መኀደረ ጤና
2.6K subscribers
36 photos
13 videos
6 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩╩═╝
ስለ ጤናዎ ወሳኝ መረጃዎች💊 ሁሉም ሰው ሊያውቃቸው የሚገባ የጤና መረጃዎችን ከፈለጉ ይህን ቻናል ይቀላቀሉ ይማሩበታል ያስተምሩበታል መልካም ጤና ለሁላችን..


መልካም ጤና ለሁላችን..
Download Telegram
#የጀርባ_ሕመምዎን_ለማስታገስ_የሚረዱ #ጠቃሚ_ምክሮች

👉 #አቋምዎን_ያስተካክሉ

የጀርባ ሕመም የሚያሰቃይዎት ከሆነ በመጀመሪያ አቀማመጥዎን እና ከባድ ዕቃን የሚይዙበትን ሁኔታ ያስተካክሉ፡፡ ለብዙ ሰዓት ተቀምጠው የሚሠሩ ከሆነ ለወገብዎ መደገፊያ ማዘጋጀት ይኖርብዎታል፡፡ ከመቀመጫዎ ሲነሱ ቀጥ ብለው መነሳት እና ክብደት ያላቸውን ዕቃዎች በሚያነሱበት ጊዜ ከጉልበትዎ በርከክ ብለው ጀርባዎን ቀጥ በማድረግ መሆን አለበት፡፡
የኤሎክትሮኒክስ ዕቃዎችን የሚጠቀሙበትን ሰዓት ይቀንሱ
በሥራም ሆነ በማኅበራዊ ጉዳይ ምክንያት ለረጅም ሰዓታት ከኮምፒዩተሮችና ሌሎች የኤሎክትሮኒክስ ዕቃዎች ላይ የሚያሳልፉትን ጊዜ መወሰን ተገቢ ነው፡፡ አጎንብሰን እና ለረጅም ሰዓት ተቀምጠን የምንጠቀምባቸው ከሆነ የጀርባ ሕመም እና የራስ ምታትን ያስከትላሉ፡፡

👉 #መደበኛ_የአካል_ብቃት_እንቅስቃሴን #ያድርጉ

የጀርባ ሕመምን ቀላል በሚባል የአካል ማፍታታት እና አንገትን እና ወገብን በማንቀሳቀስ መከላከል ይችላሉ፡፡

👉 #ጭንቀትን_ይቀንሱ

ጭንቀት ለብዙ ዓይነት ሕመሞች እንደ ምክንያት የሚጠቀስ ሲሆን ከጀርባ ሕመም ጋርም ተያያዥነት እንዳለው ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ስለዚህም ለራስዎ ጊዜ በመስጠት እና በመዝናናት ጭንቀትዎን ይቀንሱ፡፡

👉 #የሰውነት_ክብደትዎን_ይቀንሱ

የሰውነትዎ ክብደት መጨመር በተለይም በወገብ አካባቢ ስብ ከተከማቸ የጀርባ ጡንቻዎችን ስለሚጎዳ የጀርባ ሕመም ተጠቂ ይሆናሉ፡፡ አመጋገብዎን ማስተካከል እና ክብደትዎን መቀነስ የጀርባ ሕመምዎን ይቀንሳል፡፡

👉 #በቂ_ዕረፍት_ያድርጉ

በቂ እረፍት ማድረግ ለሙሉ ጤናማነት ጠቃሚ ነው፡፡ እንቅልፍ በሚተኙ ጊዜ በጎንዎ በኩል መተኛት የጀርባ ሕመምዎን ይቀንሳል፡፡

👉 #በቂ_የፀሐይ_ብርሃን_ያግኙ

የፀሐይ ብርሃን ቢያንስ በቀን ለ10 ደቂቃ መውሰድ ለአጥንትዎ ጠንካራነት እጅግ ጠቃሚ እና ለጀርባ ሕመምዎ አንደኛው መፍትሔ ሊሆን ይችላል፡፡

👉 #ሲጋራ_ማጤስን_ያቁሙ

ሲጋራ ማጤስ ወደ ታችኛው የጀርባችን አጥንቶች የሚሄደውን የደም ዝውውር ስለሚቀንስ ለጀርባ ሕመም ይዳርጋል፡፡ ስለዚህም ሲጋራ ማጤስዎን እንዲያቆሙ ይመከራል፡፡

