መኀደረ ጤና
2.6K subscribers
36 photos
13 videos
6 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩╩═╝
ስለ ጤናዎ ወሳኝ መረጃዎች💊 ሁሉም ሰው ሊያውቃቸው የሚገባ የጤና መረጃዎችን ከፈለጉ ይህን ቻናል ይቀላቀሉ ይማሩበታል ያስተምሩበታል መልካም ጤና ለሁላችን..


መልካም ጤና ለሁላችን..
Download Telegram
#ኪንታሮት - (Hemorrhoids)

#ኪንታሮት በፊንጢጣ ውስጥ እና በታችኛው ትልቁ አንጀት አካባቢ በህብረት
የሚገኙ የደም መልስ የደም ቧንቧዎች/ ስሮች ሲያብጡና ሲቆጡ የሚፈጠር
እብጠት ነው።
---
ለዚህ እብጠት(ኪንታሮት) መፈጠር መንስኤ ከሚሆኑት ውስጥ:-
👉ሠገራን በምናስወግድበት ወቅት አብዝተን ወይም ለረጅም ግዜ ማማጥ።
👉 ለረጅም ግዜ የቆየ ሳል።
👉ከመጠን በላይ የሆነ ውፍረት።
👉 ለረጅም ግዜ የቆየ የሆድ ድርቀት ወይም ተቅማጥ።
👉 እንዲሁም ሌሎች ሆድ ውስጥ ያለ ግፊት እንዲጨምር የሚያድርጉ ፣
(ለምሳሌ ለሆድ እብጠት የሚጋልጡ የጉበት በሽታዎች)።
👉በተጨማሪ በእርግዝና ግዜና እድሜያቸው ከ40 አመት በላይ የሆኑ ጎልማሶች ለይ በስፋት ይታያል።
#የኪንታሮት #ምልክቶችና #ሊያስከትላቸው #የሚችላቸው #ተዛማጅ #ችግሮች:-
👉 በፊንጣጣ ላይና ከፊንጢጣ ውስጥ የሚታይ እብጠት።
ኪንታሮት የውጪ/ውጫዊ ኪንታሮት (External Hemorrhoid)
እና የውስጥ ውስጣዊ ኪንታሮት(Internal Hemorrhoid) በመባል በሁለት ይከፈላል ። #የውስጥ#ውስጣዊ
👉የሚባለው ኪንታሮት(Internal Hemorrhoid) አራት ደረጃዎች ያሉት ሆኖ፣
የመጀመሪያ ደረጃ የሚባለው ላይ እብጠቱ ወደ ውጪ ወጥቶ አይታይም።
እንዲሁም ሁለተኛ ደረጃ ላይም ሰገራ በሚወገድበት ወቅት ላይ ብቻ ነው
እብጠቱ ሊታይ የሚችለው።
👉 ሰገራ በምናስወገድበት ሰዓት ህመም መሰማት፣ ማሳከክ ወይ አለመመቸት።
👉ህመም ሳይኖር በሰገራ ላይ ወይንም በምናፀዳበት ወረቀት ላይ ደም መኖር።
👉አንዳንዴ ደግሞ ያለቁጥጥራችን የሰገራ መውጣት።
👉አልፎ አልፎ ደግሞ በደንብ ሊደማ ስለሚችል ወይም ቀስ በቀስ የሚደማው
ደም ለደም ማነስ ሊያጋልጠን ይችላል።
👉አንዳንዴ እብጠቱ በመታጠፍ ወይም እብጠቱ ውስጥ ያሉ ደም ስሮች በረጋ
ደም በመዘጋት ከፍተኛ ህመም ሊሰማን ይችላል። ይህኔ ፈጥነን በአቅራቢያችን
ሚገኝ ሆስፒታል መሄድ ይኖርብናል።
---
---
#ከታች #የተዘረዘሩትን #ዘዴዎች #በመጠቀም #የኪንታሮት #ህመም #ስሜት #እና #መጠኑ
#እንዲቀንስ #ማድረግ #ይቻላል:-
👉ለብ ባለ ውሃ ውስጥ ሁለት/ሶስት ማንኪያ ጨው በመጨመር ከ15-20 ደቂቃ
በቀን ሁለት/ሶስት ግዜ በመቀመጫ/በፊንጣጣ መዘፍዘፍ።
👉 የሎሚ ጭማቂ መቀባት።
👉 በፋይበር የበለፀጉ አትክልትና ፍራፍሬዎችን መመገብ።
👉እብጠቱ ላይ በረዶን መያዝ ፣ በቀን ብዙ ግዜ እንደዚያ ማድረግ እብጠቱ
እንዲቀንስ ያደርጋል።
👉በቂ ውሃ መጠጣት።
👉ሰገራ በመጣ ግዜ ማስገወድ። አብዝተን አለማማጥ።
👉እንዲሁም ሀኪም ቤት በመሄድ የሚሰጠውን ምክርና የህክምና አገልግሎት በአግባቡ መከታተል።

