ተንቢሃት Tenbihat – ኢስላማዊ ህግጋት እና ተግሳፃት
6.76K subscribers
1.38K photos
118 videos
173 files
1.38K links
ተንቢሀት - የተለያዩ ኢስላማዊ ትምህርቶች የሚቀርቡበት ቻነል nesiha.com
Download Telegram
ከዚያም ረዘም ያለ ሩኩዕ ይደረጋል። ማለትም ረዘም ላሉ ደቂቃዎች ይጎነበሳል።
ከዚያም ቀና በማለት ቀጥ ተብሎ ይቆምና እንደገና ሱረቱል ፋቲሃ ይነበባል።
ከዚያም በመጀመርያው ረከዓ ላይ ከተቀራው የቁርኣን መጠን በተወሰነ ደረጃ አነስ ባለ መጠን ይቀርራል።
ከዚያም እንደገና ለሩኩዕ ጎንበስ ይባላል።
ከዚያም ቀና ይባላል።
ከዚያም ወደ ሱጁድ ይወረድና ሁለት ግዜ በረዥሙ ሱጁድ ይደረጋል። በዚህ አይነት የመጀመርያው ረከዓ የተሟላ ይሆናል።
ከዚያም ለሁለተኛው ረከዓ በመነሳት ይቆማል። ፋቲሃ ይቀርራል። ልክ እንደ የመጀመርያው ረከዓ ሁሉም ስርዓት ይደገማል።
ከዚያም ለተሸሁድ በመቀመጥ አትተህያ ይነበባል። በመጨረሻም በሁለቱ ሰላምታዎች ሰላቱ ይጠናቀቃል።
والله أعلم وصلى الله وسلم على نبينا محمد وعلى آله وصحبه أجمعين.

≅∷≅∷≅∷≅∷≅∷≅∷≅∷≅
✍🏽Abufewzan
ዙል ቂዕዳ 15/1439
July 28/2018
ል። ምክንያቱም ወንጀሎች ለመዓት መውረድና ለቅርቡም ሆነ ለሩቁ ቅጣት መምጣት ሰበብ ናቸውና።» ብለዋል።
"فتح الباري" (2/534) .

ሸይኽ ሳሊህ አስስንዲ ሀፊዘሁላህ ስለ ግርዶሹ ባስተላለፉት መልእክት መካከል የሚቀጥለውን ብለዋል።☞
«አላህ ባሮቹን ያስፈራራበታል የሚለውን ቃል ሲያስረዱ “ማስፈራራት ማለት ማስፈራርያን የሚያስከትል ነገር ሲገኝ ይከሰታል ለማለት ነው። ይህ ደግሞ ለቅጣት ሰበብ የሚሆን ወይም ለዚያ የሚዳርግ ምልክት ሲገኝ እንጂ ማስፈራርያ አይመጣም። ግርዶሽ ደግሞ ለምድር ነዋሪዎች የቅጣት መከሰት ምልክት ሆኖ መምጣቱ ይታወቃል።” ብለዋል በማለት የኢብኑ ተይሚያን ንግግር ጠቅሰዋል። ረሂመሁላህ።

በግርዶሽ መከሰት ሊደረጉ የሚገባቸውን ነገሮች ሲገልፁ ደግሞ

«በጨረቃ ግርዶች መከሰት ሰበብ ሊደረጉ የሚገቡ የሆኑ በሱና የተጠቆሙ ጉዳዮች ወደ ሰባት ነገሮች ናቸው። እነሱም በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገቡ ሲሆኑ አንዳንዶቹ ደግሞ በአንዳቸው ብቻ የተዘገበ ነው። ዝርዝሩም
1ኛ/ الصلاة ሰላት
2ኛ/ الدعاء ዱዓእ
3ኛ/ ذكر الله አላህን ማውሳት ማወደስ
4ኛ/ الاستغفار ምህረትን መጠየቅ
5ኛ/ التكبير ተክቢር
6ኛ/ الصدقة ሰደቃ
7ኛ/ العتق ባርያን ነፃ ማውጣት ናቸው።» ብለዋል። በማስከተልም የሰው ልጅ ይህን መሰረታዊ ጉዳይ መዘንጋቱን ሲገልፁ

«የሚያሳዝነው ጉዳይ ግን ይህች በሰው ልጆች ላይ እየተመላለሰች የምትከሰተው የጨረቃ መጋረድ ታላቅ የሆነ ተዓምር ከመሆኑም ጋር የተወሰኑ ሰዎች ሙንከር ነገርን እየተጠጡም ሳሉ ምንም አይነት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ አይታዩም። ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን።

ነቢዩﷺ ግን በዘመናቸው ፀሃይ ስትጋረድ በርግገው በፍጥነት ወደ መስጂድ ሄዱ። ከድንጋጤያቸው የተነሳም ሽርጣቸውን መሬት ላይ እየጎተቱ ነበርና ለሰሃቦቹ «فافزعوا» በስጋት ሽሹ እስኪሏቸው ድረስም ስለ ልብሳቸው አላሰቡምና ከመሰብሰብ ዘግይተው ነበር።» ብለዋል።
• موعظة عن آية الخسوف للشيخ أ. د. صالح سندي.
https://youtu.be/R89dYhsPzP4

*ኩሱፍ የሚከሰትበትን ወቅት መገመት ብሎም ማወቅ ይቻላልን?*

የፀሃይ ወይም የጨረቃ ግርዶሽ ሊከሰት የሚችልበትን ወቅት ማወቅ ወይም መገመት ከሩቅ ሚስጥር ወይም ጘይብን ለማወቅ ከመጣር የሚቆጠር አይደለም። ይልቁንም እሽርክሪቶቻቸውን በማስላት መቸና የት ሊከሰት እንደሚችል መገመት ይቻላል። ይሁንና በካልኩሌሽኑ ላይ ብቻ በመመርኮዝ በግርዶሹ ሰበብ የሚሰገደው ሰላት እንዲሰገድ አይታዘዝም። ሰላቱ የሚሰገደው ግርዶሹ በግልፅ ተከስቶ በዐይን ከታየ በኋላ ነውና።

በዚሁ አጋጣሚ የሚመከረው ጉዳይ የፀሃይ ወይም የጨረቃ ግርዶሽ ባለተከሰተባቸው አካባቢ ያሉ ሙስሊሞች አጎራባች ሀገራት ላይ መከሰቱን በመስማት ብቻ ሊሰግዱ አይገባም። ነቢዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም መስገድን ያቆራኙት ግርዶሹን ከማየት ጋር ነውና በዜና ወይም በከዋክብት ተማራማሪዎች ግምታዊ ስሌት ብቻ መስገድ አይፈቀድም። ለዚህም ከልካይ የሚሆን መመርያ ኣለ።

አላህ አዝዘ ወጀልለ በቅዱስ ቃሉ በሱረቱል አህዛብ 21ኛው አንቀፅ ላይ «በአላህ መልዕክተኛ ላይ በእርግጥም መልካም የሆነ አርዓያነት አለላችሁ።» ብሏል። በአል ሀሽር ሱራ ሰባተኛው አንቀፅ ላይ ደግሞ « መልዕክተኛው የሰጣችሁን ውሰዱት። የከለከላችሁን ደግሞ ተዉት።» በማለት ለማንኛውም አምልኳዊም ሆነ ሌላ ስርዓት እሳቸው በሰጡን መመርያ ብቻ እንድንራመድ አዝዞናል። በአል ኑር ምዕራፍ 68ኛው አንቀፅ ደግሞ «እነዚያ የሱን ትዕዛዝ የሚፃረሩ ሰዎች ፈተና እንዳትገጥማቸው ወይም አሳማሚ የሆነች ቅጣት እንዳትደርስባቸው ይጠንቀቁ።» ሲል በዲን ጉዳይ ላይ ቀልድ ሆነ ፍልስፍና ቦታ እንደሌለው በዛቻ ገልፇል።

