ተንቢሃት Tenbihat – ኢስላማዊ ህግጋት እና ተግሳፃት
6.76K subscribers
1.38K photos
118 videos
173 files
1.38K links
ተንቢሀት - የተለያዩ ኢስላማዊ ትምህርቶች የሚቀርቡበት ቻነል nesiha.com
Download Telegram
ነገ እሁድ ሐምሌ 26/2012 በነሲሓ ቲቪ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ልዩ የ 'ዳሩ-ተውሂድ ወቅፍ' ማስተባበሪያ ሀገር አቀፍ የቴሌቶን ኘሮግራም ስለሚኖር እርስዎም ይሳተፉ
መልእክቱንም ለሌሎች ያስተላልፉ!

ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር
ፕሮጀክቱን በማስተዋወቅ ተባበሩን

ዳሩ–ተውሒድ የወቅፍ ፕሮጀክት

አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ

የወቅፉ ገቢ ለምን ይውላል?
√ ነሲሓ ቲቪ
√ ነሲሓ መስጂድና መድረሳ
√ ዳሩል ሀዲስ ኢስላማዊ ኮሌጅ
√ የቁርአን ሒፍዝ ሀለቃት
√ ኢልም ተኮር ኮርሶች
√ ቃፊላ የዳዕዋ ጉዞዎች
እና ሌሎችም አንፀባራቂ የዳዕዋ ስራዎች

ኒያዎን በsms ያሳውቁ 0972757575

ኒያዎን ለወቅፍ አካውንት ገቢ ለማድረግ
ንግድ ባንክ 1000337985328
T.me/darutewhidweqf
ለምን ወቅፍ እናደርጋለን?
ኢስላማዊ ሸሪዓ የተሟላ የተዋበ እና ለሰዎች መልካሙን ሁሉ የሚያመቻች የፍትህ ህግ ነው። የሰው ልጆች በምድራዊ ህይወታችው እንዲተባበሩና እውነተኛ ማህበራዊ መደጋገፍን እውን እንዲያደርጉ ያስተምራል። አንድ የአላህ ባርያ አላህ ከሰጠው ሀብት ለሌሎች ግልጋሎት በሚሰጥና ጥቅሙ ቀጣይነት ባለው የምፅዋት አይነት (ሰደቃህ ጃሪያህ) እንዲሳተፍ ያበረታታል። ይህ አይነቱን ቀጣይ ሰደቃ ልዩ የሚያደርገው ገንዘቡን ያወጣው ሰው በህይወት ባይኖር እንኳን ሰው እስከተጠቀመበት ድረስ የመልካም ስራ ምንዳ(አጅር) የሚያስመዘግብለት መሆኑ ነው። በኢስላም ወቅፍ በመባል የሚታወቀው ይህ አይነቱ ሰደቃ እጅግ ብዙ ጥቅሞች ሲኖሩት ሸሪዓዊ መሰረቶቹም ጠንካራ ናቸው።

ወቅፍ እና ሙስሊሞች
ወቅፍ፤ ያለፉ ሰዎችን በህይወት ካሉት ጋር ያስተሳስራል፣ ማህበራዊ ግንኙነትን ያጎለብታል፣ እውነተኛ ማህበራዊ መደጋገፍን እዉን ያደርጋል። አላህ ለእርሱ ተብሎ ወጪ የተደረን ገንዘብ እንደሚተካ ቃል በመግባቱ ሙስሊሞች ለበጎ አድራጎት ቀዳሚነታቸውን አስመስክረዋል። ከመጀመሪያዎቹ ሙስሊም ትውልዶች ጀምሮ ብዙ ሙስሊሞች ማህበራዊ መደጋገፍን ባህሉ አድርጓል ከሚባል ከየትኛዉም ማህበረሰብ በበለጠ የከበረ ንብረታቸዉን ወቅፍ እንዳደረጉ ታሪክ ይዘክራል። የነብዩ هባልደረቦች አርአያነት ከምንም በላይ ለወቅፍ መበራከት ዋነኛ አስተዋፃኦ ነበረው። የተለያዩ መስጊዶችን፣ የቁርአን መማርያ መድረሳዎችን፣ አይታሞችን፣ ለችግረኞች ነፃ የምግብ እና የንፁህ ዉሀ የሚያቀርቡ ተቋማትን ወዘተ... ወቅፍ በማድረግ ሲያቋቁሙ ቆይተዋል።

እንዴት ወቅፍ ላድርግ?
ከሰደቃዎች ሁሉ የበለጠው ግን ለሰዎች የበለጠ ሊጠቅም የሚችልና ረጅም ዘመን ሊቆይ የሚችል ነው። ገቢ ካለዉና እያደገ ሊሎች ወቅፎችን የሚፈጥር ከሆነም የተመረጠ ነው። ለሰዎች የሚያስፈልጉ የወቅፍ አይነቶች ከጊዜ እና ከቦታ አንፃር ይለያያሉ። በሸሪዓ መሸጥና መለወጥ የሚፈቀድ እና ጥቅም ላይ መዋል የሚችል ሁሉ ወቅፍ መሆን ይችላል። እንደ መሬት እና ግንባታ ቋሚ ወይም እንደ መጓጓዣ ተንቀሳቃሽ የሆኑ ንብረቶች ሁሉ ወቅፍ ሊሆኑ ይችላሉ። የወቅፍ አላማ ደሀዎችን መርዳት ብቻ አይደለም።

