ለምን አልሰለምኩም?
2.91K subscribers
51 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
ወዶ አይስቁ! አሉ አበው

ተመልሸ እንደምመጣ ቃል በገባሁት መሠረት ተመልሻለሁ፤ ኡስታዝ አቡ ሀይደር እንዲህ ዐይነት ጥያቄ የሚያነሱት አለ፡-
 ይህንን ጥያቄ የሚያነሱ ወገኖች ጥያቄውን ያነሱት በጋብቻና በዝሙት መካከል ያለውን ልዩነት ለይቶ ካለማወቅ የመነጨ ነው

በእውነቱ ምኑ ይሆን ጥያቄውን የእውቀት አጠሮች ጥያቄ የሚያስመስለው? መጽሐፍ ቅዱስ አታመንዝር ብሎ ሲያዝ ምንዝርና ወይም ዝሙት ምን ማለት እንደሆነ እና መቼ ሰው አመነዘረ እንደሚባል ገደቡንና ትርጉሙን አስተምሮ ነው፡፡ ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረውን ማስነበቡ የተሻለ ይመስለኛል፡-

የማቴ 5 ፡ 27-32

አታመንዝር እንደ ተባለ ሰምታችኋል። እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ወደ ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመንዝሮአል። ቀኝ እጅህም ብታሰናክልህ ቆርጠህ ከአንተ ጣላት፤ ሙሉ ሰውነትህ በገሃነም ከሚጣል ይልቅ ከአካላትህ አንድ ቢጠፋ ይሻላልና። ሚስቱን የሚፈታት ሁሉ የፍችዋን ጽሕፈት ይስጣት ተባለ። እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ያለ ዝሙት ምክንያት ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ አመንዝራ ያደርጋታል፥ የተፈታችውንም የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል።

በዝሙትና በጋብቻ መካከል ያለውን ልዩነት በትክክል የማያውቀው ራሱ ኡስታዝ አቡ ሀይደርና መላው የኢስላም ሊቃውንት እንጂ 'ዝሙት በጀነት እንዴት ሊኖር ቻለ?' በማለት ጥያቄ ያነሱት ወገኖች ሊሆኑ አይችሉም፡፡ ልዩነቱ በትክክል ስለሚታወቅ ነው ጥያቄው ሊነሳ የቻለው፡፡ ለአቡ ሀይደር፣ ለመላው ሙስሊም፣ ለአላህ የእዝነቱ ነቢይ የልጃቸውን ሚስት አፋትተው ሲያገቡ 'ጋብቻ' ይሉታል፡፡ ለዚህ 'ትዳርም' በቁርአንና በሐዲስ ብዙ ተዘፍኖለት እንመለከታለን፡-

ይኑስ ቢን አብድ አል-አላህ ኢብን ዋሃብ ኢብን ዛይድ እንደተናገረው፡- የአላህ መልእክተኛ የአክስታቸውን ልጅ ዘይነብ ቢንት ጃሃሽን ለዛይድ ቢን ሃሪሳ አጋቡት፡፡ ከእለታት አንድ ቀን የአላህ መልእክተኛ ዛይድን ፍለጋ ወጥተው ሄዱ፡፡ ያኔ የቤቱ በር በጸጉር መሸፈኛ ሻሽ ተጋርዶ ነበር፡፡ ነገር ግን ነፋስ መጋረጃውን ሲያነሳው ክፍት ሆነ፡፡ ዘይነብ ክፍሏ ውስጥ ራቁቷን ነበረች፤ ስለ እርሷ አድናቆት ወደ ነቢዩ ልብ ሰንጥቆ ገባ፡፡ ይህ ከሆነ በኋላ ለሌላ ወንድ ክልክል ሆነች፡፡ እርሱም መጣና እንዲህ አለ፡- የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ከሚስቴ ጋር መለያየት እፈልጋለሁ፡፡ እርሳቸውም ጠየቁት፡- ችግሩ ምንድን ነው? በእርሷ በኩል እረፍት የነሳህ ነገር አለን? በአላህ የለም ሲል ዛይድ መለሰ ከመልካም ነገር በስተቀር ምንም አላየሁም፡፡ የአላህ መልእክተኛም እንዲህ አሉት፡- "አላህን ፍራ ሚስትህን አትፍታ፤ ያ የአላህ ቃል ነው፡- ለእዚያም አላህ በእርሱ ላይ ለለገሰለትና (አንተም ነጻ በማውጣት) በእርሱ ላይ ለለገስክለት ሰው (ለዘይድ) አላህ ገላጩ የሆነን ነገር በነፍስህ ውስጥ የምትደብቅና አላህ ልትፈራው ይልቅ የተገባው ሲሆን ሰዎችን የምትፈራ ሆነህ «ሚስትህን ባንተ ዘንድ ያዝ፤ (ከመፍታት) አላህንም ፍራ» በምትል ጊዜ (አስታውስ)፡፡" እንዲህ የሚለውን ሐሳብህን ደብቀሃል፡- ዛይድ በራሱ ከእርሷ ጋር ከተፋታ አገባታለሁ፡፡ (Tarik At-Tabari vol 8, page 4)

ለምን ይሆን ዘይድ 'ሚስቴን መፍታት እፈልጋለሁ' ያለው? ነቢዩ ስላፈቀሯት ዘይነብ ለዘይድ ሚስትነት ወደ እናትነት ስለተቀየረች ነበር፡፡ ይህም ለአቡ ሀይደር፣ ለሙስሊሞች፣ ለአላህ፣ለእዝነቱ ነቢይ 'ጋብቻ' 'ትዳር' እንጂ ጸያፉ ዝሙት አይደለም አይደል?

"I.e., God caused her to become unattractive to her husband Zayd." (Cf. Stowasser, Women in the Qur'an, Traditions, and Interpretation, 88) ‘Tabari embroiders the story; he quotes traditions that indicate when the Prophet approached Zayd's and Zaynab's house on this visit, Zaynab was wearing but a single slip; at the house entrance was a curtain made of pelts, and when the wind lifted this curtain, it revealed the sight of Zaynab, "uncovered" in her chamber. It was then, says Tabari, that the Prophet began to feel a liking for Zaynab. Thereafter, Zaynab "was made unattractive to the other" (i.e., by God)’

በነቢዩ በር ላይ ሴቶች ራሳቸውን በፈቃዳቸው ለማስደፈር (ግብረ ሥጋ ግንኙነት ለማድረግ) ተሰልፈው ማየት የተለመደ ነበር ቁርአንም ሐዲሳቱም ያሳብቃሉ፡፡ እናም ከነዛ ቁጥራቸው በውል ከማይቆጠር ካላገቧቸው ራሳቸውን ለማስደፈር ከመጡ የትየለሌ ሴቶች ጋር ነቢዩ የሚፈጽሙት ወሲብ ለአቡ ሀይደርና ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ ብሎም ለአላህ እና ለነቢዩ ሙሐመድ የተፈቀደ "ጋብቻ" እንጂ ዝሙት አይደለም፡፡ ወዶ አይስቁ! አይ አቡ ሀይደር፡-

ሱረቱል አል-አሕዛብ 33 ፡ 50-51

አንተ ነቢዩ ሆይ! እኛ እነዚያን መህሮቻቸውን የሰጠሃቸውን ሚስቶችህን፣ አላህ ባንተ ላይ ከመለሰልህም እነዚያን እጅህ የጨበጠቻቸውን ምርኮኞች፣ እነዚያንም ከአንተ ጋር የተሰደዱትን የአጎትህን ሴቶች ልጆች፣ የአክስቶችህንም ሴቶች ልጆች፣ የየሹማህንም ሴቶች ልጆች፣ የየሹሜዎችህንም ሴቶች ልጆች (ማግባትን) ለአንተ ፈቅደንልሃል፡፡ የአመነችንም ሴት ነፍሷን (ራሷን) ለነቢዩ ብትሰጥ ነቢዩ ሊያገባት የፈለገ እንደ ኾነ ከምእምናን ሌላ ላንተ ብቻ የጠራች ስትኾን (ፈቀድንልህ)፡፡ በእነርሱ (በምእምናን) ላይ በሚስቶቻቸውና እጆቻቸው በጨበጧቸው (ባሮች ነገር) ግዴታ ያደረግንባቸውን በእርግጥ ዐውቀናል፡፡ ባንተ ላይ ችግር እንዳይኖር (ያለፉትን ፈቀድንልህ)፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ ከእነርሱ የምትሻትን ታቆያለህ፡፡ የምትሻውንም ወደ አንተ ታስጠጋለህ፡፡ (በመፍታት) ከአራቅሃትም የፈለግሃትን (በመመለስ ብታስጠጋ) በአንተ ላይ ኀጢአት የለብህም፡፡ ይህ ዓይኖቻቸው ወደ መርጋት፣ ወደ አለማዘናቸውም፣ ለሁሉም በሰጠሃቸው ነገር ወደ መውደዳቸውም በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህም በልቦቻችሁ ውስጥ ያለውን ሁሉ ያውቃል፡፡ አላህም ዐዋቂ ታጋሽ ነው፡፡