*የኩሱፍ ሰላት ሸሪዓዊ ብይን ምን ይሆን?*

በግርዶሹ ምክንያት የሚሰገደው ሰላት ሸሪዓዊ ብይኑ ጠንከር ያለ ሱና ማለትም "ሱንና ሙአከዳህ" በመባል በፉቀሃእ ዘንድ ይታወቃል። ስለዚህ ግርዶሹ በተከሰተበት አካባቢ ያሉ ሙስሊሞች ተጠራርተውና ተሰባስበው አላህን ለመለመን መስገዳቸው ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን አላህ እንዲመልስላቸው ከመማፀንም ባለፈ ከፍ ያለ ምንዳ የሚያስገኝ ተግባርም ነው።

*ሰዎች ለሰላቱ እንዴት ይሰበሰባሉ?*

ለኩሱፍ ሰላት የያከባቢውን ሙስሊም ማህበረሰብ ጠርቶ በጋራ በመስገድ አላህን መለመን ከላይ እንደተገለፀው ጠንከር ያለ ሱንና ነው። ለዚህም ራሱን የቻለ የአጠራር ስልት አለው። እሱም "አስሰላቱ ጃሚዓ" የሚል ሲሆን ሰዎች መስማታቸው እርግጠኛ እስኪኮን ድረስም ይህን ቃል መደጋገም ይቻላልና ይህን ያህል ግዜ ብቻ ነው ጥሪ የሚደረገው ተብሎ የተገደበ ነገር የለውም። ይህም ቃል በነቢዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ዘመን ተፈጥሮ በነበረው የጨረቃ ግርዶሽ ወቅት በተሰገደው ሰላት ታሪክ ላይ ተዘግቧል።

*የሚታየው ነገር በምን ደረጃ ሲሆን ነው ሰላቱ የሚሰገደው?*

ሰማይ በጉም ከተሸፈነች ግርዶሹ በዐይን እስኪታይ ድረስ ለኩሱፉ አይሰገድም። በስነ ኮከብ አጥኚዎች ዜናና ትንታኔ ላይ ብቻ በመመርኮዝም አይሰገድም። ዞሮ ዞሮ ግርዶሹ በተጨባጭ ከታየን ብቻ ነው የሚሰገደው። በሌላ በኩል "የክልከላ ግዜያት" በመባል በሚታወቁ ሰላት ከመስገድ እንድንቆጠብ በተደረጉባቸው ጊዜያትም ቢሆን የኩሱፍ ሰላት ይሰገዳል።

*የኩሱፍ ሰላት አሰጋገድ እንዴት ይሆን?*

① የኩሱፍ ሰላትን በህብረት ሆኖ መስገድ ይቻላል። ሱንናም ነው። ጀማዓ ያመለጠው ወይም ያላገኘ ሰው ግን ልክ በጀማዓ ሲኮን እንደሚሰገደው ለብቻውም ቢሆን የሱንና ሰላቶችን እንደሚሰግደው እቤቱ ሆኖ መስገድ ይችላል።

② ሰላቱን ረዘም ማድረግ የተደነገገ ጉዳይ ነውና በተለይ በጀማዓ በሚሰገድበት ግዜ
ኢማሙ ቁርኣንን በቃሉ ያልሸመደደ የሆነ እንደሆን እንኳን ቁርኣንን ከፍቶ እያነበበ ማስሰገድ ይችላል።

③ ኢማሙ ከሰላቱ በኋላ በቃሉም ሆነ ከወረቀት እያነበበ ሰዎችን ለመምከር፣ ለማስታወስ፣ የአላህን ቅጣት እንዲጠነቀቁት በማስፈራራትና ንስሃ እንዲገቡ በመገፋፋት አንድ ግዜ ኹጥባ ማድረጉ ሱና ነው።

④ ኢማሙ እያሰገደ ሳለ ዘግይቶ የመጣ ሰው አንድ ሙሉ ረከዓ አግኝቷል የሚባለው ቢያንስ የመጀመርያዋ ሩኩዕ ላይ የደረሰ እንደሆነ ነው። ይህች የመጀመርያዋ ሩኩዕ ካመለጠችው ግን አንድ ሙሉ ረከዓ እንዳመለጠው ነውና የሚቆጠረው ሩኩዖችንም ሱጁዶችንም ሙሉ በሙሉ መተካት አለበት። እንደሚታወቀው የኩሱፍ ሰላት አሰጋገድ በየ እለቱ አምስቴ ከምንሰግደው የግዴታ ሰላት ለየት ያለ ነውና በአንድ ረከዓ ላይ ሩኩዕ የሚደረገው ማለትም ጎንበስ የሚባለው ሁለቴ ነው። በዚህ ጨኳኋን ከሌሎቹ ሰላቶች ይለያል። ሱጁድ ግን ልክ ሌላው ሰላት ለያንዳንዱ ረከዓ ሁለት ሁለቴ ነው የሚደረገው።

⑤ ሴት ልጅ የኩሱፍ ሰላትን መስገድ ከፈለገች እንደ ወንዶቹ ሁሉ መስጂድ ሄዳ በጀመዓ መስገድ ትችላለች። ከፈለገች ደግሞ እቤቷ ሆና መስገድ ትችላለች።

*የአሰጋገድ ገፅታው ምን ይመስላል?*

የኩሱፍ ሰላት ሁለት ረከዓ ነው። በእያንዳንዱ ረከዓ ሁለት ግዜ ተቁሞ የፋቲሃ ምዕራፍ እና ተጨማሪ ሌላ ምዕራፍ ይቀርራል። ሁለት ግዜ ሩኩዕ ይደረጋል። ሱጁዱ ደግሞ እንደ ማንኛውም ሰላት ሁለት ግዜ ብቻ ሲሆን ተሸሁድና ሰላምታም እንደሌሎቹ ሰላቶች ይሆናል።

*አሰጋገዱን በዝርዝር ብናየውስ?*

በቅድሚያ በተክቢረቱል ኢህራም ማለትም አላሁ አክበር በማለት ወደ ሰላቱ ይገባል።
ከዚያም ሱረቱል ፋቲሃ ይቀርራል።
ከዚያም ተጨማሪ በጣም ረዘም ያለ ምዕራፍ ይነበባል።
🔖ከፀሐይ ግርዶሽ ጋር የተያያዙ ህግጋት

🗂 ክፍል 1

🎙 በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ
እና
🎙 በኡስታዝ ሙሐመድ ሐሰን ማሜ

👇 ሊንኩን ትጭነው በዩትዩብ ቻናላችን መከታተል ይችላሉ
https://youtu.be/zrjEh6n66lA
≅∷≅∷≅∷ ﷽ ∷≅∷≅∷≅

ስለ ኩሱፍ ወይም የፀሃይና የጨረቃ ግርዶሽ መረጃ እንለዋወጥ።

ኩሱፍ ወይም الكسوف ማለት የፀሃይ ግርዶሽ ማለት ሲሆን፤ ኹሱፍ ወይም الخسوف ሲባል ደግሞ የጨረቃ ግርዶሽ ለማለት ነው።

① *ኩሱፍ ወይም ኹሱፍ ለምን ይከሰታል?*

ግርዶሽ እንዲከሰት ሰበብ የሚሆኑ ተጨባጭና ሸሪዓዊ በመባል የሚገለፁ ሁለት አይነት ምክንያቶች ኣሉ።

☞ የሚታይና በቀላሉ የሚታወቀው ተጨባጭ ጉዳይ አንደኛው ገፅታ ጨረቃ ምድርን እየዞረች ባለበት በፀሃይና በምድር መሃል ስትደርስ የሚፈጠረው የመጨለም ክስተት ነው። ይህም የሚሆነው ጨረቃ በፈለኳ ላይ መስመሯን ጠብቃ ስትዞር በአንድ ጎኗ ፀሃይ በሌላኛው ጎኗ ደግሞ ምድር ሆኖ መሃከላቸው ላይ ስትገባ የፀሃይ ብርሃን ወደ ምድር እንዳይደርስ ግርዶ ስለምትሆን የፀሃይ ግርዶሽ ወይም *ኩሱፍ አልሸምስ* የተሰኘው ክስተት ይፈጠራል።