ተከታዮቹ እንደምሳሌ የቀረቡ የወቅፍ አይነቶች ናቸው። መስጊዶችንና የዒባዳ ቦታዎችን ማስፋፋት እና መንከባከብ፣ የኢስላማዊ ዕዉቀትን የሚያስፋፉ ተቋሞችን መገንባት በመጽሀፍት ማደራጀት፤ ተማሪዎች በነጻ እንዲማሩባቸው የመድረሳዎችን ወጪ መሸፈን፣ የዲን ተማሪዎችንና አስተማሪዎችን መደገፍ፣ ኢስላማዊ ህትመቶችን ማገዝና ማበረታታት፣ የቁርአን ታህፊዝ ማዕከላትን ማቋቋም፣ ተዉሂድ እና ሱናን የሚያስፋፉ መፅሀፍትን እና ካሴቶችን ማባዛት፣ ችግረኞችን የሚያገለግሉ የጤና ተቋማትን መክፈት፣ የዉሀ ጉድጓዶችን መቆፈር፣ የየቲሞች እና የአዛዉንቶች ማረፍያዎችን ማቋቋም ወዘተ…

ዳሩ–ተውሒድ የወቅፍ ፕሮጀክትን እውን ለማድረግ ሁሉም ወገን የተቻለውን እንዲያበረክት አደራ እንላለን።

በዚሁ አጋጣሚ፤ በሀገራችን ኢትዮጵያ እየተዳከመ የመጣውን የአውቃፍ ስራ ለማነቃቃት ሁሉም በጋራ ጥረት ያደርግ ዘንድ አደራ እንላለን። አውቃፎችን የማስተዳደር እና የመንከባከብ ሀላፊነቶችንም እናስታውሳለን። ወቅፎችን የመቆጣጠር ሀላፊነት የተጣለባቸው አካላት ለወቅፍ አስተዳደር በቂ ትኩረት በመቸር ሀላፊነታቸውን ባግባቡ እንዲወጡ እንጠይቃለን።

t.me/darutewhidweqf
አንድ የነሲሓ ወዳጅ እህታችን ለዳሩተውሒድ የግል መንቀሳቀሻ Tico መኪናዋን ወደ ነሲሓ ቢሮ ልካለች

ሁላችንም እንረባረብ
ጀዛኩሙላሁ ኸይረን
🌅የተንቢሃት ልዩ መልዕክት!

🎁እንኳን አደረሳችሁ... ምን ማለት ነው?

ሰሞኑን በተደጋጋሚ እገሌና እገሌ ላይክ አድርገውታል እያለ ፌስቡክ ከሚልክልኝ መካከል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ትልቁን ቦታ ይዟል። ለጌታችን መወለድ እንኳን አደረሳችሁ ሲባል ሼር ወይም ላይክ የሚያደርጉ ብዙ እህትና ወንድሞችን አስተውያለው። ምናልባት ነገሩን እንደቀላል በመውሰድ የሚፈፀም ሊሆን ይችላል። ይህ ግን ምን የሚሉት መዘናጋት እንደሆነ አላውቅም!!

ለመሆኑ አንድ ሙስሊም እንኳን አደረሰህ ሲል፤ ምን እያለ እንደሆነ ግልፅ አይደለምን?

እንኳን አደረሰህ...

ጌታ ተወልዶ ተሰቅሎ ሞቷል ብለህ ለመለፈፍ፣ ለመስቀል ለመስገድና የፈጣሪን ክብር የሚነኩ ንግግሮችን ለመናገር በቃህ!

እንኳን አደረሰህ...
ማርያም ፈጣሪዋን ወለደችው፤ በመጠቅለያም ጠቀለለችው እያልክ ለመዘመር በቃህ!

ለዚህ ኩፍር ከሆነ መድረሱ ልምንስ እንኳን አብሮ አደረሰን ይባላል??

ከዚህ የከፋው ደግሞ እንኳን ደስ ያለህ የሚለው ነው...