ወይ አላህ! ምን ዐይነት አምላክ ነው? አይቀፈውም? ለአይሻ እና ለእርሷን መሰል ሴቶች ግን ይህ ድርጊት አስገራሚና ጸያፍ ተግባር ነበር፡-

ሳሂህ ሙስሊም ቅጽ 4፤ ቁ 3631
ሱና አን-ናሳኢ ቅጽ 4፤ ቁ 3201

አኢሻ እንዲህ አለች፡- "‘ራሳቸውን በፈቃደኝነት ለነቢዩ በሚሰጡ ሴቶች ቅንአት ተሰማኝ፤ እናም ነጻ ሴት ራሷን ለወሲብ ታቀርባለችን? ብዬ ተናገርኩ፡፡’ ከዛም ኃያሉ አላህ ‘ከእነርሱ የምትሻትን ታቆያለህ፡፡ የምትሻውንም ወደ አንተ ታስጠጋለህ፡፡ (በመፍታት) ከአራቅሃትም የፈለግሃትን (በመመለስ ብታስጠጋ) በአንተ ላይ ኀጢአት የለብህም፡፡’ የሚለውን አንቀጽ አወረደ፡፡ እኔም እንዲህ አልኩ፡- ‘በአላህ! ጌታህ የአንተን መሻት ለመመለስ ፈጣን እንደሆነ አየሁ፡፡’"
ሳሂህ ሙስሊም መጽሐፍ 8፣ ሀ.ቁ 3354
ምዕራፉ፡- በሦስት የፍች ቃላት (ፈታሁሽ፣ ፈታሁሽ፣ ፈታሁሽ) ተብላ የተፈታችን ሴት ለሌላ ወንድ ተድራ እርሱም ከእርሷ ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት ፈጽሞ ሳይፈታትና ኢዳዋን ሳትጨርስ መልሶ ማግባት የተከለከለ ስለመሆኑ፡-
አይሻ እንዳወራችው የሪፈአ ሚስት ወደ አላህ መልእክተኛ መጣችና እንዲህ አለች፡- ሪፈአን አግብቸ ነበር፤ ነገር ግን ፈታኝ፡፡ የፈታኝም በሦስት የፍች ቃላት ነው፡፡ ከዛ በኋላ አብድ አል-ረህማን ቢን አል-ዙበይርን አገባሁ፤ ነገር ግን እርሱ ያለው እንደ ልብስ ዘርፍ ይመስላል (ስንፈተ ወሲብ አለበት ማለቷ ነው)፡፡ ከዚያ በኋላ የአላህ መልእክተኛ ሳቁና እንዲህ አሉ፡- ወደ ፊፈአ መመለስ ፈልገሽ ነው? አብድ አል-ረህማን የአንችን ጥፍጥና ሳይቀምስ አንችም የእርሱን ጥፍጥና ካልቀመስሽ በስተቀር መመለስ አትችይም፡፡

ይህ በሸሪአው በማይለወጥ ሦስት የፍች ቃላት የተፋቱ ባልና ሚስት እንደገና ወደ ጥምረታቸው መመለስ ቢፈልጉ ማድረግ ስለሚገባቸው ተግባር የሚደነግግ ሕግ ነው፡፡ በኢስላም ድንገት በተነሳ አለመግባባት ሊሆን ይችላል በምንም ምክንያት ፍች ቢፈጸም እንደገና ተጋብተው መኖር ከፈለጉ ሴቷ ሌላ ወንድ 'አግብታ' ካገባችው ሰው ጋር ወሲብ ከፈጸመች በኋላ እርሱ ይፈታትና ነው ወደ መጀመሪያው ባሏ የምትመለሰው፡፡ ከሌላኛው ወንድ ጋር (ወንዱ የሰፈር ሽማግሌ፣ በመስጊድ ያለ ኢማም ሊሆን ይችላል ወይም ገንዘብ ተከፍሎት ይህንን አገልግሎት በሚሰጥ ሙስሊም ወንድ ሊሆን ይችላል) 'ጋብቻው' የሚፈጸመው እንደ መደሰቻ ጋብቻ ለሰዓታት፣ ለአንድ ቀን አዳር ሊሆን ይችላል፡፡ ከዛ ትፈታ እና ወደ ባሏ መጥታ ይጋባሉ፡፡ እስኪ በሞቴ አንዴ በዚህ ጫማ ራስዎትን ያስገቡና ይመልከቱት፤ ይቀበሉታል ይጸየፉታል? ውስጠዎት ምን አለ? ምን ዐይነት ጋብቻ ወይም ትዳር ተብሎ ይጠራ?

በለንደን እንዲህ ዐይነት ችግር የገጠማቸው ሙስሊም ሴቶች ባላቸውን እንደገና ለማግባት 2500 ፓውንድ በመክፈል መስጊድ ውስጥ ለሚገኙ 'ሃላል ሰርቪስ' ይሉታ ለሚሠሩ ወንዶች ለደቂቃዎች ራሳቸውን አስደፍረው ወደ ባሎቻቸው ይመለሳሉ፡፡ ባሎቻቸውም ይቀበሏቸዋል፡፡ በአገራችንም እየተፈጸመ የሚገኝ ኢስላማዊ ተግባር ነው፡፡ አሁን አሁን የለንደኖቹ ሙስሊም ሴቶች ይህንን አጸያፊ ተግባር እጅግ አድርገው ጠልተውት ባሉካን ጥንቅር ብለህ ቅር እያሉ ይገኛሉ፡፡ የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑና ስለ ጉዳዩ የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ https://www.bbc.com/news/uk-39480846.

ብዙ ለቁጥር የሚታክቱ ኢስላማዊ ማሳያዎችን ማምጣት ይቻላል፡፡ ይህ ነው እንግዲህ የነ አቡ ሀይደር ኢስላምና ጋብቻ፣ ጋብቻና ዝሙትን አብጠርጥሮ የማወቅ የዕውቀት ጥግ፡፡ ድንቄም ዕውቀት! ለአቡ ሀይደርና ለመላው ሙስሊም እንዲሁም ለአላህና ለእዝነቱ ነቢይ እነዚህ ድርጊቶች ጸያፍ የዝሙት ተግባራት ሳይሆኑ የአላህ ፈቃድ የተቸረው የነቢዩ ሱናዊ 'ሃላል ትዳር' 'ሃላል ጋብቻ' ናቸው፡፡ እንዲህ ዐይነት ጋብቻዎችን መፈጸም መርከስ ማርከስም እንጂ በየትኛውም የሕግ መለኪያ ሕጋዊ ሊባሉ አይችሉም፡፡ ሃይማኖተኛ ለሆነ አይደለም በስነ ምግባር መርህ ለሚመራ ሰው እንኳን አጸያፊ ተግባራት ናቸው፡፡ ዝሙት ከሚባለውም በላይ ናቸው፡፡
ቅዱሱ የአምላኬ ቃል ግን እንዲህ በእጅጉ ልዩ ነው፤ ሁሉንም በዬ ስማቸው ሳያዛባ ይጠራቸዋል፡፡ ሕዝቦቹንም ከከለከለው ታቅበው የተፈቀደውንም በአግባቡ እንዲፈጽሙ ያዛል ፈቃዱንም ይገልጣል፡፡ ለምሳሌ ስለ ፍች አምላካችን በብሉዩም ጊዜ እንኳን መፋታትን እጠላለሁ ነበር ያለው፡-

ትንቢተ ሚልክያስ 2፥16

መፋታትን እጠላለሁ፥ ይላል የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር፥ ልብሱንም በግፍ ሥራ የሚከድነውን ሰው እጠላለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ስለዚህ እንዳታታልሉ መንፈሳችሁን ጠብቁ።