ሁለተኛው የግርዶሽ ገፅታ ደግሞ ምድር በፀሃይና በጨረቃ መሃል ስትሆን ጨረቃ ከፀሃይ ይደርሳት የነበረውን ብርሃን ታጣለች። ይህን ግዜ የጨረቃ ግርዶሽ ወይም *ኹሱፍ አልቀመር* ተከሰተ ይባላል።

☞ ሁለተኛውና ሸሪዓዊው የግርዶሹ መከሰት ምክንያት የባሮች ማለትም የሰው ልጆች በወንጀልና በኃጢኣት መዘፈቅ ነው። ለዚህም ነው የግርዶሽ ሰላት የስጋት መግለጫ ሰላት ወይም ክፉና መዓትን መከላከያ የሆነ ሰላት በመባል የታወቀው።

ሸይኽ አብዱል ዐዚዝ ኢብኑ ባዝ ረሂመሁላህ ስለዚሁ ጉዳይ እንደገለፁት «የፀሀይ ግርዶሽና የጨረቃ ግርዶሽ አላህ ባሮቹን ለማስፈራራት እንዲከሰቱ የሚያደርገው ክስተት ነው ሲሉ ነቢዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም መናገራቸው ተረጋግጧል።» ብለዋል።
መጅሙዕ ፈታዋ ሊብንባዝ 30/289

በዚሁ ገፅ ላይ ትንሽ ወረድ ብሎ የሰፈረው የኢብኑ ባዝ ንግግር ደግሞ የግርዶሹን ምክንያት የሰው ልጅ ኃጢኣት በመብዛቱ ለማስፈራርያነት የሚከሰት ከመሆኑና በተፈጥሯዊው የጨረቃ ወይም የምድር እሽክርክሪት ሰበብ የሚፈጠር ከመሆኑ ጋር የሚጋጭ ኣለመሆኑን ሲያስረዱ እንዲህ ይላሉ☞

«የግርዶሿ በባለሞያዎች ስሌት መታወቅ ለማስፈራርያነት ሲል ሀያሉ አላህ እንዲከሰቱ ከማድረጉ ጋር የሚጋጭ አይደለም። ክስተቱ ከእንከን አልባው ሀያሉ አላህ ለማስጠንቀቂያነት የተደረገ ነውና። ተዓምራቱን የሚያስኬዳቸውም እሱ ራሱ ነው። በተወሰኑ ግዜያት ፀሃይ እንደምትወጣውና እንደምትጠልቀው ሁሉ የግርዶሹን መገኛ ሰበብ ያስገኘው እሱ ነው። ጨረቃም፣ ከዋክብትም ልክ እንደዚያው ሁሉም ከአላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ተዓምራት የሆኑ ናቸው።

የስነ ከዋክብት አጥኚዎች የገለፁት የግርዶሹ ሰበብም አላህ ያደረገው ሰበብ ነው። የግርዶሹን መከሰት የሚያውቁትም በዚሁ ነው። ሆነም ቀረ ለማስፈራሪያና ለማስጠንቀቂያነት ከአላህ ዘንድ የተደረገ መሆኑን የሚያግድ አይደለም።

ልክ እንደዚሁ በፀሃይ፣ በጨረቃና በከዋክብት እንዲሁም በሙቀትና በብርድ ላይ የሚታዩ ልዩ ተዓምራቱ ኣሉ። ታዲያ በነዚህ ተዓምራት ሁሉ ውስጥ ይህንን ፀጋውን በአግባቡ ባለመቀበል አላህን ላመፀ አካል ማስፈራርያና ማስጠንቀቅያ አለበት። በዚህም ትዕዛዛቱን በመፈፀም ላይ ፅኑ እስኪሆኑና ሀራም ያደረገባቸውን ነገር እስኪተዉ ድረስ በነዚህ ክስተቶች ሰበብ እንዲጠነቀቁት፣ እንዲፈሩትና እንዲሰጉት እንከን አልባው ጌታችን ይህን ነገር ያደርጋል።» ብለዋል።
መጅሙዑ ፈታዋ ሊብንባዝ 30/289

ሸይኽ ሷሊህ አልዑሰይሚን ረሂመሁላህ በገለፁት ደግሞ ቀጣዩን መልእክት እናገኛለን☞

«ግርዶሽ የሚከሰተው ለማስጠንቀቅያ ሲሆን የሆነ የሚያስቀጣ ነገር በመገኘቱ የሚመጣ እንጂ በራሱ ቅጣት ሆኖ አይደለም የሚከሰተው። ነገር ግን ማስጠንቀቅያ ነው። ይህም ልክ የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም
( يخوف الله بهما عباده )
“በሁለቱም ባሮቹን ያስፈራራበታል።” ብለው እንደተናገሩት ነው። ስለዚህ ማስፈራርያ ነው ያሉት እንጂ ባሮቹን ይቀጣበታል አላሉም። ይሁንና ከማስፈራርያው በሰረተጀርባ የሚከተለውን አናውቅም።

ምናልባትም በህይወት ላይ ወይም በንብረት ወይም በልጆች ወይም በቤተሰብ ላይ ያነጣጠረች ዘግይታ የምትመጣ ወይም ወዲያው የምትከሰት ቅጣት ልትኖር ትችላለችና። ቅጣቱ ሁሉን አቀፍ ወይም በተወሰኑት ላይ ያነጣጠረም ሊሆን ይችላል። ግን አናውቀውም።

ለዚህም ነቢዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም “ያንን ግርዶሽ ስታዩ አላህን ወደ ማውሳት በርግጉ፣ በስጋት ሽሹ።” ነበር ያሉት። ተነሱ ቁሙ አላሉም። ስገዱም ዚክር አድርጉ ብቻም አላሉም። ነገር ግን እሳቸው ያሉት በስጋት ሽሹ ነው። አላህን ወደ ማውሳት በርግጉ። ምህረትን ጠይቁት፣ ሃያልነቱን ግለፁ፣ ሰደቃ ስጡ፣ ስገዱ፣ ባርያም ነፃ አውጡ ነው ያሉት። ታዲያ ይህ ሁሉ የሚጠቁመን የዚህ ግርዶሽ ጉዳይን ክብደት ነው። ለግርዶሽ መከሰት ደግሞ ሁለት ምክንያቶች ይኖሩታል።

አንደኛው ማስፈራርያ ነው። ይህም ኃጢኣት ሲበዛና ወንጀሎች በልቦች ላይ ሲጋገሩ አላህ ባሮቹን ያስፈራራበታል። አላህ ከእንደዚህ አይነቱ በሽታ ጠብቆ ኣፊያ ይስጠን እላለሁ።

ሁለተኛው የግርዶሽ መከሰት ሰበብ ደግሞ በዓለማችን ላይ እንዲከሰት አላህ የወሰነው ተፈጥሯዊ ክስተት ነው። እሱም ሰዎች እንደሚያወሩት ሁሉ የፀሃይ ግርዶሽ ሰበቡ የጨረቃ በፀሃይና በምድር መሃል መገኘት ነው።

