መኀደረ ጤና
2.6K subscribers
36 photos
13 videos
6 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩╩═╝
ስለ ጤናዎ ወሳኝ መረጃዎች💊 ሁሉም ሰው ሊያውቃቸው የሚገባ የጤና መረጃዎችን ከፈለጉ ይህን ቻናል ይቀላቀሉ ይማሩበታል ያስተምሩበታል መልካም ጤና ለሁላችን..


መልካም ጤና ለሁላችን..
Download Telegram
#ማንኮራፋት

#ማንኮራፋት የምንለው በምንተኛበት ጊዜ በመተንፈሻ አካላችን ላይ በሚፈጠሩ ለውጦች ምክንያት በሚመጣ ድምፅ ነው። #ማንኮራፋት አብሮ የሚተኛን ሰው ከመረበሽ ባለፈ አንዳንድ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ የጤና እክሎች ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡
#ለማንኮራፋት #ተጋላጭነት #የሚዳርጉ #ሁኔታዎች
👉የሰውንት ክብደት መጨመር
በተፈጥሮ የሚኖር ጠባብ መተንፈሻ አየር የምናስገባበት አካል መጥበብ የምንስበው አየር ግፊት እንዲጨምር በማድረግ ድምፅን ይፈጥራል
👉አልኮል መጠጥ ማብዛት
የአልኮል መጠጥ የጉሮሮ ጡንቻዎችን በማፍታታት አየር በሚገባበት ወቅት ርግብግቢት በመፍጠር ድምፅ እንዲጨመር ያደርጋል
👉በአፍንጫ ላይ የሚከሰቱ ችግሮች
በአፍንጫ ላይ የሚኖሩ ተፈጥሮአዊ የአቀማመጥ ችግሮች የማንኮራፋት ዕድልን በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራሉ
#ማናኮራፋት #የሚያስከትላቸው #ችግሮች
👉ቀን ቀን የእንቅልፍ ስሜት መሰማት
👉ብስጭትና ንዴት
👉ለነገሮች ትኩረት ማጣት
👉ለደም ግፊትና ለልብ ሕመም ማጋለጥ
👉በእንቅልፍ እጦት ምክንያት ለሰው ሠራሽ አደጋዎች መጋለጥ
👉የትዳር አጋርን እንቅልፍ ማሳጣት ናቸው፡፡
#የሚያንኮራፉ #ሰዎች
▪️በእንቅልፍ ጊዜ የሚረብሽ ድምፅ ያሰማሉ
▪️የቀን እንቅልፍ ሊያስቸግራቸው ይችላል
▪️የጉሮሮ መከርከር ይኖርባቸዋል
▪️ሰላም የሌለው እንቅልፍ ያስቸግራቸዋል
▪️በእንቅለፍ ጊዜ ትንታ እና ትንፋሽ ማጠር ያጠቃቸዋል
▪️የደረት መጨምደድና የደም ግፊት ሊኖራቸው ይችላል፡፡
#ማንኮራፋትን #የምንከላከልባቸው #መንገዶች
👉አስተኛኘትዎን ያስተካክሉ
👉በጀርባዎ መተኛት ምክንያት እና ለስላሳ ላንቃዎን ወደ ጉሮሮ እንዲወርዱ ስለሚያደርግ በእንቅልፍ ጊዜ የመርገብገብ ድምፅን እንዳናሰማ ያደርጋል፡፡
👉ስለዚህ በጎን መተኛት መፍትሔ ሊሆን ይችላል፡፡
👉የሰውነት ክብደትዎን ይቀንሱ
የሰውነት ክብደት የሌላቸው ሰዎችም ቢሆኑ ያንኮራፋሉ፡፡ ነገር ግን ማንኮራፋቱ የመጣው የሰውንት ክብደት ከጨመረ በኋላ ከሆነ መንስዔው ሊሆን ስለሚችል ክብደትዎን ይቀንሱ፡፡
👉የአልኮል መጠጥ አይውሰዱ
የአልኮል መጠጥ የምንወስድ ከሆነ በጉሮሮ አካባቢ የሚገኙ ጡንቻዎችን ስለምናፍታታ ማንኮራፋት እንጀምራለን፡፡ ከመተኛታችን በፊት ባለው ከ4 – 5 ሰዓት ጊዜ ውስጥ አልኮል መጠጥን መውሰድ ማናኮራፋትን ያባብሳል፡፡
👉የእንቅልፍ ሰዓትዎን ያስተካክሉ
ለረጅም ሰዓታት ያለዕረፍት የሚሠሩ ከሆነ እና በመጨረሻ እጅግ በጣም እራስዎን ካዳከሙ በኋላ የሚተኙ ከሆነ የጉሮሮ ጡንቻዎች ባጣም ስለሚፈታቱ የማንኮራፋት ድምፅ ያሰማሉ፡፡
👉አፍንጫዎን ከመደፈን ይከላከሉ
አፍንጫዎ በቅዝቃዜም ሆነ በአለርጂ ምክንያት ከተደፈነ የማንኮራፋት ዕድልን ሰለሚጨምር ከመተኛትዎ በፊት በሙቅ ውሃ ገላን መታጠብ በተጨማሪ ውሃ በጨው በማድረግ አፍንጫን ማፅዳት፡፡ ይህ የአፍንጫን ቀዳዳዎች ስለሚከፍት ማንኮራፋትን ይከላከላል፡፡
👉ትራሰዎን ይቀይሩ
በትራስዎ ውስጥ በዓይን የማይታዩ ብናኞች ተከማችተው ሊገኙ ስለሚችሉ መቀየር ተገቢ ነው፡፡
👉ፈሳሽ በብዛት ይውሰዱ
ፈሳሽን በብዛት መውሰድ ከአፍንጫችን የሚመነጨውን ፈሳሽ ሰለሚያቀጥን ማነኮራፋት እንዳይኖር ይረዳል፡፡

#መልካም #ጤና