ምናልባት ከተፋቱም ለተፋቱት ባለ ትዳሮች ገዥ ሕግ እንዲህ የነበረው የሚለው ነበር፡-

ኦሪት ዘዳግም 24 ፡ 1-4

ሰው ሴትን ወስዶ ቢያገባ፥ የእፍረት ነገር ስላገኘባት በእርሱ ዘንድ ሞገስ ባታገኝ፥ የፍችዋን ጽሕፈት ጽፎ በእጅዋ ይስጣት፥ ከቤቱም ይስደዳት። ከቤቱም ከወጣች በኋላ ሌላ ወንድ ብታገባ፥ ሁለተኛውም ባል ቢጠላት፥ የፍችዋንም ጽሕፈት ጽፎ በእጅዋ ቢሰጣት፥ ከቤቱም ቢሰድዳት፥ ወይም ሚስት አድርጎ ያገባት ሁለተኛው ባልዋ ቢሞት፥ የሰደዳት የቀድሞ ባልዋ ከረከሰች በኋላ ደግሞ ያገባት ዘንድ አይገባውም፤ ያ በእግዚአብሔር የተጠላ ነው፤ አምላክህም እግዚአብሔር ርስት አድርጎ የሰጠህን ምድር አታርክስ።

ነገሩን በአንባቢዎቼ ወደ ብይን መስጫ ሳጥን ውስጥ ላስገባው ፤ እውን ዝሙት በጀነት እንዴት ሊኖር ቻለ? በማለት ጥያቄ ያቀረቡ ወገኖች ጥያቄያቸውን ያቀረቡት ስለ ዝሙትና ጋብቻ እውቀጥ ስላጠራቸው ነውን? ከጠያቂዎቹና ከተጠያቂዎቹ ከነ አቡ ሀይደር ወገን ማን ነው በዝሙትና በጋብቻ መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት የተሳነው? አቡ ሀይደርና መላው ሙስሊም እንዲሁም አላህና ነቢዩ ሙሐመድ ወይስ ዝሙት በጀነት እንዴት ሊሆን ቻለ? ብለው የጠየቁ? ለዚህ ነው ወዶ አይስቁ! ማለቴ፡፡

ይህ ነቢዩ ሙሐመድም ሆኑ ቁርአን ከአምላክ የተላኩ ያለመሆናቸው አንዱ ማሳያ ይኸው ነው፡፡

ሳሂህ ኢማን ነኝ!

አልጨረስኩም ተመልሸ እመጣለሁ በሰላም ቆዩኝ!
እየገረመኝ፣ እየተደመምኩ፣ አንዳንዴም 'ወዶ አይሰቁ' አሉ እየሳቅሁ እቀጥላለሁ፡፡ ሱረቱል አል-ኒሳዕ አንቀጽ 24 ም ለአቡ ሀይደርና ለሁሉም ሙስሊም፣ ለአላህና ለነቢዩ ሙሐመድ 'ጋብቻ' 'ትዳር' እንጂ ጸያፉ ዝሙት አይደለም፡፡ ስለዚህ አንቀጽ አስባብ ወይም ስለ ወረደበት ምክንያት ባስነብባችሁ አንዳንዶቻችሁ ልታስመልሱ ስለምትችሉ ትቸዋለሁ፡፡ በሙስሊም ጦረኞች ተማርከው ለባርነት የሚዳረጉ ሴቶች የሚደርስባቸውን የወሲብ ባርነትማ ልነግራችሁ አልችልም፡፡ ለማንኛውም አንቀጹ የሚያወራለት ጋብቻ ሙተአህ (የመደሰቻ ጋብቻ) (የኮንትራት ጋብቻ) ተብሎ ይታወቃል፡-

ሱራ 4 ፡ 24

ከሴቶችም (በባል) ጥብቆቹ እጆቻቸሁ (በምርኮ) የያዙዋቸው ሲቀሩ በእናንተ ላይ እርም ናቸው፡፡ (ይህን) አላህ በናንተ ላይ ጻፈ፡፡ ከዚሃችሁም (ከተከለከሉት) ወዲያ ጥብቆች ኾናችሁ ዝሙተኞች ሳትኾኑ በገንዘቦቻችሁ ልትፈልጉ ለእናንተ ተፈቀደ፡፡ ከእነሱም በርሱ (በመገናኘት) የተጠቀማችሁባቸውን ሴቶች መህሮቻቸውን ግዴታ ሲኾን ስጧቸው፡፡ ከመወሰንም በኋላ በተዋደዳችሁበት ነገር በእናንተ ላይ ኀጢአት የለም፡፡ አላህ ዐዋቂ ጥበበኛ ነውና፡፡

"በገንዘቦቻችሁ ልትፈልጉ" የሚለውን ኢብን አባስ ሲፈታው "it is also said that this means: so that you should seek with your money marrying women for an agreed period of time (zawaj al-mut'ah)" ብሎታል፡፡

ምን ማለት ነው? ትሉ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ጉዳይ በመጠኑም ቢሆን የተብራራ መረጃ "ድብቁ እውነት ሲገለጥ" የተሰኘው መጽሐፍ ውስጥ ከገጽ 135 ጀምሮ ታገኛላችሁ፡፡ በ pdf "JOSHUA EVANGELICAL ARMY (( ኢያሱ የወንጌል ስራዊት))" FB group ላይ ተለቋል እዛ ታገኙታላችሁ፡፡ ለዚህ ጽሁፍ ይሆናል ያልኩትን ግን ላስነብባችሁ፤ "ሙተአህ"

"ሙጃህዲን እንደገለጸው ‘ከእነሱም በርሱ (በመገናኘት) የተጠቀማችሁባቸውን ሴቶች መህሮቻቸውን ግዴታ ሲኾን ስጧቸው’ የሚለው የወረደው ስለ ሙተአህ (መደሰቻ) ጋብቻ ነው፡፡ ሙተአህ (የመደሰቻ) ጋብቻ አስቀድሞ በስምምነት በተወሰነ ቀን የሚያበቃ ጋብቻ ነው፡፡ (Tafsir ibn kathir vol 2 page 423-424)

ሳሂህ ሙስሊም ቅጽ 4፣ ቁ 3413

ጃብር ቢን አብዱላህና ሰላማ ቢን አል-አክዋ ሲናገሩ እንዲህ አሉ፤ የነቢዩ አፈ ቀላጤዎች ወደእኛ መጥተው የአላህ መልእክተኛ 'ከሴቶች ጋር የመደሰቻ ጋብቻ' በማድረግ እራሳችሁን እንድታስደስቱ ፈቅደዋል አሉን፡፡

በስምምነት የተወሰነው ጊዜ ማለት ምን ማለት ነው? ጊዜውስ እስከ ምን ያህል ሊሆን ይችላል? ለሚለው ሙተአህ ጋብቻን በተመለከተ ከሙስሊም ምእመናን የተጠየቀን ጥያቄ ኢስላማዊ መምህራን እንዴት ምላሽ እንደሰጡ ላስነብባችሁ፡-

"አንደኛ ጥያቄ፤ አንድ ሰው የመደሰቻ ጋብቻን 'ለአንድ ሰዓት' መዋዋል ይችላልን? መልስ፡- በመርህ ደረጃ 'አዎን' እላለሁ፤ በተመሳሳይ መንገድ አንድ በቋሚ ጋብቻ ሚስት ያገባ ሰው በአንድ ሰዓት ውስጥ እንዲያውም ከዛ ባነሰ ጊዜ ውስጥ ሊፈታት ይችላል፡፡ በተግባር በዚህ መልኩ ቋሚ ጋብቻን የማፍረሱ አጋጣሚ የለውም፤ ስለዚህ በመደሰቻ ወይንም በጊዜያዊ ጋብቻም ውስጥ አይተገበርም፡፡ (Ahlul Bayt Digital Islamic Library Project Team [3], A Shi'ite Encyclopedia, temporary-marriage-islampart-8, Ahlul Bayt Digital Islamic Library Project [4], www.al-islam.org)

በመደሰቻ ጋብቻ የሴቶቹ ቁጥር ምን ያክል ሊሆን እንደሚች እንዲሁም የሙስሊም ጦረኞች የማረኳቸውና ባሪያ ያደረጓቸው ምስኪን ምርኮኛ ሴቶች በኢስላም እንደ ሰው ሳይቆጠሩ በሙስሊም ወንዶች የሚደርስባቸውን ወሲባዊ ጥቃት ወደር የሌለው መሆኑን በጨረፍታ ላሳነብባችሁ፡-