እውቁ አሊም ኢብኑል ቀይም ረሂመሁላህ ይህ ተግባር የተከለከለ ስለመሆኑ የኡለማዎች የጋራ አቋም መሆኑን በመጠቆም እንዲህ ብለዋል፤

" وأما التهنئة بشعائر الكفر المختصة به فحرام بالاتفاق، مثل أن يهنئهم بأعيادهم وصومهم، فيقول: عيد مبارك عليك، أو تهنأ بهذا العيد ونحوه، فهذا إن سلم قائله من الكفر فهو من المحرمات ، وهو بمنزلة أن تهنئه بسجوده للصليب ، بل ذلك أعظم إثما عند الله ، وأشد مقتا من التهنئة بشرب الخمر وقتل النفس ، وارتكاب الفرج الحرام ونحوه . وكثير ممن لا قدر للدين عنده يقع في ذلك ، ولا يدري قبح ما فعل ، فمن هنأ عبدا بمعصية أو بدعة أو كفر فقد تعرض لمقت الله وسخطه ". انتهى كلامه رحمه الله

«ኩፍርን ብቻ በሚያንፀባርቁ የሀይማኖታቸው መገለጫዎች እንኳን አደረሳችሁ...እንኳን ደስ ያለችሁ ማለት ሀራም መሆኑ የሁሉም ሊቃውንት ስምምነት ያለበት ነው።
ለምሳሌ አንድ ሙስሊም በነሱ በዓላትና ፆም ጊዜ፤ «በአሉን የተባረከ ያድርግልህ» ወይም «መልካም የደስታ በአል ያድርግልህ» እና መሰል የደስታ መግለጫዎችን ቢያስተላልፍ፤ ተናጋሪው ከኩፍር ቢድን እንኳ ከባድ ወንጀል ነው የፈፀመው። ይህም፤ ልክ «እንኳን ለመስቀል ሰገድክ» ብሎ ደስታን እንደመግለፅ ነው!

ይህ እንደውም፤ አንድ ሰው ነብስ በማጥፋቱ፣ አልኮል በመጠጣቱ፣ ዝሙት በመፈፀሙና በመሰል ተግባራት እንኳን ደስ ያለህ ከማለት በወንጀልነት የከበደ እና አስቀያሚ ነው። ለኢስላማዊ ድንጋጌዎች ተገቢዉን ክብር የማይሰጡ ብዙ ሰዎች ይህንን ይፈፅማሉ። ምን ያክል የሚያስጠላ የግባር እንደፈፀሙም አያስተውሉም። ቢድአ፣ ኩፍር እና ወንጀሎች በመፈፀማቸው እንኳን አደረሰህ፣ እንኳን ደስ ያለህ እና መሰል የደስታ መግለጫዎችን ያስተላለፈ፤ እራሱን ለአላህ ቁጣና ጥላቻ የተገባ እንዲሆን የሚያደርግ ምክኒያት ፈፅሟል» አህካም አህሉዚማህ

قال الشيخ ابن عثيمين: وإنما كانت تهنئة الكفار بأعيادهم الدينية حراما وبهذه المثابة التي ذكرها ابن القيم لأن فيها إقرارا لما هم عليه من شعائر الكفر ، ورضا به لهم ، وإن كان هو لا يرضى بهذا الكفر لنفسه ، لكن يحرم على المسلم أن يرضى بشعائر الكفر أو يهنئ بها غيره ، لأن الله تعالى لا يرضى بذلك ، كما قال الله تعالى : (إِنْ تَكْفُرُوا فَإِنَّ اللَّهَ غَنِيٌّ عَنْكُمْ وَلَا يَرْضَى لِعِبَادِهِ الْكُفْرَ وَإِنْ تَشْكُرُوا يَرْضَهُ لَكُمْ) الزمر/7 . وقال تعالى : (الْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمْ الْإِسْلَامَ دِينًا) المائدة/3 .

የዘመናችን ፈቂህ ሸይኽ ኡሰይሚን ረሂመሁላህ እንዲህ አሉ «ካፊሮችን እንኳን አደረሳችሁ ማለት ኢብኑል ቀይም እንዳለው የዚህን ያክል ከባድ የሆነበት ምክኒያት እነርሱ የሚፈፅሟቸውን የኩፍር መገለጫዎች ማፅደቅ ስለሆነ ነው። ምንም እንኳን ለራሱ ይህንን ኩፍር መፈፀምን ባይወድም እነሱ መፈፀማቸውን ወዷልና። ሙስሊም ደግሞ የኩፍር መገለጫዎችን መውደድም ይሁን ሌሎችን እንኳን ደስ ያላችሁ ማለት አይፈቀድለትም።»
መጅሙዑ ፈታዋ ወረሳኢል አሸይኽ ኢብኑ ኡሰይሚን 3/44

በካፊሮች በአል፤ እንኳን አደረሳችሁ... እንኳን ደስ አላችሁ... እንኳን አብሮ አደረሰን ማለት እነሱን ለማስደሰትም ይሁን ለመመሳሰል ከአላህ ዲን መንሸራተት እና የካፊሮችን ኩፍር የመናገር ስነልቦና መካብ ስለሆነ
ክልክል ነው።

በተመሳሳይ መልኩ፤ ክሪስማስም ሆነ ሌሎች በአላት ላይ ስጦታ ወይም ፓስት ካርድ መለዋወጥ፤ እንዲሁም ማንኛውም ደስታን መግለጫ የሆኑ ነገሮችን በመፈፀም በአሉን መካፈል የተከለከለ ነው።

አላህ ከጥፋት ሁሉ ይጠብቀን!

