TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
217 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጥንቃቄ

" ... በግለሰብም ሆነ በድርጅት ደረጃ ለፕሮጀክት ማስፈጸሚያ ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን የእርዳታ ገንዘብ አያድልም " - ገንዘብ ሚኒስቴር

ገንዘብ ሚኒስቴር አርማና ስሙን በመጠቀም #በተሳሳተ_መረጃ ህዝብን በማጭበርብር ላይ ያሉ አካላት እንዳሉ በመግለፅ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስቧል።

ሚኒስቴሩ በግለሰብም ሆነ በድርጅት ደረጃ ለፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የእርዳታ ገንዘብ የማያድል መሆኑ በአጽንኦት ገልጿል።

ለህብረተሰቡ ፥ " ፎርም ሞልታችሁ ላኩ፤ የአባልነት መመዝገቢያ በግል ከሆነ 175 ዶላር በድርጅት ከሆነ 225 ዶላር ላኩ " እያሉ ከሚያጭበረብሩ አካላት እንዲጠነቀቅ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ፤ አርማውን እና ስሙን በመጠቀም የሚያጭበረብሩ አካላትን በተመከተ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ክትትል እያደረግን መሆኑን ገልጿል።

በሌላ በኩል ፤ ሚኒስቴሩ ትክክለኛው የፌስቡክ ገፁ " Ministry of Finance - Ethiopia የሚለውና ከ70ሺ በላይ ተከታዮች ያሉትና ማረጋገጫ (Verification ) ልዩ ምልክት ያለው መሆኑን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
👍3