩ አደራ ያሉት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ለተፈታኞቹ " የኢትዮጵያ አምላክ ዕውቀቱን ይግለጥላችሁ " ሲሉ መልዕክታቸውን ቋጭተዋል።

@tikvahethiopia
👍2.49K👎478138🙏124🕊111😢51😱40