____
🕰ረጀብ 24/1437
🕰 1 ሜይ 2016
www.facebook.com/tenbihat

©ተንቢሀት
www.tenbihat.blogspot.com
ዓሹራን የመጾም ትሩፋት

ቡኻሪይ እንደዘገቡት ዐብዱሏህ ኢብን ዐባስ ረዲየሏሁ ዐንሁ የዓሹራን ጾም አስመልክተው ሲናገሩ የሚከተለውን ብለዋል (ነቢዩም ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንደ ዓሹራ ቀንና እንደ ረመዷን ወር ሆን ብለው <በጉጉት ጠብቀው> ሲጾሙ አይቻቸው አላውቅም!) ብለዋል።

በሌላም ሀዲስ ነቢዩ
(የዓሹራ ቀን ጾም ያለፈውን ዓመት ወንጀል ያስምራል<ያስሰርዛል> ብዬ ከአሏህ ላይ ተስፋ አደርጋለሁ) ብለዋል።

አንድን ቀን በመጾም የዓመት ወንጀል መማር ለሙእሚኖች ታላቅ የአሏህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ስጦታ ነው እድሉም ለሁሉም ክፍት ነው መሽቀዳደም እና መወዳደር ያማረው ሰው በሙሉ እንዲህ አይነቱ የኸይር ስራ ሜዳ ላይ ይሽቀዳደም!

የዓሹራ ቀን ጾም ያለፈውን ዓመት ወንጀል ያስምራል ያስሰርዛል በቀላል ስራ ይህን የምያህል ምንዳ የሚገኝ ሆኖ ሳለ ብዙ ለአኼራቸው ግድ የለሽ የሆኑ ሰዎች እድሉን ችላ ሲሉ እንመለከታለን።
ዱኒያዊ ጥቅም ቢሆን ግን አይዘናጉም ነበር አልፎም እድሉ ላይ በመሻማት ይፋጁ ነበር ግን {አብዛኞችየሰው ልጆች አያውቁም} አርሩም 6

የዓሹራእ ጾም ሙሐረም ስንተኛው ቀን ላይ ነውን?

የዓሹራእ ጾም ማለት የሙሐረም ወር 10ኛው ቀን ላይ ሲሆን ከፊቱ ወይም ከኋላው አንድ ቀን (9ኛውን ወይም 11ኛውን) ቀን ጨምሮ መጾም ይመረጣል። ምክኒያቱም ነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ዓሹራን ሲጾሙና ሷሓባዎችም እንዲጾሙት በመከሯቸው ጊዜ አይሁዶች የሚያከብሩት ቀን እንደሆነ ለነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ሲነግራቸው የሚከተለውን ብለዋል, (አሏህ ካለ የሚመጣው ዓመት ላይ 9ኛውንም ቀን እንጾማለን) ብለዋል ከዚህም በመነሳት ዑለማዎች ዘጠነኛውንም ቀን መጾም ሱና ነው ብለዋል።

ከዓሹራ ጋር 9ኛውን ቀን መጾም ምክኒያቶች አሉት
ከነዚህም መሀል አንዱ 10ኛውን ቀን ብቻ መጾም ከአይሁዶች ጋር መመሳሰልን ስለሚያመጣ አንድ ቀን ጨምሮ መጾሙ ከነሱ ጋር መለያየትን ያስገኛል ከጠመሙ ህዝቦች ጋር መመሳሰል በዲናችን ክልክል ከመሆኑ አንጻር እነሱን ለመቃረን ተብሎ ሸሪዓችን አንድን ነገር ማድረግ ሲከለክል ወይም ደግሞ ስያዝ ሁሉ እናያለን ይህም ሆኖ ሳለ ግን ብዙ ሙስሊሞች አይሁድና ነሳራ ያደረጉትን ለማድረግ ሲሽቀዳደሙ እንመለከታለንል!

ይህ በንዲህ እንዳለ ምናልባት የቀን አቆጣጠር ላይ ስህተት ቢፈጠር እና የወሩ መግቢያ አሻሚ ቢሆን ሁለቱን ቀናት መጾም የዓሹራን ቀን ማግኘት ላይ እርግጠኛ ያደርጋል። በላጩ 9 እና 10ኛውን ቀን መጾሙ ሲሆን ያልተመቸው ሰው 10 እና 11ኛውን ቀን መጾም ይችላል። እንዲሁ ዋናውን የዓሹራን ቀን ብቻ እንጂ ሌላ ተጨማሪ ቀን መጾም ያልቻለ ሰው ብቻውን መጾም እንደማይከለከል ዑለማዎች ገልጸዋል

