#ኦሮሚያ
" በቤጊ ሁለት ቀበሌዎች ረሃብ ተከስቷል "
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ቤጊ ወረዳ በሁለት ቀበሌዎች ረሃብ መከሰቱ ተነገረ።
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀውና ራሱን " የኦሮሞ ሕዝብ ነጻ አውጪ " ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ሲንቀሳቀስባቸው ከነበሩ አካባቢዎች መካከል በቤጊ ወረዳ በሁለት ቀበሌዎች ረሃብ መከሰቱን የምዕራብ ወለጋ ዞን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።
የምዕራብ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሰለሞን ታምሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ " ሸኔ የያዛቸውና ለጥቂት ጊዜያት ያስተዳደራቸው ወረዳዎች ነበሩ። እነዛ ወረዳዎች ብዙ ችግሮች ገጥሟዋቸዋል " ብለዋል።
ለአብነት ታጣቂ ቡድኑ ሲንቀሳቀስባቸው በነበሩ አንዳንድ አካባቢዎች #ረሃብ መከሰቱን ገልጸዋል።
አቶ ሰለሞን ፣ " እስፔሻሊ ጠረፍ ላይ የሚገኙ ቀበሌዎች ተጎድተዋል። በምዕራብ ወለጋ ዞን ቤጊ ወረዳ ተጋባና ሻንታ ቀበሌዎች ረሃብ አለባቸው " ብለዋል።
ረሃብ ተከሰተበት የተባለውን የቤጊ ወረዳ ሁኔታን ሲያስረዱም አቶ ሰለሞን ፣ " መሰረተ ልማት፣ ቀበሌዎች፣ የአስተዳደር ጽሕፈት ቤቶች ጤና ኬላዎች፣ ጤና ጣቢያዎች ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በጣም ጉዳት የደረሰበት ወረዳ ነው " ብለዋል።
" ከጤና ጋር በተያያዘ ቢያንስ 45 የሚሆን ጤና ኬላ ወድሟል ወደ አምስት ጤና ጣቢያዎች ተቃጥለዋል " ሲሉ አስታውሰው፣ ወረዳውን ታጣቂ ቡድኑ ሲቆጣጠረው አርሶ አደሩ እንዳያርስ በማዳበሪያ እንዳይጠቀም፣ ማኅበረሰቡ የሕክምና አገልግሎት እንዳያገኝ ማድረጉን አስረድተዋል።
" ሸኔ አገሪቱን ወደ ድህነት የሚመራ እንጂ ምንም አላማ የሌለው ነው " ያሉት የዞኑ አስተዳዳሪ ታጣቂ ቡድኑ " በቄለም ወለጋና በቤጊ፣ በቆንዳላ በተለይ ገጠሩን አካባቢ ተቆጣጥሮ ጉዳት አድርሷል። ሰው ገድሏል። ብዙ ንብረቶች በዚህ ታጣቂ ቡድን ወድመዋል " በማለት ተናግረዋል።
ረሃብ የተጋረጠባቸው የሰሊጥ አምራቾች ናቸው ያሉት የዞኑ አስተዳዳሪ፣ " ሸኔ አርሶ አደሩ ማዳበሪያ በሚወስድበት ጊዜ ቀቅሎ እንዲበላ ሲያደርግ ነበር። መብላት ማለት እንደ ምግብ እንዲበላ በማድረግ እንዳያርስበት፣ እንዳይጠቀምበት ማድረግ ነው " ብለዋል።
ነዋሪዎች በበኩላቸው በተከሰተው ረሃብ የሰዎች ሕይወት ማለፉን ገልጸው፣ መንግሥት የምግብ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
አክለውም፣ በወባ ወረርሽኝም የሰው ሕይወት እያለፈ መሆኑን አስረድተዋል።
በረሃብ የሞተ ሰው እንዳለና እንዴሌለ ማብራሪያ እንዲሰጡ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ አቶ ሰለሞን ፣ " ከረሃብ የተነሳ የሞተ ሰው ሪፓርት አልደረሰኝም። ከምግብ ጋር በተያያዘ ግን የኦሮሚያ ቡሳ ጎኖፋ ሰሞኑን 400 ኩንታል ዱቄት አድርሷል። እርዳታ ግን አሁንም ያስፈልጋል " ብለዋል።
ከረሃብ ባሻገርም በዞኑ በሚጉኙ ወረዳዎች የወባ ወረርሽኝ እንደተከሰተ፣ #የሞቱ ሰዎችም እንዳሉ ገልጽው፣ መንግሥትና መንግስታዊ ያልሆኑ የተራድኦ ድርጅቶች እርብርብ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
መንግሥት " ኦነግ ሸኔ " እያለ የሚጠራውና እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሚለው ታጣቂ ቡድን ከላይ በምዕራብ ወለጋ ዞን በቀረበበት ክስ ዙሪያ ይፋዊ ምላሽ የሚሰጥ ከሆነ ተከታትለን እናሳውቃለን።
@tikvahethiopia

😢300❤75😡27🙏25🕊13🥰12😱3