"ጥያቄ ሰባት፡- አንድ ወንድ አራት ጊዜያዊ (የመደሰቻ) ሚስቶች ወይም ቋሚ ሚስቶች እያሉት 'ተጨማሪ የመደሰቻ ጋብቻ ሚስት' መዋዋል ይችላልን? መልስ፡- 'አዎን፤' ይህን በተመለከተ በጊዜያዊ (በመደሰቻ) ጋብቻ የተገባች ሴት ጉዳይ፣ በእስልምና 'ከሴት ባሪያ ጉዳይ ጋር ተመሳሳይ ነው'፡፡ ሁሉም ሙስሊሞች እንደሚስማሙት አንድ ሙስሊም በቁጥር ሳይገደብ የፈለገውን ያክል ባሪያ ልጃገረዶችን እንዲያገባ ይፈቀዳል፡፡ እስልምና በቋሚ ጋብቻ ገደብን እንደሚያስቀምጠው በዚህ ላይ ገደብን አላስቀመጠም፡፡" (A Shi'ite Encyclopedia, temporary-marriage-islam-part-8)

ይህ እንግዲህ ለአላህና ለነቢዩ ሙሐመድ፣ ለአቡ ሀይደርና ለመላው ሙስሊም 'ጋብቻ' እንጂ ዝሙት አይደለም፡፡ ይገርምልሻል አለ አንድ ወዳጄ! የባሰውንና አቡ ሀይደርም ሆነ መላው የኢስላም ሊቃውንት እንዲሁም አላህና ነቢዩ በዝሙትና በጋብቻ መካከል ያለውን ልዩነት እንደማያውቁ የሚያሳየውን ነጥብ ልጨምርላችሁ፡፡ አንድ የታብሊግ ጀምአቲ ምሑር ሙተአህን (ጊዜያዊ ጋብቻን) 'የመተዳደሪያ ሥራ' ስለ ማድረግ ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ እንዲህ የሚል ነው፡-

"ጊዜያዊ ጋብቻን መተዳደሪያ ስለማድረግ፡- ጥያቄ፡- አንድ ሴት በመደሰቻ ጋብቻ አንድን ወንድ ብታገባ፣ መኸሯን ብትወስድ ከዛም ኢዳዋን ብትፈጽም፣ እንደገና 'ለአጭር ጊዜ' ሌላ ወንድ ብታገባ፣ እንዲህ እንዲህ እያደረገች በዓመት ከግማሽ ደርዘን ወንዶች ጋር ብታገባና 'መተዳደሪያዋ ብታደርግ' ሃራም ነውን? የጊዜያዊ ጋብቻ መርህ የሚደነግገውን እንከፈጸመች 'ሃራም የሚያደርገው ምንድን ነው?' ሃራም ካልሆነ ደግሞ እንደ ኀጢአተኛ ልትወገዝ ይገባልን? መልስ፡- በሚገባ የሻሪአውን ህግጋቶች ከተከተለች በዚህ መንገድ 'መተዳደሪያዋ ብታደርግ ሃራም አይደለም፡፡' ልትኮነንም አይገባም፡፡ ይህ እርሷን በሚያገቡ ወንዶችም ላይ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡" (Ali Rashid, copyright TAbligh Sub-committee, 2002. http://daiichicorp.com)

በለው! ይህ ነው እንግዲህ ኡስታዝ አቡ ሀይደር 'ጋብቻ' የሚለን፡፡ በስምምነት ገንዘብ ስለ ተከፈለ ብቻ 'ዝሙት' የሚለውን መጠሪያ ያሽርና 'ጋብቻ' የሚለውን ስያሜ በመውረስ የክብር ዙፋን ላይ ይቀመጣል፡፡ ከኢስላም ውጭ ባሉ ወገኖች ዘንድ ምንም የተለያየ ቅብ ቢያርፍበትም ስሙ አንድ ነው፤ ገላን ሽጦ ማደርና ገላ ገዝቶ ማደር፡፡ አገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው ዝሙት፡፡ ለአላህና ለነቢዩ ግን የሻጭና የገዥ በገንዘብ ውል ስለያዙበት 'ትዳር' ቢባል ች-ግ-ግ-ግር የለውም፡፡

እስኪ ደግሞ አንድ በጣም ጸያፍ ስለሆነ አንድ የኢስላም ጉድ ላስነብባችሁ፡፡ ጸያፍነቱ ለእኔ የሴት ልጆች አባት ለሆንኩት ብቻ ሳይሆን ሙስሊም ሴቶችም ውዳቸውን መልሶ ለማቀፍ በጣም የሚያስፈልጋቸው ቢሆንም ተጸይፈውታል፣ በጎ ሕሊና ላለቸው የሰው ልጆች ሁሉ ሲያወጉት እንኳን ሳይቀር ጸያፍነቱ የጎፈንናል፡፡ እርሱ ምንደን ነው? ላላችሁኝ እነሆ የነቢዩ ሙሐመድን ቃል፡-
መልካም የአባቶች ቀን። ያላነበባችሁ አንብቡት።
የመካው ሙሐመድ – መካን አምላክ ያስተዋወቀ መካን ሰው http://www.ewnetlehulu.org/am/mo-impotent/
http://www.ewnetlehulu.org/am/ask-those-who-read-the-book/

"መፅሃፉን የሚያነቡትን ጠይቅ!"

ሊንኩን ይጫኑ!
ሙሐመድ የሴት ልብስ ለባሹ!
መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ በማለት ይህንን ተግባር አጥብቆ ይከለክላል፡-

“ሴት የወንድ ልብስ አትልበስ፥ ወንድም የሴት ልብስ አይልበስ፤ ይህን የሚያደርግ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነውና።” (ዘዳግም 22፡5)

የተቃራኒ ፆታ ልብስ መልበስ (Cross Dressing) በብዙ ባሕሎች ውስጥ ከስነ ምግባር ጉድለት የሚቆጠር ፀያፍ ድርጊት ነው፡፡ ተባዕታይና አንስታይ ፆታዎች ተለይተው የሚታወቁት አንድም በአለባበሳቸው በመሆኑ የአንድን ማሕበረሰብ ጤናማ መስተጋብር ለመጠበቅ የአለባበስ ስርዓትን ማክበር አስፈላጊ ነው፡፡

ነቢይ የተባለው ሙሐመድ ይህንን ወሳኝ ግብረ ገባዊ ስርዓት ካለማክበሩም በላይ መለኮታዊ መገለጥ የሚመጣለት በሚስቱ ቀሚስ ውስጥ መሆኑን በመናገር መለኮታዊ ልዕልናን የሚያንኳስስ ስህተት ፈፅሟል፡፡
http://www.ewnetlehulu.org/am/mo-cross-dresser/
ውድ ጓደኞቼ እንዴት ሰነበታችሁልኝ! እነሆ ቃሌን አክብሬ ተመልሻለሁ፡፡ በዚህኛው ጽሑፌ በቀሩኝ ሁለት የአቡ ሀይደር የሙግት ነጥቦች ላይ ትችቴን አስነብቤያችሁ ነገሬን ልቋጭ አስቤያለሁ፡፡ ከዛም አቡ ሀይደርና የሕያ ኢብኑ ኑሕ የመልስ መልስ ካላቸው እንጠብቃቸዋለን፡፡ በግልባጭ ወደ ሁለቱም እንዲደርስ ይደረጋል፡፡ ኡስታዝ አቡ ሀይደር ወሲብ በጀነት ለመኖሩ ሁለቱ አስረጅዎች አሉኝ ማለቱ ይታወሳል፡-

1. ትንሳኤ ሙታን በመንፈስ ብቻ ሳይሆን በሥጋም ነው፤ በሥጋ የምንነሳው የጀነት ጸጋዎችን እንድንቋደስ ነው፡፡ ይህ ካልሆነ በሥጋ መነሳት ጥቅሙ ምንድን ነው? በሥጋ መነሳቱ በራሱ ትዳር ለመኖሩ አንድ ማስረጃ ነው፤ ምድር ላይ ጋብቻ ጸጋ ሆኖ ከተሰጠ ጀነት ላይ ይህ ቢቀጥል በምን መልኩ ዝሙት ሊባል ይችላል? በምድር የተቀደሰ ተግባር በጀነት ይቀጥል ቢባል ምንድን ነው ችግራቸው? ጀነት ውስጥ ትዳር መኖሩ ድርጊቱን ዝሙት ካሰኘው እንዴት በዚህ ምድር ሊፈቀድ ቻለ? በዛ ሃራም ከሆነ በዚህም ሃራም መሆን ነበረበት በማለት ይሞግታል፤