ጁሙዓ ወይም ቅዳሜ ቀንን ለብቻው (ከፊት ወይም ከኋላ አንድ ቀን ሳይጾሙ) ነጥሎ መጾም እንደማይቻል በሐዲሶች የተገለጸ ሲሆን አጋጣሚ ዓሹራ ጾም በጁሙዓ ወይም ቅዳሜ ዕለት ቢሆን መጾም አይከለከልም።

ዓሹራ ጾም ብቻ ሳይሆን ሌሎችም እንደ ቀዷ ወይም የነዝር (ስለት) እነ መስል ምክንያይ ያላቸው ጾሞችንም መጾም አይከለከልም

ዓሹራን መጾም የቱን ወንጀል ነው የሚያስምረው?
ዓሹራን መጾም ያለፈውን ዓመት ወንጀል እንደሚያሠርዝ ጠቅሰናል ይህ ምህረት ጥቃቀን ወንጀሎችን ነው የሚመለከተው ወይስ ከበባዶችንም ጭምር? ይህን አስመልክተው ኢማም አንነወዊይ የሚከተለውን ብለዋል፦
"የዓረፋ ጾምም ይሁን የዓሹራ ሌሎችም ወንጀልን ያስምራሉ የተባሉ ኢባዳዎች ጥቃቅን የሚባሉ ወንጀሎችን በሙሉ ያሰርዛሉ ጥቃቅን ወንጀሎች የሌሉበት እንደሆነ በምትኩ መልካም ስራዎች ይመዘገቡለታል አላህ ዘንድም ያለው ደረጃ ይጨምራል ጥቃቅን ወንጀሎች የሌሉበት ሆኖ አንድ ወይም ከዛ በላይ ከባድ ወንጀል ያለበት እንደሆነ ወንጀሉን ያቀለዋል ብለን አሏህ ላይ ተስፋ እናደርጋለን""

ቀዷ ያለበት ሰው ዓሹራ መጾም ይችላልን?

እንደ ዓሹራ ያሉ ሱና ጾሞችን ያለምንም ጥርጣሬ ለመጾም ያለብንን ቀዷ ፈጠን ብለን ማውጣቱ ይመረጣል።ቀዳውን ሳይጾም ወቅቱ የሚያልፍ የሱና ጾም የደረሰበት ሰው በቀጣይ ለቀዳ ሰፊ ጊዜ እስካለው፡ድረስ ፈርዱን ቀዳ ሳያወጣ ሱና ቢጾም ችግር አይኖረውም።

ከዓሹራ ጋር በተያያዘ የሚፈፀሙ ቢድዓዎች
ታላቁ የዲን መሪ ሸይክኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ ይህን በተመለከተ የሚከተለውን ጥያቄ ተጠየቁ
"በዓሹራ ቀን ሰዎች ገላቸውን ሲታጠቡ፣ ሲኳኳሉ፣ሂና ሲቀቡ፣ ልዩ ሰላምታ ሲለዋወጡና ሲጨባበጡ፣ልዩ ምግብም ሲሰሩ እና ልዩ ደስታ ሲደሰቱ ይታያል ይህ ነገር በሸሪዓችን መሰረት አለውን?" እሳቸውም ሲመልሱ {{ ይህን አስመልክቶ ከነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም የተገኘ አንድም ሷሒሕ ሐዲስ የለም ሷሓቦቻቸውም ይህን አስመልክተው ያሉት ነገር የለም ቀደምት የዲን መሪዎችም አረቱም መሪዎች (ኢማም፥አቡ ሐኒፋ፣ማሊክ፣ሻፊዒ እና አሕመድ) ይሁን ሌሎችም፣ ከነሱም ውጪ ያሉት ታዋቂ የሸሪዓ እውቀት ምንጭ የሚባሉ መጻህፍት ባለቤቶችም በዚህ ጉዳይ ከነቢዩም ይሁን ከሷሓቦች ወይም ከተከታዮቻቸው ምንም የዘገቡት ነገር የለም)) ብለው መልሰዋል
ከቢድዓ በመጠንቀቅ በዲኑ የተፈቀዱ ነገሮችን ብቻ በመስራት ወደ አላህ እንቃረብ!

አላህ ይወፍቀን

ኡስታዝ አሕመድ ኣደም
ሙሐረም 7/1439ዓ.ሂ
🔸 🔹 🔸🔹 🔸🔹🔸
🌐https://telegram.me/ahmedadem
አልሀምዱሊላህ!
ዛሬ በአላህ ፍቃድ ለአፋር የጎርፍ አደጋ ተጎጂ ወገኖቻችን በነሲሓ በጎ አድራጎትና የልማት ድርጅት በኩል የተሰበሰበውን ድጋፍ ጭነት ጉዞ እናደርጋለን!