የጨረቃ ግርዶሽ ሰበብ ደግሞ የምድር በፀሃይና በጨረቃ መሃል መገኘት ነው። በዚህም መሰረት አላህ አዝዘ ወጀልለ ባሮቹን ለማስፈራራት ሲል ተፈጥሯዊ የሆኑ ሰበቦች እንዲከሰቱ ከማድረግ ከልካይ ነገር እንደሌለበት ነው።» በማለት አብራርተዋል። [ሊቃኡል ባብ አልመፍቱህ ቅፅ 15 ገፅ 4–5]

② *መስገዱ ለምን አስፈለገ?*

ጌታችን አላህ የፀሃይ ወይም የጨረቃ ግርዶሽ እንዲፈጠር በማድረግ ባሮቹን ያስፈራራበታል። በዚህም ሊወርድባቸው የሚችል ቅጣትና መዓት እንዳለ በመጠቆም ለዚያ ጥበበኛና ሃያል ፈጣሪያቸው ሰግደው በመፀለይ፣ ከኃጢኣታቸው በመመለስ ይቅርታንና ምህረትን በመጠየቅ፣ የሱን ሃያልነትና ታላቅነት በተክቢር በመግለፅና ለሱ ሲሉ ሰደቃ በመስጠት ሲለማመኑት ሊከሰት ከሚችለው አደጋ ይጠብቃቸዋል።

ነቢዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ስለ ክስተቱ ሲገልፁ
( هَذِهِ الْآيَاتُ الَّتِي يُرْسِلُ اللَّهُ لَا تَكُونُ لِمَوْتِ أَحَدٍ وَلَا لِحَيَاتِهِ وَلَكِنْ يُخَوِّفُ اللَّهُ بِهِ عِبَادَهُ ؛ فَإِذَا رَأَيْتُمْ شَيْئًا مِنْ ذَلِكَ فَافْزَعُوا إِلَى ذِكْرِهِ وَدُعَائِهِ وَاسْتِغْفَارِهِ ).
«ይህች ተዓምር ማንም ስለሞተ ወይም በህይወት ስለተገኘ አላህ የሚልካት አይደለችም። ነገር ግን አላህ ባሮቹን የሚያስፈራራበት ክስተት ነውና ከዚህ ጉዳይ የሆነ ነገር ካያችሁ አላህን ወደ ማውሳት፣ ወደ መለመንና ምህረቱን ወደ መጠየቅ በፍራቻ ሽሹ።» ብለዋል።
ቡኻሪና ሙስሊም

ኢብኑ ሀጀር ረሂመሁላህ ወደዚያ ደንብሩ የሚለውን ቃል ሲተነትኑ «ፈፍዘዑ (فَأَفْزَعُوا) ማለት ወደሱ ተመለሱ፣ ተቅጣጩ ለማለት ነው። በዚህ አገላለፅ ውስጥ ወደ ታዘዙት ነገሮች መሽቀዳደምን የሚጠቁም መልዕክት ኣለ። አስጊ ነገር ሲገጥም ወደ አላህ የሚሸሸው ደግሞ ድንበር ጥሰው የፈፀሙት ወንጀል እንዲሰረይ ሰበቡን ለማድረስ እሱን በመለመንና ምህረቱን በመጠየቅ ነው።

ቀሪዉን ያንብቡ👇
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=2985666274864229&id=402250953205787
የኩሱፍ አሰጋገድ ምን ይመስላል?

የኩሱፍ ሰላት ሁለት ረከዓ ነው። በእያንዳንዱ ረከዓ ሁለት ግዜ ተቁሞ የፋቲሃ ምዕራፍ እና ተጨማሪ ሌላ ምዕራፍ ይቀርራል። ሁለት ግዜ ሩኩዕ ይደረጋል። ሱጁዱ ደግሞ እንደ ማንኛውም ሰላት ሁለት ግዜ ብቻ ሲሆን ተሸሁድና ሰላምታም እንደሌሎቹ ሰላቶች ይሆናል።

በቅድሚያ በተክቢረቱል ኢህራም ማለትም አላሁ አክበር በማለት ወደ ሰላቱ ይገባል።
ከዚያም ሱረቱል ፋቲሃ ይቀርራል።
ከዚያም ተጨማሪ በጣም ረዘም ያለ ምዕራፍ ይነበባል።
ከዚያም ረዘም ያለ ሩኩዕ ይደረጋል። ማለትም ረዘም ላሉ ደቂቃዎች ይጎነበሳል።
ከዚያም ቀና በማለት ቀጥ ተብሎ ይቆምና እንደገና ሱረቱል ፋቲሃ ይነበባል።
ከዚያም በመጀመርያው ረከዓ ላይ ከተቀራው የቁርኣን መጠን በተወሰነ ደረጃ አነስ ባለ መጠን ይቀርራል።
ከዚያም እንደገና ለሩኩዕ ጎንበስ ይባላል።
ከዚያም ቀና ይባላል።
ከዚያም ወደ ሱጁድ ይወረድና ሁለት ግዜ በረዥሙ ሱጁድ ይደረጋል። በዚህ አይነት የመጀመርያው ረከዓ የተሟላ ይሆናል።
ከዚያም ለሁለተኛው ረከዓ በመነሳት ይቆማል። ፋቲሃ ይቀርራል። ልክ እንደ የመጀመርያው ረከዓ ሁሉም ስርዓት ይደገማል።
ከዚያም ለተሸሁድ በመቀመጥ አትተህያ ይነበባል። በመጨረሻም በሁለቱ ሰላምታዎች ሰላቱ ይጠናቀቃል።

@tenbihat
አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ

ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ባዘጋጀው
#የደርስ_መርሀግብር
ለተሳተፋችሁ ሁሉ እናመሰግናለን።
የሸዋል ወር በ29 መጠናቀቁን ከግንዛቤ በማስገባት እስከ ዛሬ ሰኞ 15/2012 ምሽት ብቻ ተሳትፎ የምንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን።

ውጤቱን በቀጣዩ ወር በመርከዙ የቴሌግራም ቻነል ላይ እንድትጠብቁ በአክብሮት እንጠይቃለን።

ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር
T.me/merkezuna
Aselamu alikum,
Alhamdulilah I'm excited to announce that Nesiha Da'wah Atlanta now has an app on Android Google play (Nesiha Atlanta) so that all the class that sheikh Hussain Isaa gives will be accessible inshallah at a tip of your finger at one place at any time. In this app you will be able to play, share, comment and get notified when the class is live. So I kindly ask everyone to download, comment and share to all your friends and family.
Barakllah fikum.

https://play.google.com/store/apps/details?id=com.spreaker.custom.prod.app_59885

As for iOS(iPhone) it be available soon inshallah.
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📺 እሁድን በነሲሓ ቲቪ

🗂 የእለተ እሁድ ፕሮግራሞች በነሲሓ ቲቪ

📌ነሲሓ ቋንቋ

🔖ኦሮምኛ ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ
🔖ስልጥኛ ከጠዋቱ 4፡15 ጀምሮ
🔖ጉራግኛ ቀን ከ5፡30 ጀምሮ
🔖ትግርኛ ቀን ከ6፡45 ጀምሮ

📌ነሲሓ ለወጣቶች

🔖ሀኢያህ ሊብኒ አቢዳዉድ
🔖የሰለፎች መንገድ
🔖ምክር ለወጣቶች
🔖የተውሒድ ውበት

📌ኢስላምና ሙስሊሞች
⌚️ከ10፡00 ጀምሮ

📌የዐርብኛ ትምህርት

🔖የዐረብኛ ሰዋሰው በቀላሉ
⌚️ከ11፡00 ጀምሮ

📌ከሐዲስ ማህደር

🔖ኡምደቱል አህካም
⌚️ከ11፡45 ጀምሮ

📌ተፍሲር

🔖ቁርኣን ተፍሲር
⌚️ከምሽቱ 12፡30 ጀምሮ

📺ነሲሓ ቲቪ ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም
🗂 እለታዊ ፕሮግራሞች በነሲሓ ቲቪ
ሰኞ ሰኔ 22/2012

