መኀደረ ጤና
2.6K subscribers
36 photos
13 videos
6 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩╩═╝
ስለ ጤናዎ ወሳኝ መረጃዎች💊 ሁሉም ሰው ሊያውቃቸው የሚገባ የጤና መረጃዎችን ከፈለጉ ይህን ቻናል ይቀላቀሉ ይማሩበታል ያስተምሩበታል መልካም ጤና ለሁላችን..


መልካም ጤና ለሁላችን..
Download Telegram
#የኮሮና_ቫይረስ_ምልክቶች

ዋና ምልክቶች (Major Indicators)
👉ትኩሳት (Fever)
👉ሳል (Cough)
የምግብ መፈጨት ችግር
👉ማስመለስ (Vomiting)
👉ተቅማጥ (Diarrhea)
👉የምግብ ፍላጎት መቀነስ (Loss of Apetite)

የነርቭ ምልክት (Nerve Symptoms)
👉የራስ ህመም (Head Ache)
👉የእይታ ችግር (Vision Problems)
👉የአይን ማቃጠል ወይም መለብለብ ናቸው።

#የቫይረሱ_መተላለፊያ_መንገዶች

በቻይና የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ (Coronavirus) ወረርሽኝ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ወደ ጤነኛ ሰው በሚከተሉት መንገዶች በሚከተሉት መንገዶች ይተላለፋል፦
👉በበሽታው የተያዘ ሰው በሚያስልበት ወይም በሚያስነጥስበት ወቅት በአየር ይተላለፋል
👉በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ከተነካካን ወይም እጅ ለእጅ ከተጨባበጥን (ሰላምታ)
👉ቫይረሱ ያለበትን ዕቃ ወይም ቁስ ከነካን በኋላ አፋችንን፣ አፍንጫችንን ወይም አይናችንን ከነካን በቫይረሱ በቀላሉ እንያዛለን

#ቫይረሱን_ለመከላከል_ምን_ማድረግ #አለብን?

ለኮሮና ቫይተስ የሚሆን ክትባት እስካሁን አልተሰራም፤ ለኮሮና ቫይረስ ኢንፌክሽንን ለመከላከል የሚረዳን ልክ ጉንፋን እንዳይዝዎት የሚያደርጉትን አይነት ጥንቃቄ ያድርጉ
👉እጅዎን ለብ ባለ ውሃ እና ሳሙና ይታጠቡ ወይም ከአልኮል የተሰሩ የእጅ ሳኒታይዘሮች (Hand Sanitizer) ይጠቀሙ
👉ህዝብ በተጨናነቀባቸው ቦታዎች ላለመሄድ ይሞክሩ
※ በሽታው ቢኖርብዎትም ባይኖርብዎትም አፍና አፍንጫዎን የሚከልል ማስክ ያድርጉ
👉አፍዎን፣ አፍንጫዎንና አይንዎን በፍጽም በእጅዎ ወይም በጣትዎ አይንኩ
👉በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ያለዎትን ቅርርብ (ንክኪ) ይቀንሱ።

#መልካም_ጤና