#ሲዳማ_ክልል
" 26,000 ኢንተርፕራይዞች የከሰሙ መሆናቸውን አረጋጥጠናል " - የሲዳማ ክልል ሥራ፣ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ቢሮ
በአነስተኛ እና ጥቃቅን የተደራጁ ኢንተርፕራይዞች በቦታ ጥበትና ሌሎች መሰል ችግሮች ሥራ ለማቆም እየተገደዱ መሆናቸውን ተደራጆቹ በተደጋጋሚ ቅሬታ ሲያነሱ ይደመጣሉ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለሚነሱ ቅሬታዎች የሲዳማ ክልል ሥራ፣ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ቢሮ ምክችል ኃልፊ እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ከፍያለው ከበደን ጠይቋል።
አቶ ከፍያለው ፤ " 26,000 ኢንተርፕራይዞች የከሰሙ መሆናቸውን አረጋጥጠናል። " ብለዋል።
" ከዛ ውጭ ያሉት 48 በመቶ አካባቢ የሚሆኑት ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ናቸው። ሌሎች ወደ 52 በመቶ አካባቢ የሚሆኑት የተሻለ ደረጃ ላይ ናቸው " ሲሉ ተናግረዋል።
ኢንተርፕራይዞቹ የከሰሙበት ችግር ምን እንደሆነ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄ ፦
- ድርቅ፣
- የፀጥታ ችግር
- ወደ ከተማ ያሉት ደግሞ በገበያ ማጣት፣
- በማኅበር እስከ 30 ድረስ የሚደራጁት እርስ በእርሳቸው ባለመስማማት
- ሌሎችም በግል ምክንያት
- በቂ ስልጠና እና አግኝተው ካለመግባታ ጋር የተያያዘ ነው ብለዋል።
አዲስ አበባን ጨምሮ በሌሎች አካባቢዎች የተደራጁ ኢንተርፕራይዞች በመሬት ጥበት ሥራ ለማቋረጥ እንደሚገደዱ ይገልፃሉ።
ሲዳማ ክልልም አዲስ ክልል ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ብዙ ቅሬታዎች ሲነሱ ይደመጣልና በመሬት ጥበት ምክንያት ያለው ችግር ለመቅረፍ ምን እየተሰራ እንደሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቢሮው ጥያቄ አቅቧል።
ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-12-17
@tikvahethiopia

😢94❤51👏6😡6🕊5🥰3😭1