2. የአዳምና የሄዋን ታሪክ በራሱ አንድ ማስረጃ እንደሆነ፤ እነርሱ በጀነት እያሉ ትዳር ነበራቸው፡፡ ስለዚህ ለእኛም በዛ ትዳር ለመኖሩ ማሳያ ነው

ኡስታዝ አስረጅ ይሆኑልኛል ብሎ እነዚህን ቢያቀርብም ሐሳቦቹ ውኃ የሚያነሱ አይደሉም፤ ሁለት በመክፈል እሞግታቸዋለሁ፡፡ የመጀመሪያው ኡስታዝ "ምድር ላይ ጋብቻ ጸጋ ሆኖ ከተሰጠ ጀነት ላይ ይህ ቢቀጥል በምን መልኩ ዝሙት ሊባል ይችላል? በምድር የተቀደሰ ተግባር በጀነት ይቀጥል ቢባል ምንድን ነው ችግራቸው? ጀነት ውስጥ ትዳር መኖሩ ድርጊቱን ዝሙት ካሰኘው እንዴት በዚህ ምድር ሊፈቀድ ቻለ?" የሚለው የሐሰት ክስና ውኃ የማይቋጥር ሐሳብ ነው፡፡ ሲጀመር ጋብቻን ዝሙት ብሎ የጠራ በሌለበት እንዲህ አይነት ማጠልሸት ተገቢ ሊሆን አይችልም፡፡ ሁለተኛ ዝሙቶችን በዐይነት ጋብቻ የሚባል ካባ እያለበሰ ሕጋዊ የሚያደርግ ብቸኛው ተቋም ኢስላም ብቻ ነው፡፡ "ጋብቻ" የሚባል ካባ የተደረበላቸውን ግልጽ ዝሙቶች ዝርዝር ከዚህ በፊት ማስነበቤ ይታወሳል፡፡ እነዛ ግልጽ ዝሙቶች ጋብቻ ከተባሉና በጀነትም ይቀጥሉ ከተባለ ዝሙት በጀነት የለም ብሎ መከራከር እንዴት ይቻላል? ዝሙት ዝሙት እንጂ ጋብቻ ሊሆን አይችልም፡፡

ልቀጥል! ኡስታዝ አቡ ሀይደር እንዲህ ዓይነት የሙግት ሐሳብ ካነሳ አላህ በጽድቅና በእርኩሰት ላይ ግልጽ አቋም የሌለው አምላክ መሆኑን አልተረዳም ማለት ነው፡፡ ጋብቻ በምድር ጸጋ ስለ ሆነ በገነት መቀጠሉ ትክክል ነው በሎ ካሰበ ለሙስሊሙ በምድር "እርኩስ" የሆነ በገነት በዛው ልክ መቀጠል ይኖርባቸዋል የሚል መደምደሚያ ላይ ያደርሳል፡፡ ነገር ግን በአላህ ገነት ይህ ሲሆን አይታይም፡፡ ለምን? አንዱን ጥሎ ሌላውን አንጠልጥሎ አይቻልም፡፡ በምድር ሀራም የሆኑ በገነት በስፋት የተደገሱ ጸጋዎች ሆነው ሙስሊሙን እየጠበቁ ነው ተብሏል፡፡ ታዲያ ኡስታዝ ጸጋ ይቀጥል ካለ ሀራምም ሀራም ሆኖ መቀጠል አለበት የሚል ጥያቄ ለምን አላነሳም? መልስ ያስፈልገዋል፡፡ ስለዚህ የሙግት ሐሳቡ ተቀባይነት ሊኖረው አይችልም፤ በገነት ትዳር አለ የሚለውንና የተስፋውን ትክክለኛነትም ፈጽሞ የሚያሳይ አይሆንም፡፡

ሁለተኛው ትንሣኤ ሙታን እንዳለ በሚያምኑ ዘንድ የሙታን ትንሣዔ በሥጋ ነው የሚለው የሚያከራክራቸው ነጥብ አይደለም፡፡ የአምላካችን ቃል መጽሐፍ ቅዱስም ሙታን ሥጋቸው እንደሚነሳ በግልጽ ያስተምራል፡፡ ኡስታዝ አቡ ሀይደር በዚህ ላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን እንደተለመደው አንሻፎ መጠቃቀሱ ሳይረሳብኝ፡፡ ለማንኛውም ምንም ሙታን በሥጋ ቢነሱም ጥያቄው፡-

 ኢስላም ከሞት የሚነሳው አካል በሚከውናቸው ተግባራት ከምድራዊው አካል ጋር ፍጹም ተመሳሳይ ሆኖ ይነሳል ይላልን? ካልሆነና ለውጦች የሚኖሩ ከሆነ የተሰጠውን ተስፋ ተብየውን እንደ ተስፋ እንዴት መቀበል ይቻላል?

ከላይ እንዳነበባችሁት ኡስታዝ አቡ ሀይደር ትንሣኤ በሥጋ ቢሆንም የሚነሳው አጠቃላይ ለውጥ ተደርጎበት እንደሆነ ዕውቀቱ ገና ስላልደረው ሙታን ከሞት በሥጋ መነሳታቸው በጀነት ወሲብ ስለመኖሩ ማሳያ እንደ አድርጎ አቅርቧል፡፡ የኢስላም የእውቀት ምንጮች የሙስሊሞች የትንሣዔ አካል ምንም በሥጋ የሚነሳ ቢሆንም በምድር ያከናውን የነበረውን ዐይነት ተግባራት በሙላት የሚከውን አካል እንዳልሆነ ያሳያሉ፡፡ ስለዚህ የኡስታዝ መደምደሚያ ተቀባይነት ሊኖረው አይችልም፡፡ የትንሣኤው አካል ከምድራዊው አካል የሚለይባቸው በርካታ መገለጫዎች ያሉት አካል ነው፤ ከእነዛ ልዩነቶቹ መካከል የኡስታዝ የሙግት ሐሳብ ውኃ እንደማያነሳ ያሳዩልኛል የምላቸውን ጥቂቶቹን ብቻ ላንሳ፡-

1. የሙስሊሞች የትንሣዔ አካል በመጠን እና በአካላዊ ባሕሪው ፍጹም ይለያል፡-

ምድራዊ አካል በአማካይ ቁመቱ 1.80 ሜትር አካባቢ ሲሆን የትንሣዔው አካል ግን 60 ክንድ ወይም 30 ሜትር አካባቢ ነው፡፡ ምድራዊው አካል የሚያረጅና የሚሞት፣ የሚደክምና ሲመሽ የሚያንቀላፋ ሲሆን የትንሣኤው አካል ግን ዘላለማዊ፣ የማያንቀላፋ ሁሌም ወጣት እንደሆነ ይኖራል፡-

ሙስሊም መጽሐፍ 40፣ ሐ.ቁ 6795
"… አይሸኑም፣ አይጸዳዱም፣ ጉንፋን አይዛቸውም፣ ምራቅ የላቸውም፣ የጸጉራቸው ማበጠሪያ ከወርቅ የተሠራ ነው፣ ላባቸውም ዝባድ ነው…. ሚስቶቻቸውም ትላልቅ አይኖች ያሏቸው ልጃ ገረዶች ናቸው፣ ቁመናቸው እንደ አንድ ሰው እንደ አባታቸው እንደ አዳም ቁመና 60 ክንድ ነው፡፡ "

እዚህ ላይ! ወርቅ በምድር ለሙስሊም ወንድ ሀራም ነው፤ እዛ ግን ማበጠሪያ የተሠራው ከወርቅ ነው ለምን? አብን ከሲር "አል-ቢዳያ ወን ኒሃያ" በተሰኘው መጽሐፋቸው የመጨረሻውን ሁኔታ በዘገቡበት ክፍል እንዲህ የሚል አስፍረዋል፡-