📌 ነሲሓ ቁርኣን ቤት

🔖 ቃዒደቱ ኑራኒያህ
🔖 ቁርኣን ሐለቃ

⌚️ ዛሬ ቀን ከ10፡00 ጀምሮ

🔁 በድጋሚ
⌚️ ነገ ጠዋት ከ4፡00 ጀምሮ

📌 የነብያት ውርስ

🔖 ኪታቡ ተውሒድ
🔖 መንዙመቱል ፊቅህያ
🔖 ኪታቡ ሰላት

⌚️ ዛሬ ከ11:30 ጀምሮ

🔁 በድጋሚ
⌚️ ነገ ቀን ከ5:30 ጀምሮ

📌 ነሲሓ መሠረታዊ

🔖 የዓቂዳ ትምህርት
🔖 የሰላት ህግጋት

⌚️ ዛሬ ምሽት ከ1፡30 ጀምሮ

🔁 በድጋሚ
⌚️ ነገ ቀን ከ7:30 ጀምሮ

📌 ነሲሓ ለእህቶች

🔖 የተፈጥሮ ደም እና ሸሪዓዊ ህግጋቶቹ
🔖 ተንቢሃት

⌚️ ዛሬ ምሽት ከ2፡45 ጀምሮ

🔁 በድጋሚ
⌚️ ነገ ቀን ከ8:45 ጀምሮ

📺 ነሲሓ ቲቪ ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም
የመረጋጋት እና የማረጋጋት ኃላፊነት

ሰላም እና መረጋጋት ለዲንና ለዳዕዋ የሚያበረክተው አስተዋፅኦ እጅግ በጣም ከፍ ያለ ነው። ነገር ግን ይህንን ብዙዎች ባለመገንዘብ ምናልባት ሰላምን የሚያደፈርሱ ክስተቶች ላይ በቀጥታ ባይሳተፉ ራሱ በተዘዋዋሪ የሚሳተፉባቸው አጋጣሚዎች አሉ።
ቀጥታ ተሳትፈው ሰዎችን የሚገድሉ ወይ ንብረትን የሚያወድሙትን - እንዲያው ስለነሱ ብዙ ማለት የሚያስፈልግ አይመስለኝም። ሆኖም ግን ከኋላ ሆኖ በንግግር እና በመሰል ድጋፎች ሰዎች እርስ በርስ እንዲባሉ፣ ሰላም እንዲጠፋ፣ ሁከት እንዲጎለብት አስተዋፅኦ የሚያደርግ ሊኖር ይችላል።
ንግግራችን የሚያመጣውን ተፅእኖ ሳናስብ እንዲሁ ያለገደብ ድጋፍን ወይም ተቃውሞን እንሰነዝራለን። ይህ ደግሞ ከተጠያቂነት አያድነንም። ሀላፊነት የጎደላቸውን ቃላት እንዲሁ መሰንዘር ማብቃት ይጠበቅበታል። አንዳንድ ግዜኮ የትላልቅ እልቂቶች መነሻ ንግግር ሊሆን ይችላል። ጦር ያልፈታውን ወሬ ይፈታዋል ነው ነገሩ። ችግሮች በተፈጠሩ ቁጥር ገና ሳይባባሱ የማረጋጋት ስራ መስራት የሁሉም ሀላፊነት ሊሆን ይገባዋል። ትንሽ እሳት ደግሞ ቶሎ አስፈላጊውን እርምጃ ካልተወሰደ አገር ልታጠፋ ትችላለች።

ለሁከትና ለአላስፈላጊ እልቂት የሚያበቁ ክስተቶችን ባጠቃላይ ገና ሳያድጉ በፊት ቶሎ የማርገብና የማረጋጋት ስራን መስራት ልማዳችን ሊሆን ይገባል።
አዎ! ብዙዎች ባለመገንዘብ ምናልባት ሰላምን የሚያደፈርሱ ክስተቶች ላይ በቀጥታ ባይሳተፉ ራሱ በተዘዋዋሪ የሚሳተፉባቸው አጋጣሚዎች አሉ

ኢልያስ አህመድ (የሰላም ዋጋ)

t.me/tenbihat
ወርቃማ የዙል-ሒጃ 10 ቀናትና
መልካም ስራ ላይ መበርታት

بسم الله الرحمن الرحيم فضل عشر ذي الحجة ووصايا لمن أدركها

ምስጋናና ውዳሴ ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ ይሁን ሰላትና ሰላም የሰው ልጆች ሁሉ ምርጥ በሆኑት በነቢዩ ሙሐመድ ላይ ይስፈን አላህ በእዝነቱ ለባሮቹ የተለያዩ ወደርሱ የሚያቃርቡ ልዩ የመልካም ስራ እድሎችን ፈጥሯል በዚህም ተፎካካሪዎች እንዲፎካከሩ፣ ተሽቀዳዳሚዎችም እንዲሽቀዳደሙ ገፋፍቷል የስው ልጅ ነፍስ ሁሌ አንድ አይነት ሁኔታ ላይ ስትሆን ትሰለቻለች አዲስ ነገር ስታገኝም ትነቃቃለች ይህንም ባህሪይ ሽሪዓችን ለነፍሲያ በሚገባ ጠብቆላታል ነቢያችን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሐዲሳቸው የሚከተለውን ብለዋል

" ነፍስ፥ አንዳንዴ ለመልካም ስራ ትነቃቃለች አንዳንዴም ትሰለቻለች ንቃትና ከፍተኛ ፍላጎት ባላት ጊዜ ኸይርን ስራ በሚገባ አሰሯት በታከተችና በሰለቸች ጊዜ ግዴታ ለሆኑ ነገሮች እንጂ አትጫኗት" ብለዋል

ይህ በጌታው በሚገባ የሚያምንና ስሜቱንም የማይከተልን ሰው ነፍስ ለማለት እንጂ በመሰረቱ ስሜቱን የሚከተልና የጌታውን ህግ የሚጥስን ሰው ነፍስ አይመለከትም!

መንፈስን ለማደስና ነፍስንም መልካም ነገር ላይ ለማነቃቃት አላህ በየጊዜው በመጠነኛ ልፋትና ጥረት ከፍተኛ ምንዳ የሚያስገኙ እድሎችን አስገኝቷል ይህንንም እድል ፈጥነን እንድንጠቀም ትሩፋቱን ገልጿል

ከነዚህም እድሎች መካከል አንዱ የዙል_ሒጃ የመጀመሪያ 10 ቀናቶች ናቸው ቡኻሪይና ሌሎችም ባስተላለፉት ሐዲስ ነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም የሚከተለውን ብለዋል

[ما من أيام العمل الصالح فيها أحب إلى الله من هذه الأيام يعني أيام العشر .... الحديث]

"ከዙል ሒጃ 10 ቀናት የበለጠ መልካም ስራ ከመቼውም በላይ አሏህ ዘንድ ውድ የሚሆንበት ቀን የለም"

እነሆ አዱኒያ አጭር ናት እድሜያችንም አጭር ነው ከአጭሯ ዱኒያ የቀረውም በጣም አጭር ከአጭሯ ዱኒያ የአንተ ድርሻ ደግሞ እጅግ በጣም አጭር ነው ይህም እውነታ ቀደም ሲል በቁርኣን ተነግኖራል