#መልካም #ጤና
#ቫሪኮስ #ቬይንስ (Varicose veins)

#ቫሪኮስ #ቬይንስ የምንለው የህመም ዓይነት በማንኛውም የሰውነት ክፍላችን ቬይኖች (የደም መልስ) ቱቦዎች ሊከሰት የሚችል ቢሆንም በአብዛኛው የሚያጠቃውና የተለመደው በእግር ላይ የሚከሰተው ነው ይህም የሚሆነው ብዙ መቆምና በሰውነታችን ቬይንስ (የደም መልስ) ቱቦዎች ላይ ግፊት ስለሚፈጥር ነው

#ለቫሪኮስ #ቬይንስ #የሚያጋልጡ #ሁኔታዎች

👉ዕድሜ ፡-ዕድሜ መጨመር ለህመሙ ያጋልጣል
👉ፆታ፡- በሴቶች ላይ በአብዛኛው ይከሰታል ይህም የሚሆነው በሰውነታቸው ላይ ከሚከሰቱ ሆርሞን ለውጦች እና በእርግዝና ጊዜ ነው፡፡
👉በዘር፡- ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ አንድ የቤተሰብ አባል ተጠቂ ከሆነ ለሌላው የቤተሰብ አባል የመያዝ ዕድሉን ይጨምራል፡፡
👉ከልክ ያለፈ ውፍረት፡- የሰውነት ክብደት መጨመር በቬኖች የደም መመለስ ሥራ ላይ ጫናን ይፈጥራል፡፡
👉ለብዙ ሰዓታት መቆም ወይንም መቀመጥ፡- ደም ከእግራችን ወደ ልብ የሚመላለስበትን ሁኔታ በማዛባት ለብዙ ሰዓታት መቆምም ሆነ መቀመጥ ለቫሪኮስ ቬን ሕመም ተጋላጭ ያደርገል

#የቫሪኮስ #ቬይንስ #ህመም #ምልክቶች

በሽታው ብዙ ጊዜ ከፍተኛ ህመም ያለው ምልክት ባያሳይም ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ምልክቶች ሊከሰቱ ይችላሉ
ጥቁር ወይንጠጅ ወይንም ሰማያዊ ቀለም ያለው 👉የደምስር እብጠት በእግራችን ላይ መኖር
ጠመዝማዛ የሆኑና የአበጡ የደም ስሮች በእግሮ ላይ መታየት
👉እግሮን የመክበድና ህመም ስሜት መሰማት
በታችኛው የእግር ክፍሎ የማቃጠል፣ የመጨምደድና የመርገብገብ ስሜት መሰማት
ለረጅም ሰዓታት ሲቆሙም ሆነ ሲቀመጡ የሚብስ የህመም ስሜት የማሳከክ ስሜት

#የቫሪኮስ #ቬይንስ #የመከላከያ #መንገዶች

👉ሙሉ በሙሉ በሽታውን የምንቆጣጠርበት መንገድ ባይኖርም የደም ዝውውሮን ወይም የጡንቻ ጥንካሬን መጨመር ለበሽታው ያለውን ተጋላጭነት መቀነስ ይችላሉ

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማድረግ በሽታንውን ለመከላከል ይረዱናል

👉የአካል ብቃት እንቅስቃሴ
👉ክብደቶን መቆጣጠር
👉ጨው የበዛበት ምግብን መቀነስ
👉ከፍታ ያለው ጫማ አለማዘውተር
👉በእረፍት ወቅት ወይም ሲተኙ እግሮን በትራስ ከፍ ማድረግ
👉አቋቋምዎንና አቀማመጥዎን መለዋወጥ
ቫሪኮስ ቬይንስ ከፍተኛ ጉዳትን በአብዛኛው ባያስከትልም ከታች የሚጠቀሱትን ችግሮች ግን አልፎ አልፎም ቢሆን ሊያስከትል ይችላል

#ቁስለት እጅግ በጣም የሕመም ስሜት ያለው የእግር ቁስለት ከአበጠው የደም ስር አጠገብ በሚገኝ ቆዳ ላይ ሊከሰት ይችላል፡፡
በቆዳ ላይ የቀለም ለውጥ ከተከሰተ ወደ ሐኪም በመሄድ መመርመር ያስፈልጋል፡፡
#የደም #መርጋት አንዳንድ ጊዜ ከውስጥ የሚገኙ የደም መልስ ቱቦዎች ሊያብጡ ይችላሉ፡በዚህን ጊዜ የተጎዳው እግር ዕብጠትን ያሳያል፡፡
ድንገተኛ የሆነ እግር ማበጥ ከተከሰተ በአፋጣኝ ወደ ሕክምና መሄድ ተገቢ ነው