"ጃብር እንዳወራው የአላህ መልእክተኛ ተጠይቀው ነበር፡- የገነት ገቢዎች ይተኛሉን? ሲመልሱም፡- እንቅልፍ የሞት ወንድም ነው፣ እናም የገነት ሰዎች አይተኙም፡፡" (The book of the End, page 693)

ስለዚህ የትንሣዔው አካል ይህንን ያክል ልውጥና ከምድራዊው አካል ጋር መጠነ ሰፊ ልዩነት ካለው የትንሣዔውን አካል እንደ ምድራዊው አካል ይተገብራል ብሎ መጠበቅ ሞኝነት ነው፡፡

2. የምግብ መፈጨትና ተረፈ ምግብ የማስወገድ ሥርዓታቸው ፍጹም የተለያየ ነው፡-

ምድራዊው አካል ምግብ እንደሚያስፈልገው ሁሉ የሙስሊሞች የትንሣዔ አካልም የሚኖረው በምግብ ኀይል ነው፡፡ ምድራዊው አካል ተረፈ ምግብና መጠጥ ከውስጡ በሽንትና በአይነ ምድር መልክ ያስወግዳል፡፡ አዲሱ የሙስሊሞች የትንሣዔ አካል ግን የሚያስወግድበት ሥርዐት ከዚህ ይለያል፡፡ ከቀረበለት 300 ሳህን የጀነት ምግብ የቻለውን ከበላና ከጠጣ በኋላ ተረፈ ምግቡን የሚያስወግደው በሽንትና ዐይነ ምድር መልክ ሳይሆን እ.ፕ.ስ ብሎ በማግሳትና በላብ መልክ ነው፡-

ሙስናድ አቢ ሁሬይራ ሙስናድ አህመድ ኢብን ሐምባሊ ቁጥር 10511
“የአላህ መልእክተኛ እንዲህ አሉ፡- ‘በገነት የሰው ዝቅተኛው ስልጣን ሰባት ደረጃ አለው፤ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ያለውና ከእርሱ ከፍ ብሎ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ያለ ሰው 300 አገልጋዮች አሉት፤ በየቀኑ 300 የወርቅ ትሪ ምግብ ይቀርብለታል፡፡

ሳሂህ ሙስሊም መጽሐፍ 40፣ ሐቁ 6798
"ጃብር እንደዘገበው ሲናገሩ እንደሰማሁት የጀነት ነዋሪዎች ይበላሉ ይጠጣሉ ነገር ግን አይተፉም፣ አይሸኑም፣ አይጸዳዱም፣ በጉንፋንም አይቸገሩም፡፡ ጠያቂውም እንዲህ አለ፡- ምግቡ ምን ይሆናል? ወዲያውም እንዲህ አሉ፡- ያጋሳሉ እንዲሁም ያልባቸዋል፤ ላባቸውም ዝባድ… "
1ኛ የዮሐንስ መልእክት 5 ፡ 10-13
በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን በነፍሱ ምስክር አለው፤ በእግዚአብሔር የማያምን እግዚአብሔር ስለ ልጁ የመሰከረውን ምስክር ስላላመነ ሐሰተኛ አድርጎታል። እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደ ሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው። ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም። የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ ይህን ጽፌላችኋለሁ።

ውድ ሙስሊም እህቶቼና ወንድሞቼ ከዚህ ተረት ወጥታችሁ ወደ እውነተኛው ተስፋና ወደ አምላካችሁ ሕይወት መጥታችሁ ማየት የነፍሴ ናፍቆት ነው፡፡ በነገር ሁሉ ጌታዬና አምላኬ እንዲረዳችሁ የዘወትር ፀሎቴ ነው፡፡

ጨረስኩ

ሳሂህ ኢማን ነኝ!
በሌላ ርዕስ ደግመን እንገናኛለን እስከዛው ግን ሰላማችሁ የበዛ እንዲሆን ተመኘሁላችሁ ቸር ግጠመን!
የሙስሊሞቹ የትንሣዔ አካል ከምድራዊው አካል ጋር በተግባር አፈጻጸም ይህንን የመሰለ ልዩነት ካላቸው የትንሣዔውን አካል ከምድራዊው አካል ጋር አንድ ማድረግና በምድር ያደረገውን በገነትም ያደርጋል ብሎ ድምዳሜ ላይ መድረስ እንዴት ይቻላል?

3. በወሲብ ሥርዓትና በሂደቱ ይዘት ሁለቱ ይለያያሉ፡-

በዚህኛው ያላቸው ልዩነት ደግሞ እጅጉን ይገዝፋል፡፡ ልዩነቱ ከተጣማሪ እስከ ተግባር አፈጻጸምና ውጤት ድረስ የሚዘልቅ ነው፡፡ ምድራዊው አካል የሚጣመረውና ወሲብ የሚፈጽመው በአፈጣጠር ልዩነት ከሌላት ሴት ተብላ ከምትጠራው አዳም ጋር ነው፡፡ በጾታና ጾታዊ ልዩነት ከሚያስከትለው ልዩነት ውጭ ፍጹም አንድ ከሆነች አካል ጋር ጥምረቱን ያደርጋል፡፡ በዚህ ወሲብን ወሲብ የሚያሰኙት ሁኔታዎች ሁሉ ይፈጸማሉ፤ ግልጽ ስለሆነ መዘርዘር አያስፈልገኝም፡፡ በወሲብ ሂደት ውስጥ ወንዱ እርካታ ላይ ሲደርስ የዘር ፈሳሹን ይረጫል፡፡ የሙስሊሞች የትንሣዔ አካል ግን ከዚህ በእጅጉ ይለያል፡፡ "ለትዳር" የተፈጠሩለት አካላት (ሴት ብሎ መጥራት አይቻልም፤ ሴት አዳም ከአካሉ ተፈጥራ ለመጣችለት ለሔዋን ያወጣላት ስም ነው) ቀደም ብዬ እንዳስነበብኳችሁ ከእርሱ የማይመሳሰሉ ሳፍሮን (saffron) ተብሎ ከሚጠራ አበባ ወንዴ (stigma) የተፈበረኩ በጣም አስቀያሚ አካላት ናቸው፡፡

"ኢብን አባስ፣ አነስ፣ አቡ ሰላማህ እና ሙጃሂድ እንዳወሩት ሁር አል ዐይኖች የሚፈጠሩት ከሳፍሮን (saffron) ነው፡፡ ሳፍሮን ብርቱካናማ ቀለም ያለው ከአበባ የሚገኝ የምግብ ማቅለሚያና ማጣፈጫ ቅመም ነው፡፡ አሁን ያለው ከአፈር የተፈጠረው የሰው ልጅ በጣም ውብ ከሆነ ከሳፍሮን ቅመም የተፈጠሩት ሴቶች እንዴት ውብ ሊሆኑ እንደሚችሉ መገመት ትችላላችሁ፡፡" ብሏል፡፡ (The Maidens of Jannat (Paradise) page 22-23)

አላህ ለሴት አዳም ሙስሊም እህቶቻችን ያለውን ጥላቻና ንቀት ምን ያክል እንደሆነና የት ድረስ እንደሆነ እየተመለከታችሁ ነው? ይህንን የእናቱን፣ የእህቱን፣ የልጁንና የአክስቶቹን በአላህ መጠላትና መዋረድ እየተመለከተ ለዚህ ጥብቅና የሚቆም ሙስሊም ወንድ አለ፡፡ አላህን ለምን ብሎ ከመጠየቅ ይልቅ ይህችን በአላህ የ "Artificial Intelligence" የእውቀት ልቀት የተፈበረከችን ጉድ ለሀጩን እየጣለ ሲጠባበቅ፣ ሲገድል ሲገደል ማየት ሌላው ገራሚ ነገር ነው፡፡ ይሁንና እነዚህ ፍብርክ አካላት ከትንሣዔው ሙስሊም አካል ጋር ወሲብ ይፈጽማሉ ማለት አይቻልም፡፡ ምክንያቱም ወሲብን ወሲብ የሚያሰኙት ቅመሞች በመካከላቸው ስለሌሉ ግንኙነታቸውን ወሲብ ብሎ መጥራት አይቻልም፡፡ እርካታ የሌለው ወሲብ ትርፉ ድካም ብቻ ነው ፡-

"የጀነት ሰዎች ከሴቶች ጋር ወሲብ ይፈጽማሉ፣ እንዲሁም አይወልዱም፡፡ በገነት ውስጥ የወንድ የዘር ፈሳሽ (sperm) እንዲሁም ሞት የለም፡፡" (ʿAbd al-Razzāq, Muṣannaf xi, 420)