👉 ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ደግሞ በአላህ ፍቃድ በስልጤ ክልል በጎርፍ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የሚሆን ድጋፍ የማሰባሰብ ስራ ጀምረናል።

👉 በነሲሓ በጎ አድራጎትና የልማት ድርጅት ስር ባሉት ሁሉም የድጋፍ ማሰባሰቢያ ጣቢያዎች ማለትም በአዲስ አበባ በተለያዩ ቦታዎች ፣ በባህዳር፣ በአዳማ፣ በወልቂጤ እንዲሁም በስልጤ የድጋፍ ስራ ተጀምሯል።

👉 ሁላችንም በያለንበት ለወገኖቻችን አለሁላችሁ እንበላቸው ባረከላሁ ፊኩም!

🕌 " አላህ ባርያውን በመርዳት ላይ ነው ባርያው ወንድሙን በመርዳት ላይ እስካለ ድረስ" ረሱል ( صلى الله عليه وسلم)

📱 ለበለጠ መረጃ በ 0972 747474

www.nesiha.com/charity
@NesihaCharityMain
Darutawhid Waqf:
አሰላሙአለይኩም

መልዕክትም ነበረኝ እሱም እኔና ባለቤቴ ከተጋባን ሁለት ዐመት እንኳን አልሞላንም ያ ማለት የባለቤቴንና ቀለበቴን በውል ያለጣጣምኩበት ሆኔታ ነው ያለው ይህ ሆኖ ሳለ ልሰጥ የተነሳሳሁበት ምክንት ኢብኑ መስዑድ ኢስለሚክ ሴንተር ማህበረሰባችን ካለበት ዘርፈብዙ ሗለቀርነት ለማውጣት በጣም ብዙ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ ነው በተለይ ነሲሓ ቲቪ አንድም ቀን ባአቅም ችግር ፕሮግራሙ ሲስቶጓገል ማየት ስለማልፈልግ እና አላህ እውቀት እንዲጨምርልኝ ወንጀሌን እንዲምርልኝ
ሁለተኛ ደግሞ ይህንን ልዘረዝር የፈለግኩት ብዙ እህቶቼ ከኔ በበለጠ አቅም ያለቸው ሁኔታውም የተመቻቸላቸው መስጠት /ወቅፍ ማረግ እያቻሉ ያልሰጡ ስላሉ ና ባይሰጡ እንኳ በዚህ ተናሳስተው ነሲሓ የሚያስተላልፈውን የዕውቀት ማዕድ ተካፍለው ካሉበት መዘነጋት ሊወጡ ሰበብ ይሆናቸዋል ብዬ ስላሰብኩ ነው ይህንን ስል ግን ብዙ ማሻዓ አሏሂ የሆኑና ከሌላቸው የሰደቁ እህቶችንም ዘንግቼ አይደለም።

እንዴት ገቢ እንደማደርግ ግን ጠቁሙኝ ባረከላሁ ፊኩም

እህታችሁ አይሻ መሀመድ

---------//-----------



ዳሩ–ተውሒድ የወቅፍ ፕሮጀክት

የወቅፉ ገቢ ለምን ይውላል?
√ ነሲሓ ቲቪ
√ ነሲሓ መስጂድና መድረሳ
√ ዳሩል ሀዲስ ኢስላማዊ ኮሌጅ
√ የቁርአን ሒፍዝ ሀለቃት
√ ኢልም ተኮር ኮርሶች
√ ቃፊላ የዳዕዋ ጉዞዎች
እና ሌሎችም አንፀባራቂ የዳዕዋ ስራዎች

ኒያዎን በsms ያሳውቁ 0972757575

ኒያዎን ለወቅፍ አካውንት ገቢ ለማድረግ
ንግድ ባንክ 1000337985328
T.me/darutewhidweqf
ተንቢሃት Tenbihat – ኢስላማዊ ህግጋት እና ተግሳፃት pinned «የሺዓና የአህሉሱና የዓሹራ ውሎ የዓሹራ ቀን፤ የፊዓአውንን ትእቢትና አምባገነነንነት ያከተመበትና ለሌሎችም መቀጣጫ የሆነበት፣ ነብዩላህ ሙሳም የተደሰቱበት ለአህሉሱና ታላቅ ትርጉም ያለው የድል ብስራት ቀን ነው። አህሉሱና ይህንን ቀን በአል አያደርጉትም። የተለየ ድግስም ሆነ አለባበስ የላቸውም። ሆኖም መልእክተኛው ﷺ በደነገጉት መሰረት ይፆሙታል፣ መልካም ተግባራትን ይፈፅሙበታል፣ ከአላህ ልዩ ምንዳን በመከጀልም…»
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ዳሩ–ተውሒድ የወቅፍ ፕሮጀክት

የወቅፉ ገቢ ለምን ይውላል?
√ ነሲሓ ቲቪ
√ ነሲሓ መስጂድና መድረሳ
√ ዳሩል ሀዲስ ኢስላማዊ ኮሌጅ
√ የቁርአን ሒፍዝ ሀለቃት
√ ኢልም ተኮር ኮርሶች
√ ቃፊላ የዳዕዋ ጉዞዎች
እና ሌሎችም አንፀባራቂ የዳዕዋ ስራዎች

ኒያዎን በsms ያሳውቁ 0972757575

ኒያዎን ለወቅፍ አካውንት ገቢ ለማድረግ
ንግድ ባንክ 1000337985328
T.me/darutewhidweqf
Jenet Na Tsegawocha
Muhammed Hassen Mame
🍁 ጀነት እና ፀጋዎቿ
(ከ 10 አመት በፊት የቀረበ ሙሐደራ)

🎤 ሙሀመድ ሀሰን ማሜ
https://tttttt.me/nesihastudio/1846

Share... share

@nesihastudio
መዓዘላህ... በአላህ እጠበቃለሁ!