#መልካም #ጤና
#ግላውኮማ(Glaucoma)

#ግላውኮማ የምንለው የአይን ህመም በአይናችን ነርቭ ላይ ችግር የሚያስከትል ሲሆን በአይናችን ውስጥ የሚገኘው ግፊት መጨመር ምክንያት የሚከሰት ነው። የዚህ ግፊት መጨመር በአይናችን የምናያቸውን ምስሎች ወደ አንጎል የሚውስደውን የአይናችንን ነርቭ ይጎዳል ይህም በቀጣይነት ቋሚ ለሆነ የአይን ብርሃንን እጦት ይዳርጋል።

#የግላኮማ #ዓይነቶች #ምንድ #ናቸው?

🔘ሁለት ዋነኛ ዓይነቶች አሉ

👉Open-angle glaucoma በጣም የተለመደ ዓይነት ነው በዓይናችን ውስጥ ያለውን የውኃ ማስተላለፊያ አካል trabecular meshwork ተብሎ የሚጠራዉ ጤናማ ይመስላል, ግን ፈሳሹ እንደ ልብ አይንቀሳቀስም
👉Angle-closure glaucoma. በምዕራቡ ዓለም በእስያ እንጂ በስፋት የተለመደ አይደለም በአይንዎ መካከል ያለው ፍሰት በጣም ጠባብ ስለሚሆን ዓይንዎ በትክክል አይሰራም. ይህ በአይኑ ውስጥ ድንገተኛ መጨናነቅ ሊያስከትል ይችላል. በተጨማሪም በአይንዎ ውስጥ ያለውን ሌንስ ጭጋግ መሰል ነገር ያለብሰዋል

👉ግላውኮማ በሚጀምርበት ጊዜ የሚያሳየው ቀዳሚ ምልክት ወይንም የህመም ስሜት ስለሌለ ማንኛውም ሰው መደበኛ የሆነ የአይን ህክምና ማድረግ አስፈላጊ ነው ይህም አይናችን ለከፋ ጉዳት ከመጋለጡ በፊት ህክምና እንድናደርግለት ይረዳናል። ከ40 አመት እድሜ በላይ ያሉ ሰዎች በአመት አንድ ጊዜ ወደ ሃኪም በመሄድ ምርመራን ማድረግ አለባቸው።

#የአይናችን #ውስጥ #ግፊት #ለምን #ይጨምራል?

🔘ግላውኮማ የሚከሰተው በአይናችን ውስጥ የሚገኘው ግፊት ሲጨምር ነው ያልን ሲሆን ይህደግሞ
👉በኢንፌክሽን
👉በአይን በቀዶ ጥገና ምክንያት በፊተኛው የአይናችን ውስጥ የሚገኘው ፈሳሽ በጤናማ ሁኔታ መንሸራሸር ሲያዳግተው ነው።
ግላውኮማ በአብዛኛው ሁለቱንም አይነቶች የሚያጠቃ ሲሁን የህመሙ ክብደት ግን ሊለያይ ይችላል።
#በግላውኮማ #የሚጠቁ #እነማን #ናቸው?

👉ከአርባ አመት እድሜ በላይ የሆኑ
👉በግላውኮማ የተጠቃ ቤተሰብ ያላቸው
👉የስኳር ህመምተኞች
👉የአይን ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች

#የግላውኮማ #ህመም #ምልክቶች #ምንድን #ናቸው?

🔘በአብዛኛው ግላውኮማ በቅድሚያ የህመም ምልክት ላያሳይ ቢችልም ከጊዜ በሗላ ግን የመጀመሪያ ምልክት የሚሆነው
በጥግ በኩል የሚጀምር የአይን ብርሃን ችግር ነው።
#ከምልክቶቹ #ውስጥ
👉ድንገተኛ የሆነ የአይን ህመም
👉ከፍተኛ የራስ ምታት
👉የአይን ብዥታ
👉ጥርት ያለ እይታ አለመኖር
👉የአይን መቅላት
👉የአይን ብርሃን ማጣት
👉የአይን እይታ ጥበት ናቸው
እነዚህ ሁኔታዎች ሲያጋጥምዎ በአፋጣኝ ወደ አይን ሀኪም መሄድ ይጠበቅቦታል።

#ግላውኮማን #መከላከል #ይቻላል?