ከሞት የተነሳው ሙስሊሙ ወንድ እንደ ምድራዊው አዳም የወንድ ዘር ፈሳሽ የዘር ፈሳሽ (sperm) የለውም የሚለው ልዩነቱን ያጎላዋል፡፡ ሌላው በእነዚህ አዲስ ፍብርክ እንስት ተብየዎች እና በትንሣዔው ሙስሊም ወንዶች መካከል ያለው የመጠን ፍጹም አለመመጣጠን የልዩነቱ አካል ነው፡፡ አዳም ወንድና አዳም ሴት ተመጣጣኝ ተክለ ሰውነት ሲኖራቸው የጀነቶቹ ሙስሊም ወንድና ሁርየዋ በተክለ ሰውነት ዝሆንና ትንኝ የማለት ያክል ናቸው፡፡ ይታያችኋል ዝሆን ሁርዬ እና ትንኝ ሙስሊም ወንድ ወሲብ ሲፈጽሙ? ዘይገርም! ይሏችኋል ይሄ ነው፡፡

ሙሰነድ አቢ ሁሬይራ በሙሰነድ አህመድ ኢብን ሐምባሊ ቁጥር 10511
"…በምድር ከነበሩት ሚስቶቹ የተለዩ 72 ልጃገረድ ሚስቶች ይኖሩታል፤ የእያንዳንዷ ድንግል የመቀመጫ ስፋት የምድር አንድ ማይል (1.6 ኪ.ሜ) ያህል ነው'፡፡”

የትንሣዔው ሙስሊም ወንድ የሚኖረው ስፋት ደግሞ 7 ክንድ ወይም 3.5 ሜትር ብቻ ነው፡፡

እነዚህ ሁሉ በትንሣኤው ሙስሊም አካልና በምድራዊው ሙስሊም መካከል ያሉ ልዩነቶች የትንሣዔው ሙስሊም ወንድ ተለውጦ እንደሚነሣ ጉልህ ማሳያዎች ናቸው፡፡ ታዲያ የትንሣኤውን አካል በምድራዊው አካል ዐይን መመልከትና በዚህኛው ስሜት ያንን ተስፋ ማድረግ ትልቅ ስህተት አይደለም ትላላችሁ? ስለዚህ ተስፋ ተብሎ በቁርአንና በነቢዩ ሐዲሳት የተነገሩት አቡ ሀይደርም ከሁለት ከፍሎ የተረከልን፣ ሙስሊም ወንድሞቻችንም የሚጠባበቁት ሁሉ ጉም ነው፤ የለም፡፡ ቁርአን እንደተናገረው ሙስሊሞች ሁሉም ጉዟቸው ወደ ጀሀነም ነው፡፡ ከዚህ መውጣት ሳይኖር ስለ ገነትና በዛ ስለሚኖር ተድላ ማውራት ምን ይጠቅማል?

ሱረቱል መርየም 19 ፡ 71
ከእናንተም ወደ እርሷ ወራጅ እንጂ አንድም የለም፡፡ (መውረዱም) ጌታህ የፈረደው ግዴታ ነው፡፡

ይህንን ኢብን አባስ ሲያብራሩት እንዲህ ነበር ያሉት፡-

(ከእናንተም ወደ እርሷ ወራጅ እንጂ አንድም የለም፡፡) ነቢያትንና መልእክተኞችን ሳይጨምር ከእናንተ ገሃነም ሳይገባ የሚድን አንድም ሰው የለም ማለት ነው፤ ((መውረዱም) ጌታህ የፈረደው ግዴታ ነው፡፡) ይህም የግድ ተፈጻሚ የሚሆን ድንጋጌ ነው፡፡

ነቢዩ ሙሐመድ እንዲህ በሚል አንቀጹን አብራርተውታል፡-

"ሰይደኒ አቢ ሱመያ እንዳወሩት የአላህ መልእክተኛ አንዴ እንዲህ አሉ፡- ‘ማንኛውም ሰው ጻድቅ ይሁን ኃጢአተኛ በመጀመሪያ ገሃነመ እሳት ውስጥ ይገባል፤ ነገር ግን ጻድቁ አማኝ ልክ ናምሩድ ለአብርሃም ያነደደው እሳት እንደቀዘዘቀዘ እና እንደወጣ እንዲሁ ይቀዘቅዝለታል፤ ስለዚህ አማኙ ወደ ገነት ይወሰዳል፡፡' ይህም በሚቀጥለው የቁርአን አንቀጽ ተረጋግጧል (19 ፡ 72)”

ስለዚህ የኢስላም ጀነት "ላም አለኝ በሰማይ ወተቷንም አላይ" ሲሆን ነቢዩ ሙሐመድም የእውነተኛው አምላክ መልእክተኛ አይደሉም የሚለውን እምነታችንን ያጠናክራል፡፡

የ “እውን በጀነት ዝሙት አለን?” ጥያቄ ምላሽ!

አይ ልክ አይደለም ተስፋው አለ፤ አላህ አይዋሸንም ካሉ ደግሞ የመጀመሪያውን "በእውኑ በጀነት ዝሙት አለን?" የሚለውን የተነሳንበትን ጥያቄ ለመመለስ እገደዳለሁ፡፡ አቡ ሀይደር እንዲህ ማለቱ ይታወሳል፡-

 ይህን የመሰለ ምላሽ ሲሰጣቸው የቁጥሩ ጉዳይ ይላሉ፡፡ ዝሙትን ዝሙት የሚያሰኘው ሕገ ወጥነቱ እንጂ ቁጥሩ አይደለም፡፡ በዚህ ምድር እንኳን በእኩል ማስተዳደር ከቻለ ለአንድ ወንድ እስከ አራት ሴቶችን ማግባት ተፈቅዶለት የለምን?

ለጥያቄው ምንም እዚህ ግባ የማይባል ውትፍትፍና በብዙ ግድፈቶች የተጣበበ ምላሽ እንደ ሰጠ፣ አልፎ ተርፎ የጥያቄውን አቅጣጫ ለማስቀየር ሲሞክር እየተመለከትን ነው፡፡ ከሳፍሮች የተፈበረኩት ጉዶች (ሴቶች ያላልኩት ሴት ስላልሆኑ መሆኑ ይታወቅልኝ) ቁጥር በራሱ አስገራሚና ብዛታቸው ተስፋው ከእውነተኛው አምላክ ላለመሆኑ ማሳያ ቢሆንም ያንን የተመለከተው ጥያቄ ግን ከዚህኛው ጋር ተያያዥ አይደለም፡፡ ስለዚህ ከብዛታቸው ተነስቶ ስለ ዝሙት ተየጠየቅን የሚለው ሐሰት ነው፡፡ ብዛቱንም ሕጋዊ ለማስመሰል ሱረቱል አል-ኒሳዕ 4 ፡ 3 ያያዘውን የሚስቶች ብዛት ጠቅሷል፡፡ ይህም ቢሆን ቁርአን የአምላክ ቃል ያለመሆኑ አንዱ ማሳያ እንጂ በአስረጅነት ተጠቃሽ ሊሆን የሚችል አይደለም፡፡ ለማንኛውም "በጀነት ዝሙት እንዴት ሊኖር ቻለ?" ለሚለው ጥያቄ የሁርዬዎቹ ብዛት አለመሆኑ ይሰመርበት፡፡
"በጀነት ዝሙት እንዴት ሊኖር ቻለ?" ለሚለው ጥያቄ መነሻ ጀነት ውስጥ በሚገኘው ገበያ የጀነት ገቢ ሙስሊም ወንዶች የሚፈጽሙት ልቅ የወሲብ ተግባር ነው፡፡ ነቢዩ ሙሐመድ በገነት የገበያ ሥፍራ ስለመኖሩ ተናግረው በተለያዩ የሐዲስ ዘጋቢዎች ተዘግቧል፡-

ሱና ቲሪሚዚ ቅጽ 4፣ ቁ. 2549
….ከዛ ጌታችን አዘ ወ-ጀል እንዲህ ይላል፡- ተነሱ ስለክብራችሁ ወዳዘጋጀሁላችሁ፤ ያንን የምትፈልጉትንም ውሰዱ፡፡ ከዛም በመላእክት የተከበበ የገበያ ቦታ አገኙ፡፡…

የዚህ የገበያ ሥፍራ ተግባርና የተዘጋጀበት ዋና ዐላማ ምንድን ነው? የሚለውንም ነቢዩ መልሰውታል፡፡ ኢማም ገዛሊ ያንን እንዲህ አስቀምጠውታል፡-

"ጨምረውም እንዲህ አሉ፡- በገነት ገበያ ይኖራል፤ በዛ ምንም አይሸጥበትም አይገዛበትም፤ ነገር ግን ወንዶችና ሴቶች ይኖሩበታል፡፡ ማንኛውም ወንድ ከሴቶቹ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ለማድረግ ከፈለገ በፍጥነት ያደርጋል፡፡…" (Ihya Ulum-Id-Din (Revival of religious learnings), translated by Fazl-ul-Karim, vol 4, page 430.)