[قُل متاعُ الحياةِ الدنيا قَليل والآخِرةُ خَيرٌ لِمَن اتَقى....] النساء 77

" ነቢዩ ሙሐመድ ሆይ ንገራቸው፥ የዱኒያ ህይወትና መጠቃቀሚያዋ አጭርና ጥቂት ነው የአኼራ ህይወትም (አሏህን ለሚፈሩ) ከዱኒያ የተሻለ ነው" "ሱረቱንኒሳእ 77"

አጭርና ጥቂት ከሆነችዋ የዱኒያ ህይወት የቀረው ጥቂቱ መሆኑንም ሲነግረንም አሏህ እንዲህ ብሏል

(اقتَرَبَت الساعةُ وانشَقَّ القَمَر)

" ቂያማ ተቃረበች ጨረቃም ለሁለት ተከፈለች “ ሱረቱልቀመር 1

(اقتَرَبَ للنَّاسِ حِسابُهم)

“ የሰው ልጆች መተሳሰቢያና መመርመሪያ ጊዜያቸው ተቃረበ እነሱ ግን ቸልታና መዘናጋት ላይ ናቸው
” ሱረቱል አንቢያ 1

አጭሩ እድሜያችን መች እንደሚቋጭ አናውቅምና ሁሌም ራስን ለሞት ማዘጋጀት ብልህነት ነው

ለሞት መዘጋጃትም፥ መልካምን ስራ ተሽቀዳድሞ በመስራት ከወንጀል በመራቅ አኼራን በመናፈቅ ነው

ጊዜያችንን በአግባቡ እንጠቀም የውርደትም ይሁን የስኬት ሰበቡ የጊዜ አጠቃቀም ነው

በዱኒያም በአኼራ በማይጠቅም ነገር ጊዜና ገንዘባችንን የምናባክን ሰዎች

ቀጣይ ምርጥ 10 የዙልሒጃ ቀናትን በአግባቡና ወደ አላህ በሚያቃርብ ስራ ለማሳለፍ ከወዲሁ ነፍሲያችሁን አሸንፉ

ሌት-ተቀን በኔት ጊዜ፣ ገንዘብና አይናችሁን የምታቃጥሉ፥ አሏህን ፍሩ እራሳችሁንም ፈትሹ ከማይጠቅም ወሬና ተግባርም ራቁ መለከል_መውት ከመምጣቱ በፊትም ከእንቅልፋችሁ ንቁ! የአኼራው ድልድይ/ ሲራጥ ላይ እንዳትወድቁ አላህ ከሚጠላው ስራ በሙሉ በመራቅ ቁርኣን ቅሩ ዘክሩ የኔትና የወሬን ፍቅር በአላህ ውዴታ ቀይሩ!

ውድ የአሏህ ባሮች =

አላህ ዘንድ ውድ የሆኑ 10 ቀናትን፥

አምስት ወቅት ሰላቶችን በወቅታቸው፣ ከፊትና ከኋላ የሚሰገዱ ሱናችን ከመጠበቅ ጋር፣ ወንዶች በጀማዓ በመስገድ፣

ቁርኣን በመቅራት፣ ዚር፣ ዱዓ እንዲሁም ተክቢራ በማብዛት፣

የተቸገሩ ሰዎችን በመርዳትና የታመሙን በመጠየቅ፣

ከዙልሂጃ 1 ጀምሮ እስከ 9ኛው ቀን በመጾምና የጾሙ ሰዎችንም በማስፈጠር ወዘተ አሏህ የሚወዳቸው መልካም ስራዎችን በመስራት እናሳልፋቸው

ከላይ እንደተጠቀሰው የሰው ልጅ እድሜ በጣም አጭር ነው አሏህ ኸይርን የሻለት ሰው ግን በአጭር ጊዜ ብዙ ቁም ነገር መስራት ይችላል::

በነዚህ ውድ ቀናት ለአኼራችን ስንቅ እንሸምት በጣም ድንቅና የተከበሩ ቀናት ናቸው አሏህ በተከበረው ቁርኣኑ በነዚህ ቀናት ምሏል አሏህ ትልቅ ነው በትልቅና ጠቃሚ ነገር እንጂ አይምልም! ነቢያችንም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በነዚህ ቀናት መልካም ስራ ላይ እንደንበረታ ገፋፍተውናል

እራሳቸውም ቀናቱን በመልካም ስራዎች ያሳልፏቸው እንደነበረ ተዘግቧል

እነሆ ኢማሙ አሕመድና ሌሎችም ዘግበውት አልባኒይ ሰሒህ ባሉት ሐዲስ የምእምናን እናት ሐፍሳ ረዲየላሁ ዐንሃ እንዲህ ብለዋል "ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የዓሹራ፣ የዙልሒጃ 10 ቀናትና በየወሩ 3ቀን መጾምን አይተውም ነበር" ብላለች

እዚህ ላይ ልብ መባል ያለበት ነጥብ ቢኖር እናታችን ዓኢሻ ረዲየላሁ ዐንሃ " ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የዙልሒጃ10 ቀናትን ጾመው አያውቁም" ብላ የተናገረችበት አጋጣሚ አለ ይህ ማለት እሷ እስከ ምታውቀው ድረስ ለማለት ነው ምክንያቱም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘጠኝ ሚስቶች ነበር ያሏቸው እሷ ቤት በሚያድሩበት እለት ጾመው አለማየቷን ነው የሚያሳየው እንጂ በጭራሽ አይጾሙም ነበረ ማለት አይደለም

ኡመታቸውን ወደ መልካም ነገር አመላክተው እራሳቸው ወደ ኋላ አይቀሩም!

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኡሱል ትምህርት ዘርፍ ዑለሞች እንደጠቀሱት አንድን ጉዳይ በተመለከተ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አድርገዉታል ወይስ አላደረጉትም የሚል ውዝግብ ከተነሳ ማድረጋቸው የተጠቀሰው በትክክለኛ ሰነድ መሆኑ ከተረጋገጠ ቅድሚያ የሚሰጠውና ተቀባይነት የሚያገኘው እሱ ነው ምክንያቱም አላደረጉም ያለው አካል የማያውቀውን ነገር እርሱ በማወቁ ጉዳዩ ላይ ይበልጥ አዋቂው ቅድሚያ ይሰጠዋል:: በመሆኑም ከነቢዩ ባለቤቶች መሀል አንደኛዋ ጾመዋል ስትል ሌላኛዋ ደግሞ አልጾሙም ካለች ተቀባይነትና ቅድሚያ የሚያገኘው ጾመዋል ያለችዋ ሃሳብ ይሆናል ማለት ነው

ሰሓቦችና ተከታዮቻቸው እንዲሁም ፈለጋቸውን ይከተሉ የነበሩ ደጋግ ቀደምቶች ትልቁ ጭንቃቸውና የህይወት ዓላማቸው "ዒባዳ" ወይም መልካም ስራ ላይ መሽቀዳደም ነበር ለዚህም ነው ከነሱ መካከል አንዱ እንዲህ ያሉት

" በዱኒያ ጉዳይ አንድ ሰው ሊቀድምህ ቢፈልግ መንገዱን አስፋለት በአኼራ ጉዳይ ግን ማንም እንዳይቀድምህ! "

አሁን አሁን እየዘነጋን ኖሮ እንጂ አላህም በተከበረው ቃሉ እንዲህ ሲል መክሮን ነበር

(سابقوا إلى مغفرة من ربكم وجنة)

" ተሽቀዳደሙ……..ወደ ጌታህቹ ምህረትና ወደ ጀነት" ሱረቱልሀዲድ 21 አላህ መልካሙን ሁሉ ካገራላቸው እርሱ ከሚጠላው ነገር በሙሉ ከጠበቃቸው ባሮቹ ያድርገን!