🔘ግላውኮማ እንዳይከሰት መከላከል የማንችል ሲሆን ነገር ግን በቶሎ የህመሙ መኖር ከታወቀ ለመቆጣጠርና እንዳይባባስ ማድረግ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው።
በግላውኮማ ምክንያት የተከሰተ የአይን ብርሃን ጉዳት ተመልሶ ሊስተካከል የማይችል ሲሆን የነበረው ጉዳት እየተባባሰ እንዳይሄድ ግን የአይን ግፊት መጠኑን መቀነስ ይቻላል። ህክምናቸውን በሚገባ የሚከታተሉ ታካሚዎች የአይን ብርሃናቸውን ማዳን ይችላሉ።

#መልካም #ጤና
#ስትሮክ (Stroke)

#ስትሮክ በመባል የሚታወቀው የህመም አይነት በመላው ዓለም እንዲሁም በሀገራችን እጅግ እየተበራከተ የሚገኝ እና ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ የህመም አይነት ነው፡፡
ስትሮክ ሊከሰትባቸው የሚችሉባቸው መንገዶች ሁለት ናቸው እነዚህም

👉በጭንቅላት ውስ በሚከሰት የደደም መፍሰስ
👉ወደ ጭንቅላት ሊደርስ የሚገባው የደም ፍሰት መቀነስ ወይም መቋረጥ ናቸዉ
ስትሮክ ከተከሰተ በኋላ በአፈጣኝ ወደ ህክምና መውሰድ እና ህክምናውን ወዲያውኑ መውሰድ የታማሚውን ሊደርስበት የሚችለውን የጉዳት ክብደት መቀነስ እና የማገገም ሁኔታውን ሊፋጥን ይችላል፡፡
#ለበሽታው #ሚያጋልጡ #ሁኔታዎች
👉እድሜ፦በእድሜ በገፋን ቁጥር በስትሮክ የመጠቃት እድላችን ይጨምራል
👉ጾታ፦ስትሮክ በአብዛኛው በወንዶች ላይ እንደሚከሰት ጥናቶች ያመለክታሉ
በዘር ሊተላለፍ እንደሚችልም ጥናቶች ያመለክታሉ
👉የደም ግፊት መጨመር
👉የኮሌስትሮል መጠን መጨመር
👉ሲጋራ ማጤስ
👉በስኳር ህመም መያዝ
👉የሰውነት ክብደት መጨመር
👉ከዚህ ቀደም በስትሮክ መጠቃት
#የስትሮክ #ህመም #ምልክቶች
ስትሮክ በተከሰተ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ የአንጎል ህዋሶች መሞት ይጀምራሉ ይህም የሚከተሉትን አይነት ምልክቶች ያስከትላል
👉ለመራመድ መቸገር ወይም ሚዛን አለመጠበቅ
👉ለመነጋገር መቸገር
👉የሰውነት ክፍል (እጅ ወይንም እግር) ያለመታዘዝ
👉የአይን ብዥታ
👉ድንገተኛ የሆነ ከፍተኛ የራስ ምታት
👉ግራ የመጋባት ስሜት
ከላይ የተጠቀሱትን ምልክቶች በአቅራቢያው በሚገኘው ሰው ከተመለከቱ አፋጣኝ እርዳታ እንዲያገኝ ማድረግ ተገቢ ነው።
#ስትሮክን #የመከላከያ #መንገዶች
የመጀመሪያ እና ቀዳሚው የመከላከያ መንገድ ስለበሽታው ምንነት እና ስለሚያስከትለው ጉዳት ማወቅ ነው፡፡
ስትሮክን የመከላከያ መንገዶች ከእለት ተእለት የአኗኗር ሁኔታችን ጋር የተያያዘ ነው፡፡
👉የደም ግፊት መጠናችንን ማወቅ እና የደም ግፊታችን ከፍተኛ ከሆነም በሚገባ ለመቆጣጠር መሞከር፡፡ የደም ግፊት መድሃኒት የምንወስድም ከሆነ በትክክል እና ያለማቋረጥ መውሰድ፡፡
👉 የስኳር ህመም ተጠቂ ከሆኑ የስኳር መጠኖን መቆጣጠር
👉 ጭንቀትን ማስወገድ
👉ሲጋራ አለማጤስ
👉 የአልኮል መጠናቸው ከፍተኛ የሆኑ መጠጦችን አለመውሰድ
👉የምንጠቀመውን የጨው መጠን መቀነስ
👉ቅባት የበዛባቸውን ምግቦች ያለማዘውተር
👉በቀን ለ 30 ደቂቃ ያህል የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ወይም የእግር መንገድ መሄድ
👉 የሰውነት ክብደትን መቀነስ ናቸዉ።
መረጃዉ ከተመቾት ላይክ 👍 ማረጎን አይርሱ

#መልካም #ጤና