ከስክሪን በስተጀርባ ካሰፈሰፉ ሰይጣናት ሁሉ በአላህ እጠበቃለሁ!

👒 እህቴ ሆይ!
በቅድሚያ፤ ያለሽው በፈተናዎች ዘመን ስለሆነ የተጋረጠብሽን ለመወጣት ካንቺ ጥንቁቅነት፣ ቆራጥነትና በአላህ መመካት የመሳሰሉ ባህርያትን መላበስ እጅግ አስፈላጊ መሆናቸውን ልብ በይ።

ባለንበት ዘመን አንቺን ወደ መጥፎ ነገሮች የሚጎተጉቱ ወስዋሶች በርካታ ናቸው።

☞ በተለይም ነፍሲያ፣ የሰው ሰይጣናትና የጂን ሰይጣናት ተጠቃሾች ናቸው።

ነፍሲያ ማለት የየራሳችን ግላዊ ስሜት ሲሆን፤

የሰው ሰይጣናት ስንል ደግሞ እንደ እኛው ሰዎች የሆኑ፤ ግና በሩቅም በቅርብም ሆነው ወደ ክፉ ነገር የሚያነሳሱን፣ ወደ ስህተት የሚገፋፉንና ለወንጀል የሚያመቻቹን የጥፋት ጓዶች ናቸው።

ባህሪያቸው የሰይጣንን ባህሪ የተላበሰ በመሆኑ የሰው ሰይጣናት ይባላሉ።

የጂን ሰይጣናት ደግሞ በተፈጥሮአቸው ከማይታዩት ከጂኖች/አጋንንቶች የሚመደቡ ሲሆን፤ በቁንጮአቸው ኢብሊስና ዝርዮቹ የሚመሩ ናቸው። እነኝህ ሰዎችን በስውር የሚጎተጉቱና ለወንጀል የሚዳርጉ ክፉ ፍጡሮች ናቸው።

☞ የሰው ሰይጣናዊነት አንዱ ባንዱ ላይ በሚያደርገው ክፉ እምነትና ተግባር የሚገለፅ በመሆኑ በብዙ ነገሮች ውስጥ ይገባል።

ለምሳሌ ያክል በዘመኑ የመገናኛ አውታር በኢንተርኔት በሰው ሰይጣኖች ገፋፊነት ብዙ ፈሳዶች ሲተገበሩ ይታያል ይሰማልም።

ሙስሊሟን ሴት ለማጥቃት እና ወደ ብልግና ለመሳብ ከስክሪን ጀርባ እንዳሰፈሰፉ መሽቶ የሚነጋባቸው ወስላቶች እዚህ ጋር ተጠቃሽ ናቸው።

በተለያዩ ዘዴዎች ካንቺ ጋር ይፃፃፋሉ፣ ያወጋሉ። አንቺም ሂጃብሽ፣ ድብቅነትሽና ጥንቃቄሽ ትርጉም እንዲያጣ በሚያደርግ መልኩ በሱስ ትጠመጂና ወሬ ለጀመረ ሁሉ በርሽን ክፍት ታደርጊያለሽ።

የዚያኔ ቀድመው የተዘጋጁት መሰሪዎች የባጡን የቆጡን እየፈለፈሉልሽና እያስለፈለፉሽ ወደ ተንኮል መረባቸው ይከቱሻል። የትዳርም ይሁን ሌላ ወሬ ይዘው በምርቃና ያከንፉሻል፤ ላሰቡት ፀያፍ ምግባር ግብአት እስክትሆኚም በነገር ያዋኙሻል፤

ይህ ጉዳይ አንተን ወንድሜንም ይመለከተሃል

በእንደዚህ አይነቶቹ የሰው ሰይጣናት ተሸንግለህ እውነተኛ ማንነቷን በውል ከማታውቃት ሴት ጋር የቻት የወሬ ትጀምራለህ፤ ቀስ በቀስም ውሃ ውስጥ እንደገባ ጨው ትሟሟለህ።

ሀራምን የመራቅ ብቃትህ፣ ሃይልህና ትእግስትህ ሁሉ ይመናመናል።

እናስታውስ...

