ለምን አልሰለምኩም?
3.01K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
🔵 ቁርኣን = ዝብርቅርቅ መጽሐፍ

በስነጽሑፍ ረገድ ቁርአን ከሞላ ጎደል የተረከው ታሪክ በመጽሐፍ ቅዱስ ከኦሪት ዘፍጥረት መጽሐፍ ሙሉ ታሪኩን ከምናገኘው ዮሴፍ በስተቀር የአንድን ርዕሰ ጉዳይ #መነሻና_ፍጻሜ_የሚያብራ_የአጻጻፍ_ስርዓት_የለውም፡፡ ከአንድ ጉዳይ ወደ ሌላው፣ ከአንድ ዘመን ወደ ሌላው፣ ከአንዱ ቤተሰብ ወደ ሌላው፣ በማጣቀስ የተደራጀ መጽሐፍ ነው፡፡ ከመጥምቁ ዮሐንሰ ጀምሮ ወደ ሙሴ ይመለሳል፡፡ ስለ አብርሃም ጀምሮ ስለማይታወቅ ጉዳይ ይተርካል፡፡

📌ቁርአን ራሱን እንኳ አያብራራም፡፡ የመልዕክት ቅደም ተከተል የለውም፡፡ ከአንድ ሀሳብ ወደ ሌላው ሲዘልቅ የቋንቋን ስርዓት በጠበቀ መንገድ የማያያዣ ቃላትን (መስተዋድድና መስተፃምር) አይጠቀምም ግስና ስምን እያመሳቀለ ግራ የሚያጋባ ድግግሞሽ የበዛበት ስለሆነ ማንም ሰው በቀላሉ ሊረዳው አይችልም፡፡ 👉የቁርአን ሊቃውንት እንኳን ሃያ ከመቶውን ወይም አንድ አምስተኛውን ያህል አልተረዱትም፡፡

🔴 በርካታ ሙስሊሞች ቁርአን አይነኬ፣ አይጠየቄ፣ አይደፈሬ፣ ተደርጎ ስለተነገራቸው ብቻ በጭፍን ድንቅነቱን ይናገራሉ እንጂ በአግባቡ ያልተረዱት መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ከአረብኛው ቋንቋ ውጪ የተተረጐሙትን ቁርአኖች ሙሉ ተቀባይነት ስለሌላቸው የአረብኛን ቋንቋ በከፍተኛ ዕውቀት ደረጃ ያልተረዱት ተከታዮቹ አያውቁትም፡፡ እናውቀዋለን የሚሉትም ለራሱ ለቁርአን ማብራሪያ የተዘጋጁትን መጽሐፍቶች ከመቀበል ውጪ መተርጎምም መጠየቅም መተቸት አይፈቀድላቸውም፡፡
👍1