ኡስታዝ አሕመድ ኣደም

ذو القعدة
@ዛዱልመዓድ
https://tttttt.me/ahmedadem
ነገ ማክሰኞ (ሐምሌ 14/2012) የዙልቀዕዳ ማሟያ (30) ሲሆን፣
ዙልሒጃ የሚጀምረው ከነገ ወዲያ እሮብ (ሐምሌ 15) ነው።
የተከበሩ የዙል-ሒጃ 10 ቀናትን አላህ በሚወደው ስራ ለማሳለፍ ይወፍቀን
!

@ዛዱል-መዓድ
አንድ ሰው ኡድሕያ ሲያርድ የሚለው ዚክር አለን?
ሸይኽ ኡሰይሚን ረሂመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦
"ቢስሚላህ፣አላሁ አክበር አላሁመ ሀዛ ሚንክ ወለከ አላሁመ ሀዚሂ ዐኒ ወዐን አህል በይቲ"
【"አልፈታዋ"(25–55)】
ከዓረፋ ቀን ትሩፋቶች
≅∷≅∷≅∷≅∷≅∷≅∷
✍🏽Abufewzan A/siira

በዚህች ዓለም ካሉት ቀናት መካከል ብልጫ ያላቸው አስርቱ የዙል ሒጃ ቀናት ናቸው። ከነዚያ ቀናት መካከል ዘጠነኛው እለት የዓረፋ ቀን ነው። በሌላ ግዜ ከሚተገበሩ መልካም ስራዎች በዚህ እለት የሚተገበረው በከፍተኛ ደረጃ የአጅር ብልጫ ኣለው። አላህ ዘንድም እጅግ ተወዳጁ እለት ነው። መልካም ስራውም እንደዚያው በተለየ መልኩ ተወዳጅ ነው። ለሁሉም በሐዲሶች ተረጋግጠዋልና እንጎብኛቸው።
‏•••══ ༻✿༺══ •••

የአረፋ እለት አላህ ዲናችንን ያሟላበትና ፀጋውንም የተሟላ ያደረገበት እለት ነው

ባንድ ወቅት አንድ ይሁዲ ለአሚረል ሙእሚኒን ዑመር ኢብነል ኸጣብ ረዲየላሁ አንሁ “በኪታባችሁ የተጠቀሰችና የምታነቧት አንዲት አንቀፅ በኛ በይሁዳውያን ላይ ቢሆን ኖሮ የወረደችው ያንን እለት በዓል አድርገን እናከብረው ነበር።” በማለት ምን ያህል የምታስቀና እለት እንደሆነች መደበቅ ሳይችል ገልፆ ነበር።

ያቺ እለት አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ
﴿اليَومَ أَكمَلتُ لَكُم دينَكُم وَأَتمَمتُ عَلَيكُم نِعمَتي وَرَضيتُ لَكُمُ الإِسلامَ دينًا﴾
«ዛሬ ሃይማኖታችሁን ሞላሁላችሁ። ፀጋዬንም በናንተ ላይ የተሟላ አደረግኩኝ። ኢስላምንም በሃይማኖትነት ወደድኩላችሁ።» በማለት የገለፀበት እለት ናት።

ዑመር የይሁዲውን ምኞት እንደሰሙ ያልካት አንቀፅ መች እንደወረደች እንዲሁም የት እንደወረደች አውቃታለሁ። ነቢዩ ﷺ ጁምዓ እለት በአረፋ ቆመው ባሉበት ነው የተወረደችው።» በማለት ገልፀዋል። [ቡኻሪና ሙስሊም እንደዘገቡት]

የአረፋ እለትን ሃያሉ አላህ ክብደት ስለሰጠው በእለቱ መሀላ ፈፀመ

አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ በፍጡራኑ በፈለገው የመማል መብት አለውና በጁምዓ ቀንና በዓረፋ ቀን «ወሻሂዲን ወመሽሁድ وشاهدٍ ومشهود» በማለት ምሏል። ይህ የሚያሳየን የነዚህን ቀናት ልቅና ነው።

ይህንኑ ነቢዩﷺ ሲያስረዱ «አላህ “اليوم الموعود” በማለት የገለፀው የቂያማ እለት ለማለት ነው። “ومشهود ወመሽሁድ” በማለት የገለፀው ደግሞ የአረፋ እለትን ነው። “وشاهدወሻሂዲን” ያለው የጁምዓ እለትን ነው።» በማለት አስረድተዋል። ሀዲሱን ሸይኽ አልአልባኒይ ሀሰን ነው ብለውታል።

③ የዓረፋ እለት ፆም የሁለት አመታት ኃጢኣትን ያብሳል

ነቢዩﷺ ስለ የዓረፋ እለት ፆም ተጠይቀው ሲመልሱ «ያለፈውን ዓመት እና የመጪውን ዓመት ኃጢኣት ያብሳል።» ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። ስለዚህ በአንድ ቀን ፆም ሸክማችንን የምናራግፍበት እድል አዛኙ ጌታችን ሰጥቶናልና ከወዲሁ እንወስን። ሀዲሱን [ኢማም ሙስሊም ዘግበውታል።]

④የዓረፋ ቀን በዓረፋ ምድር ቆመው ላሉት ሑጃጆች የበዓላቸው ቀን ነው

አልአልባኒይ ሰሂህ ባሉት ሐዲስ የአላህ መልእክተኛﷺ «የዓረፋ እለት፣ የእርዱ ቀን እንዲሁም ሚና የሚቆይበት ቀናት በሙሉ ለኛ ለሙስሊሞች የበዓላችን ቀን ነው።» ብለዋል።

የእርዱ ቀን ማለት ዋነኛው የዒድ ቀን ሲሆን የእርዱ ቀን የተባለው ለኡድሂያ የምናርድበት ቀን ስለሆነ ነው። በዚሁ አጋጣሚ ልናውቅ የሚገባው የአድሃ በዓል ቀናት አምስት ተከታታይ ቀናት ናቸው። እነሱም ነገ ሰኞ ዘጠነኛው ዙል ሒጃ በዓረፋ ሜዳ ለተሰበሰቡት ሲሆን ሐጅ ላይ ለሌሉት ደግሞ በነጋታው ከአስረኛው ዙልሒጃ ይጀምርና 11ኛው 12ኛውና 13ኛው ዙልሒጃን ያጠቃልላል።

በመጀመርያው የዒዱ እለት በተለያዩ ምክንያቶች ለኡድሂያ ማረድ ያልቻለ ሰው በነዚህ ቀናት ማረድ ይችላል። የመጨረሻዋ ቀን ግን ከአስር ወቅት ማለፍ የለበትም። በተጨማሪም እነዚህ ቀናት የበዓል ቀናቶቻችን ናቸውና ከመፆም ልንታቀብ ይገባል። በደስታ፣ በዚያራና እንግዶችን፣ ጎረቤትን፣ ዘመድ አዝማድን በማስተናገድ በልተን አብልተን ተጨዋውተን ልናሳልፈው ይገባል። ይኸም ከምስጋና ይቆጠራልና።

⑤ ከምናደርጋቸው ዱዓኦች ሁሉ የዓረፋ ቀን ዱዓእ እጅግ የላቀ ነው

የአላህ መልእክተኛﷺ ስለዚህ ቀን የዱዓእ ትሩፋት ሲገልፁ «ምርጥ ዱዓእ ማለት የዓረፋ እለት የሚደረግ ዱዓእ ነው። እኔም ሆንኩ ከኔ በስተፊት የነበሩት ነቢያት ከተናገሩት ቃል መካከል በላጩም “ከአላህ በስተቀር በሀቅ ሊመለክ የሚገባው አምላክ የለም። እሱ ብቸኛ ነው። አጋር የለውም። ንግስናም ለሱ ነው። ምስጋናም የሚገባው ለሱ ነው። እሱ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነውና።” የሚለው ቃል ነው።» ብለዋል። [አልአልባኒ ሀሰን ብለውታል።]