ነቢዩላህ ዩሱፍ (ዓለይሂሰላም) ባሪያ ሆነው ተሽጦ ነበር። እንደፈለገ በሚያዝዘውና በሚያደርገው ንጉስ ስር በቤተመንግስት ነዋሪም ነበር።

በወቅቱ ነቢዩ ዩሱፍ በንጉሱም ሆነ ንግስቲቱ የታዘዘውን ከመፈም ውጭ አማራጭ አልነበረውም።

አንድ ጊዜ በክፍሉ ውስጥ ብቻውን እያለ የንጉሱ ሚስት በጣም ተውባና ተቆነጃጅታ ዘው ብላ ገባች። በሮቹን ሁሉ ቆላለፈች። ለእርሱ ስትል ዝግጅቷን እንዳጠናቀቀችም አበሰረችው። የምትፈልገውን እንዲያደርጋትም ሹክ አለችው።

ይህንን ታሪክ አላህ በቅዱስ ቃሉ እንዲህ ገለፀልን፦

{ وَرَاوَدَتْهُ الَّتِي هُوَ فِي بَيْتِهَا عَن نَّفْسِهِ وَغَلَّقَتِ الْأَبْوَابَ وَقَالَتْ هَيْتَ لَكَ ۚ قَالَ مَعَاذَ اللَّهِ ۖ إِنَّهُ رَبِّي أَحْسَنَ مَثْوَايَ ۖ إِنَّهُ لَا يُفْلِحُ الظَّالِمُون َ} [يوسف : 23]

« ያቺም እርሱ በቤትዋ የነበረባት ሴት፣ ከነፍሱ አባበለችው፤ ደጃፎችንም ዘጋች፤ ላንተ ተዘጋጅቼልሀለሁና ቶሎ ና አለች፤ *"በአላህ እጠበቃለሁ"* እርሱ (አሳዳሪዬ የገዛኝ) ጌታዬ ኑሮዬንም ያሳመረልኝ ነውና (አልከዳውም)፤ እነሆ! በደለኞች አይድኑም፤ አላት።» ዩሱፍ : 23

ነቢዩላሂ ዩሱፍ (ዓለይሂ ሰላም) ስሜቱን ከጫፍ የሚያደርሱ ነገሮች ቢያጋጥሙትም ራሱን አቅቦ፣ አሳዳሪ ንጉሱን ባለመክዳት፣ ፈጣሪ ጌታው አላህንም በመፍራት ይህን አጭር ምላሽ ሰጣት።

ምንም በንግስቲቷ ጥላ ስር ቢኖር፣ በሩን ቆላልፋበት ብታስገድደው፣ አማራጭ ማምለጫ ባይኖረውም ተስፋ አልቆረጠም፤ የጭንቅ ግዜ ደራሹ ወደሆነው አላህ ጥሪውን አቀረበ።

"قال معاذ الله"
«በአላህ እጠበቃለሁ አላት» ዩሱፍ : 23

በልቡ ውስጥ ያለና እርግጠኛ እምነቱ ነበርና ጌታውም አላህ ጠበቀው ፤ ከፈተናም አዳነው።

የዚህ አይነቱ ወደ ፀያፍ ተግባር የሚደረግ ጥሪ ዛሬም በኢንተርኔት የቻት መስኮቶች በተደጋጋሚ እየተለፈፈ ነው። ነገር ግን ከወንዱም ከሴቷም የነብዩ ዩሱፍን አይነት አቋምና ምላሽ ማን ይስጥ
«በአላህ እጠበቃለሁ!» የሚል!

ሁሌም ከአጉል ስሜት፣ ከሰውና ከጂን ሰይጣናት ለመጠበቅ የአላህ ፍራቻና ዱዓእ ሊለየን አይገባም።

ውድ እህቴ በተለያዩ የመገናኛ መስመሮች ከሚደረጉብሽ ትንኮሳዎችና የተሳሳቱ ግብዣዎች ራስሽን ተከላከይማንነትሽን ጠብቂ! ክብርሽንም አታስደፍሪ! በአቋምሽ ላይም የፀናሽ ቆራጥ ሁኚ!

«በአላህ እጠበቃለሁ!» ማለት የሁልጊዜ ልማድሽ ይሁን!

አላህ ሆይ! እህቶቻችንን ከጥፋት ሁሉ ጠብቅልን! የሙስሊሙ ማህበረሰብ አለኝታና የቤተሰብ መሰረት ናቸውና ከሰውና ከጂን ሰይጣናት ሁሉ ሰውራቸው! ለትእዛዝህ ተገዢም አድርጋቸው!!

አሚን!

ውዷ እህታችን፤ ይህ መልእክት ለጓደኞችሽ ይደርስ ዘንድ፤ «በአላህ እጠበቃለው» የሚለውን ድንቅ መርሆ በኮሜንት ላይ አስፍሪው።
_____
🌱ተንቢሃት
አማኝ ሴቶችን የተመለከቱ ህግጋት4
t.me/tenbihat