#መልካም_ጤና
#በቻይና_ሰዎች_የሰጧቸው_ዋና_ዋና #ጠቃሚ_ምክሮች

👉ሁለት አይነት ጫማ ይኑርዎት። አንዱ ከቤት ውጪ የሚጠቀሙበት ሲሆን ሌላኛው ቤት ውስጥ የሚጠቀሙበት ይሆናል። ከቤት ውጪ የሚጠቀሙበትን በፍጹም ወደ ቤት ውስጥ አያስገቡ። ቤት ውስጥ የሚጠቀሙበትን በፍጹም ወደ ውጪ አያውጡ።
👉አንድ የተለየ ጠረጴዛ ይኑርዎት። ከውጪ የሚገዟቸውን እቃዎች ለማኖር የሚያገለግል አንድ የተለየ ጠረጴዛ ይኑርዎት። ከውጪ የሚገዟቸውን እቃዎች በሙሉ ለምሳሌ እንደ መድሐኒት: መጠጦች: አትክልቶች እና ሌሎችንም ሳይነኩ ለ24 ሰዓት በጠረጴዛው እንዲቆዩ ያድርጉ።
👉በተቻለ መጠን የገንዘብ ኖቶችንም ሆነ ሳንቲሞችን አይስጡ: አይቀበሉ። የገንዘብ ኖቶችንም ሆነ ሳንቲሞችን ወደ ወደ ቤት የሚያመጡ ከሆነ ለዚህ ጉዳይ ለይተው ባስቀመጡት ጠረጴዛ ላይ ለ24 ሰዓት አቆይተው ይጠቀሙ።
👉ሁሉንም አይነት አትክልቶች ማለትም ቀይ ሽንኩርት: ነጭ ሽንኩርት: ድንች እና ሌሎችንም በፈላ ውሃ ሙልጭ አድርገው ይጠቡ። በፈላ ውሃ ሊታጠቡ የማይችሉ አትክልቶችን አይግዙ።
👉ከቤት ከወጡ በተቻለ መጠን የእጅ ስልክዎን ይዘው አይሂዱ። ይዘው ከወጡ ደግሞ ወደ ቤት ሲመልሱ በአልኮል ያጽዱ።
👉ከቤት ከወጡ በተቻለ መጠን የቤት ቁልፎችን ይዘው አይውጡ። ይዘው ከወጡ ደግሞ ወደ ቤት ሲመልሱ በአልኮል ያጽዱ።
👉ከቤት ወጥተው ሲመልሱ እጅዎንና ፊትዎን በሳሙና ይታጠቡ። ቤት እንደተመለሱ የለበሱትን ልብስ አውልቀው እንዲታጠብ ያድርጉ።
👉ሴት እህቶቻችን ከቤት ስትወጡ ጸጉራችሁ በአግባቡ መጠቅለሉን አረጋግጡ:: ጸጉራችሁን በእጃችሁ አትነካኩ:: ፊታችሁን ጸጉር በነካ እጃችሁ አትንኩ።
👉አትክልት ለመግዛት ሲሄዱ የእጅ ጓንት ያድርጉ። ወይም አትክልቶችን ሲያነሱ የፕላስቲክ ከረጢቶችን በሁለቱም እጅዎት ማጥለቅዎትን እርግጠኛ ይሁኑ። ወደ ቤት ሲመልሱ የእጅ ጓንትዎን ማጠብዎን አይዘንጉ። በፕላስቲክ ከረጢቶች ተጠቅመው ከሆነ ወደ ቤት ሲመልሱ ወይም ወዲያውን ከተጠቀሙ በኋላ ያስወግዱ።
👉 ሁልጊዜ ከቤት ከመውጣትዎ በፊት ራስዎን እና የሚያመጧቸውን ነገሮች ደህንነት እንዴት መጠበቅ እንደሚችሉ ያቅዱና በቂ ዝግጅት ያድርጉ።
👉በጣም የግድ ካልሆነ በስተቀር ምግብ ወይም መድሐኒት ለመግዛት ባይሰለፉ ይመረጣል። መሰለፉ ደግሞ የግድ ከሆነ እስከ ሁለት ሜትር ርቀትዎን ይጠብቁ።
👉ከውሾች እና ድመቶች ጋር ያለዎትን ንክኪ ያስወግዱ።
👉. በተቻለ መጠን አረጋውያን ወደ ውጪ ባይወጡ ይመክራል። ቤት ውስጥ ያሉ ወይም በአካባቢው ያሉ ሰዎች ለአረጋውያን የሚፈልጉትን ነገር ገዝተው ቢያመጡላቸው ይመክራል።
👉 ሁልጊዜ ከቤትዎ ከመውጣትዎ በፊት ከላይ የተጠቀሱትን መልዕክቶች በመመልከት አቅደው ተግባራዊ ያድርጉ።

#መልካም_ጤና