ኢብኑ ዐብዱል በር እንደገለፁት «በዚህ ቃል መሰረት የዓረፋ እለት ዱዓእ ሁሉም ተቀባይነት እንደሚያገኝ ባብዛኛው ይታመናል።» በማለት የዱዓእን ደንብ ጠብቀን አላህን ከልብ እንለምነው እንጂ ጠብ አይልብንም የሚል መልእክት አስተላልፈዋል።

አላህ በዓረፋ ምድር በቆሙለት ባሮቹ በሰማይ ያሉት መላዕክቱ ላይ ይፎክራል

ይህንኑ ነቢዩﷺሲናገሩ «አላህ እኮ በዓረፋ ምድር በሰፈሩ ባሮቹ በሰማይ ያሉ ባሮቹ ላይ ይፎክራል።» በማለት ገልፀውታል። [አልአልባኒይ ሰሂህ ብለውታል።]

ከዚህ እንደምንረዳው ጌታችን አላህ በዓረፋ ምድር ያሉትን ባሮቹን በመጥቀስ እዩኣቸው ባሮቼን ለኔ ብለው ቤት ንብረታቸውን ትተው፣ የሚወዱትን የሚጓጉለትን ሁሉ ርቀው፣ ምቾታቸውን ድሎታቸውን ሁሉ እርግፍ አድርገው፣ ይህችን ከፈን ተሸፍነው፣ በጉዞ ጣጣ ደክመው ተጎሳቅለው፣ አቧራ ቡን ብሎባቸው፣ የዱንያ ላይ ማንነትና መበላለጣቸው ሳያግዳቸው ባንድ ሜዳ ተሰብስበው፣ ጌታችን ሆይ፣ አምላኬ ሆይ ማረን፣ ስጠን፣ ጠብቀን፣ አድርግልን፣ አድርሰን እያሉ ይለምኑኛል። በማለት በተግባራቸው እንደሚደሰትና እንደሚፎክርበት ያስገነዝበናል።

⑦ ከእሳት ቅጣት ነፃ ተደርጋችኋል የሚባሉ ሰዎች አብዛኞቹ በዓረፋ ቀን ነው

ኢማሙ ሙስሊም በዘገቡት ሀዲስ ነቢዩﷺ «አላህ ባርያውን ከእሳት ነፃ ከሚያወጣበት ቀናት መካከል የዓረፋ እለት ያህል የሚበዛበት እለት የለም። ጌታችን በእለቱ ቀረብ ይላል። ከዚያም “እነዚያ ሰዎች ምን ፈልገው ነው?” በማለት መላዕክቱ ላይ ይፎክራል።» በማለት ጌታችን አላህ ለሱ ግርማ ሞገስና ማንነት ተገቢ በሆነ መልኩ ለባሮቹ ወደ ቅርቢቷ ሰማይ ቀረብ ብሎ ምን እንደፈለጉ እያወቀ እንደነዚህ አይነት ባሮች ኣለኝ በሚል ለመሆኑ ከኔ ምን ፈልገው ነው በዚህ መልኩ የሚለምኑኝ የሚያመልኩኝ በማለት መላዕክቱ ላይ እንደሚፎር ገልፀዋል።

ኢብኑ ዐብዱል በር ረሂመሁላህ እንደገለፁት «ይህ ሀዲስ እንደሚጠቁመው እነዚያ ሐጃጆች ምህረት እንደተደረገላቸው ነው። ምክንያቱም ይቅርታና ምህረት ካደረገላቸው በኋላ ቢሆን እንጂ አላህ በኃጢኣተኞችና በወንጀለኞች ተኩራርቶ አይፎክርምና ነው።» ብለዋል።

⑧ በዓረፋ ቀን በዓረፋ ሜዳ መገኘት ከሐጅ ተግባር መስፈርቶች አንዱና ዋነኛው ነው

ነቢዩﷺ ጠቅለል አድርገው አንኳርነቱን ሲገልፁ «ሐጅ ዓረፋ ነው።» በማለት በዓረፋ ያልተገኘ ሐጅ እንደሌለው ጠቁመዋል። [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

ስለዚህም በዛሬዋ እለት እ
ንዲሁም ባሳለፍናቸው አመታትም በዓረፋ ሜዳ ከተገኙት ሐጃጆች ሁሉ አላህ መልካም ስራቸውን ይቀበላቸው። ከወንጀል ኃጢኣታቸው ያጥራቸው። ከእሳትም ነፃ ናችሁ ብሎ ለጀነቱ ይጫቸው። እኛንም ይወፍቀን።

ا•┈┈••✦••┈┈•ا
ዙልሒጃ 09/1439
ነሐሴ 14/2010
Aug 20/2018

@tenbihat
عيدكم مبارك
وتقبل الله منا ومنكم صالح الاعمال

እንኳን ለዒድ አል አድሐ በአል በሰላም አደረሳችሁ

© ተንቢሀት
ዳሩ–ተውሒድ የወቅፍ ፕሮጀክት

በታሪካዊው የወቅፍ ፕሮጀክት ላይ አሻራዎን ያኑሩ!

በኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር አማካኝነት በመካሄድ ላይ ያሉ ህጋዊና ዘርፈ ብዙ የዳዕዋ እንቅስቃሴዎችን በቋሚነት የሚደጉመውን ዳሩ–ተውሒድ የወቅፍ ፕሮጀክት ተባብረን እውን እናድርግ!

የፕሮጀክቱ ቦታ፦ አዲስ አበባ
ተመን፦ 100 ሚልየን
አላማ፦ በኪራይ ገቢ ዳዕዋን በቋሚነት መደገፍ

🤝 ድጋፍዎን በ sms ይምረጡ

🎁 በቤተሰብ ስም
50,000 ብር ለመነየት 1 ቁጥር

🎁አባትና ለእናት ስም ወቅፍ
20,000 ብር ለመነየት 2 ቁጥር

🎁 የግለሰብ ወቅፍ
10,000 ብር ለመነየት 3 ቁጥር

🎁 በልጆች ስም ወቅፍ
5,000 ብር ለመነየት 4 ቁጥር

🤝 አሁኑኑ ኒያዎን ለማሳወቅ ወደ 0972757575 መልእክት ይላኩ!


የወቅፉ ገቢ ለምን ይውላል?
√ ነሲሓ ቲቪ
√ ነሲሓ መስጂድና መድረሳ
√ ዳሩል ሀዲስ ኢስላማዊ ኮሌጅ
√ የቁርአን ሒፍዝ ሀለቃት
√ ኢልም ተኮር ኮርሶች
√ ቃፊላ የዳዕዋ ጉዞዎች
√ ነሲሓ በራሪ ወረቀቶች

እና ሌሎችም አንፀባራቂ የዳዕዋ ስራዎች

وَأَقۡرِضُوا۟ ٱللَّهَ قَرۡضًا حَسَنࣰاۚ وَمَا تُقَدِّمُوا۟ لِأَنفُسِكُم مِّنۡ خَیۡرࣲ تَجِدُوهُ عِندَ ٱللَّهِ هُوَ خَیۡرࣰا وَأَعۡظَمَ أَجۡرࣰاۚ

[ለአላህም መልካም ብደርን አበድሩ፡፡ ከመልካም ሥራም ለነፍሶቻችሁ የምታስቀድሙትን ሁሉ እርሱ የተሻለና በምንዳም ታላቅ ኾኖ አላህ ዘንድ ታገኙታላችሁ] ሙዘሚል 20

ኒያዎን ለወቅፍ አካውንት ገቢ ለማድረግ

የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000337985328
ኢብኑ መሰኡድ ኢስላሚክ ሴንተር


T.me/Merkezuna