መኀደረ ጤና
2.58K subscribers
36 photos
13 videos
6 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩╩═╝
ስለ ጤናዎ ወሳኝ መረጃዎች💊 ሁሉም ሰው ሊያውቃቸው የሚገባ የጤና መረጃዎችን ከፈለጉ ይህን ቻናል ይቀላቀሉ ይማሩበታል ያስተምሩበታል መልካም ጤና ለሁላችን..


መልካም ጤና ለሁላችን..
Download Telegram
#የሆድ #ጥገኛ #ትላትሎች

የሆድ ጥገኛ ትላትሎች ህፃናትንና አዋቂዎችን የሚያጠቁ ቢሆኑም በአብዛኛዉ
በህፃናት ላይ ይከሰታሉ/ይበዛሉ፡፡ በጣም የተለያዩ የሆድ ጥገኛ ትላትሎች ያሉ
ሲሆን የተለመዱትና በብዛት ከሚገኙት ዉስጥ 👉ወስፋት፣
👉የመንጠቆ ትል፣
👉ጊኒ ወርም፣
👉ስተሮንግሎይድስ፣
👉የኮሶ ትል፣
👉ጃርድያና
👉አሜባ ይገኛሉ፡፡
የሆድ ጥገኛ ትላትሎች ወደ ሰዉነታችን የሚገቡት በቆዳ፣ በአፍንጫና በተበከለ ዉሃና ምግብ
ሲሆን ወደ ሰዉነታችን ከገቡ በኃላ በአንጀታችን ላይ በመራባት ጥሩ ስሜት
የሌላቸዉ የህመም ስሜቶች እንዲከሰቱ ያደርጋሉ፡፡
የህመም ምልክቶቹ
የአንጀት ስርዓት ለዉጥ መኖር፡- የሆድ ጥገኛ ትላትሎች የአንጀት ስርዓት ለዉጥ
እንዲኖር ያደርጋሉ፡፡ ይህም እንደ ጥገኛ ትላትሉ አይነት ሊለያይ የሚችል ሲሆን
ከነዚህም ዉስጥ #የሆድ #ድርቀት#ተቅማጥ ወይም #ልል #ሰገራ እንዲከሰት ያደርጋሉ፡፡
የምግብ ፍላጎት መለወጥ፡- የሆድ ጥገኛ ትላትሎች የሚመገቡትን ምግብዎን
ስለሚሻሙ በብዛት የሚከሰተዉ የምግብ ፍላጎት መጨመር ነዉ፡፡ እንድያዉም
አንዳንድ ሰዎች የምግብ ፍላጎታቸዉ እንደጨመረ እያለና ምግብ በደንብ
እየተመገቡ ሳለ ምንም ክብደት ያለመጨመር ሁኔታ ይታያል፡፡ በተቃራኒዉ ደግሞ
አንዳንድ ሰዎች ላይ የምግብ ፍላጎታቸዉ እንዲቀንስ ያደርጋሉ፡፡
ከምግብ ፍላጎት መቀነስ ጋር ተያይዞ ሰዉነታችን ፓራሳይቱን ለማስወገድ በሚያደርገዉ ጥረት
ዉስጥ ማቅለሽለሽና ማስታወክ በተጨማሪ ሊኖር ይችላል፡፡
ህመም፡- የሆድ ጥገኛ ትላትሎች አንጀት እንዲቆጣ ስሊሚያደርጉ የሆድ ህመም
እንዲከሰት ያደርጋሉ፡፡ የሆድ ጥገኛ ትላትሉ ለረጅም ጊዜ በአንጀት ዉስጥ
ከነበሩና ከአንጀት ዉጪ ወደ ሌሎች ቦታዎች ከተሰ0ራጩ ህመሙ ከአንጀት ዉጪ
በየትኛዉም የሰዉነት ክፍል እንዲኖር/እንዲከሰት ያደርጋሉ፡፡
ተጨማሪ የህመም ምልክቶች፡- ጉንፋን መሰል የህመም ምልክቶች፣ የሆድ መነፋትና ጋዝ መብዛት፣ በሰገራ ላይ የሆድ ጥገኛ ትላትሎችን
መታየት፣በፊንጢጣ ወይም በሴቶች ብልት ዙሪያ ማሳከክና የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡
ለሆድ ጥገኛ ትላትሎች መከሰት ምክንያቶች
የሆድ ጥገኛ ትላትሎች በየትኛዉም የአለማችን ክፍል የሚገኙ ቢሆንም ከሰሃራ
በታችና በከፊል ሰሃራማ አካባቢዎች በብዛት ይገኛሉ፡፡ ለሆድ ጥገኛ ትላትሎች
መከሰት ምክንያት ከሆኑት ዉስጥ የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡- #በንፅህና #ያልተዘጋጁ #ምግቦችን #መመገብ #የተበከለ #ዉሃ
#ቆሻሻ #የእጅ #ጣቶች
በደንብ ያልበሰለ ያልተቀቀሉ ስጋ( ለብ ለብ የተደረገ)
ጤናማ ያልሆነ የአመጋገብ ባህሪይ መኖር
በባዶ እግር መሄድ፡- እንደ መንጠቆ ትል ያሉ የሆድ ጥገኛ
ትላትሎች በባዶ እግር
የምንሄድ ከሆነ ትሉ የእግር ቆዳን በስቶ ወደ ሰዉነታችን ይገባል፡፡
ጥገኛ ተዋሲያን በብዛት ወደሚገኙበት ስፍራ መሄድ፡- ለምሳሌ የንፅህና አጠባበቃቸዉ ጥሩ ወደያልሆኑበት ቦታዎች መሄድ የግል ንፅህና አጠባበቅ አነስተኛ/ጥሩ ያለመሆን
የበሽታ መከላከል አቅም ደካማ መሆን/ መቀነስ
የኤች አይቪ ቫይረስ በደምዎ መኖር
በጥገኛ ትላትሎች የተያዙ የቤት እንስሳ ጋር መኖር
ለሆድ ጥገኛ ትላትሎች ሊደረጉ የሚችሉ ህክምናዎች
ለሆድ ጥገኛ ትላትሎች የሚደረገዉ ህክምና እንደጥገኛ ትላትሉ አይነት የሚለያይ
ሲሆን የህክምና ባለሙያዎን በማማከር አስፈላጊዉን ህክምና ማግኘት ይገባል፡፡
እንደ ጥገኛ ትላትሉ የህክምናዉ እርዝማኔ የሚለያይ ስለሆነ ከቀናት እስከ
ሳምንታት ሊዘልቅ ይችላል፡፡
የሆድ ጥገኛ ትላትሎችን #እንዴት #መከላከል #ይቻላል
👉የእጅ ጥፍርዎን ማሳጠር
ይህ ቆሻሻ በጥፍርዎ ስር
እንዳይጠራቀም በማድረግ
ብክለትን ይከላከላል፡፡
👉ሁሉንም አትክልትና ፍራፍሬዎች ከመመገብዎ በፊት በደንብ ማጠብ
👉ከመመገብዎ በፊት ምግብዎን በደንብ ማብሰል ፓራሳይቶችን ለመግደል ይረዳል፡፡
በተለይ ዝናባማ ወራትን ጨምሮ በሌሎች ጊዜያትም ቢሆን መጠጣት ያለብዎ
ፈልቶ የቀዘቀዘ አልያም የተጣራ ዉሃ መሆን አለበት፡፡
👉የግል ንፅህናዎን በደንብ/ በአግባቡ መጠበቅ
ምግብ ከመመገብዎ በፊት፣
👉ምግብ በሚያበስሉበት ወቅትና ከመፀዳጃ ቤት መልስ እጅዎን በዉሃና ሳሙና
መታጠብ
👉 እንዲሁም የቤት እንስሳዎችን ከነኩ/ካጫወቱ በኃላ እጅዎን በደንብ መታጠብ
👉የቤት እንስሳቶችን መደበኛ በሆነ መልኩ ከሆድ ጥገኛ ትላትሎች እንዲፀዱ
ማድረግ ከቤተሰብዎ መሃል አንድ ሰዉ የሆድ ጥገኛ ተዋህሲያን እንዳለበት ከታወቀ
ሌሎች የቤተሰቡ አባላትም መድሃኒት እንዲወስዱ በማድረግ ከሆድ ጥገኛ ትላትሎች እንዲፀዱ ማድረግ።
መልካም ጤና.