ኢማም ቡኸሪም የዚህን ስፍራ አገልግሎት እንደሚከተለው የነቢዩን ንግግር በመውሰድ አስተላልፈዋል፡-

ሳሂህ አል-ቡኻሪ ቅጽ 4፣ 56 ፡ 468
ሳሂህ አል-ቡኻሪ ቅጽ 6፣ 60 ፡ 402
አብዱላህ ቢን ቃኢስ ሲናገር የአላህ መልእክተኛ እንዲህ አሉ፡- በገነት ከአንድ ወጥ ሉል የተሠራ ስፋቱ 60 ማይል የሆነ አዳራሽ አለ፡፡ ከአንዱ ጥግ ያለው በሌላው ጥግ ያለውን በማይመለከትበት በዚህ አዳራሽ ሚስቶች በየጥጉ አሉ፤ አማኞች ይጎበኟቸዋል በእነርሱ ይደሰቱባቸዋል፡፡…

ከዚህ እንደምንገነዘበው ቦታው የሚገዙበት የሚሸጡበት ሳይሆን የገነት ወንዶች ከመኖሪያቸው ወጥተው የሚሰባሰቡበትና ከተሰጧቸው 72 ሚስቶች ውጭ በገበያው አዳራሽ ከሚገኙት ጋር ወሲብ እንደፈለጉ የሚፈጽሙበት ቦታ ነው፡፡ የወሲብ ገበያ አዳራሽ ነው፡፡ በገበያው ያሉት ሴቶች ብቻ ሳይሆኑ ወንዶችም ጭምር እንደሆኑና ከእነርሱም ጋር ፍላጎትን መፈጸም እንደሚቻል የሚከተሉት የነቢዩ ሐዲሳት ያስገነዝባሉ፡-

"ጃብር ኢብን አብደላህ እንዲህ አለ፡- ሁላችን ተሰባስበን እያለን የአላህ መልእክተኛ ወጥተው ወደ እኛ መጡ፡፡ እንዲህም አሉ እናንተ ሙስሊሞች ሆይ በገነት ፎቶዎች ብቻ ያሉበት ምንም የማይሸጥበትና የማይገዛበት የገበያ ቦታ አለ፡፡ የወንድ ወይም የሴቶቹን ፎቶ ያፈቀረ ሰው ወደ ዛው ውስጥ ይገባል፡፡"(The book of the End, page 693)

ሱና ቲሪሚዚ ቅጽ 4፣ ቁ. 2550
ሁሉም እንዳወሩት የአላህ መልእክተኛ እንዲህ አሉ፡- በእርግጥ በገነት የወንዶችና የሴቶች ፎቶ መለጠፊያ እንጅ ማንም የማይሸጥበትና የማይገዛበት ገበያ አለ፡፡ አንድ ሰው ፎቶውን ከወደደው ወደዛው ይገባል፡፡

ጎብኝው የገነት ገቢ ሙስሊም ወንድ የወደደው የወንዱን ፎቶ ቢሆንስ? ሙስሊም ሊቃውንት ለዚህ ሐዲስ የሰጡት ማብራሪያ ምን እንደሚል እስኪ ላስነብባችሁ፡-

ሐዲሱ የሚለን በገነት ምንም የማይሸጥበትና የማይገዛበት የተለየ ዓይነት ገበያ አለ፡፡ በማሳያ ላይ ስፍር ቁጥር የሌላቸው የቆንጆ ወንዶች እና የቆነጃጅት ሴቶች ፎቶ ይኖረዋል፡፡ ወንዶቹ የትኛውንም ፎቶ ለራሳቸው ይመርጡና ይወስዳሉ፤ ሚስቶቻቸውም ወደ መረጡት ፎቶ ይለወጡላቸዋል ማለት ነው፡፡

የተመረጠው የወንድ ፎቶ ቢሆን ሁርዬዋ ወደ ተመረጠው ወንድ ፎቶ ትለወጥለትና የወደደውን ያደርጋል ማለት ነው? ወደ ዛው ይገባል ተባለ እንጂ ወደ ሚስቱ ተመልሶ ትለወጥለታለች አይልም፡፡ ሐዲሱ ምን ዐይነት መልእክ ቢያስተላልፍ ነው እንዲህ ዐይነት የማይገኛኝ ትርጉም የተሰጠው? የሚቀጥለው ግልጽ ያደርገዋልና ተከተሉኝ፡፡ ኢማም ኢብን ከሲር ቀደም ብዬ በጠቀስኩት መጽሀፋቸው የገበያውን ቦታ በተመለከተ የሚለተለውን አስፍረው እናገኛለን፤ ለላይኛው ሐዲስ ማጠናከሪያ ይሆነናል፡-

"በአት-ቲርሚዚ ውስጥ የሚገኝ ሐዲስ አሊ እንዳወራው የአላህ መልእክተኛ እንዲህ አሉ፡- በእውነት በገነት የገበያ ቦታ አለ፤ በዛ ግዥም ሽያጭም አይካሄድም፡፡ በምትኩ የሴቶችና የወንዶች ፎቶ ይገኛል፤ እናም የትኛውም ወንድ ፎቶውን ከወደደው ወደ ፎቶው ባለቤት ይገባል፡፡ (ቲሪሚዚ) ….በምንም ደረጃ ይህ እንዲህ እንደ ማለት ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል ወንዶች መግባት የሚፈልጉት ፎቶው የወንድ ወደ ሆነው ብቻ ነው፤ በተመሳሳይ ሴቶች መግባት የሚፈልጉት ፎቶው የሴት ወደ ሆነ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ ይህ ሐዲስ ከዚህ በፊት ያለው ሐዲስ ማብራሪያ ይሆናል፡፡" (The book of the End, page 693)
ታዲያ በዚህ ላይ እንዲህ የሚሉ ጥያቄዎች ማንሳት ተገቢ አይመስላችሁም፡-

 ፎቷቸው የተለጠፈላቸው ወንዶችና ሴቶች እነማን ናቸው? ከየትስ መጡ? መራጮቹስ ለምን ወንዶቹ ብቻ ሆኑ? ሴቶቹ የተባሉት የትኞቹ ሴቶች ናቸው? የምድር ሴት ምእነናን ማለት ነው? የገበያው ማዕከል የወሲብ ገበያ እንደመሆኑ መጠን ተመሳሳይ ጾታ ያለቸው በወሲብ እዛም ይፈላለጋሉ ማለት ነው?

 የወንድና የሴት ፎቶዎች የሚለጠፉበት ገበያ ከሆነ ወንድ ሁርየዎችም ይፈጠራሉ ማለት ነው?


 መለወጥ የሚለውን አመለካከት እንውሰድ ቢባል ወደ ገበያ የወጣው ሙስሊም የተሳበው በወንዱ ፎቶ ቢሆን ምንድን ነው የሚሆነው? ሁርዬ ወደ ወንድ ተለውጣለት ከወንዱ ጋር ግብረ ሰዶም ይፈጽማል? ወይስ ወደ ወንዱ መልክ ተለውጣለት ወንዱን እያሰበ ወሲብ ይፈጽማል ማለት ነው?

ይህንን ያክል ከከፈትኩላችሁ በሐዲሶቹ ላይ ተመስርታችሁ እናንተው ጥያቄዎችን ጨማምሩበት፡፡ በዚህ መካከል "ሐዲሱ ደኢፍ ነው" የምትል የተለመደች ማስተባበያ ከዘለፋና ከስድብ ጋር መነሳቷ አይቀርም፡፡ ለዚህ ያለኝ ምላሽ አንደኛው የጠቀስኩዋቸው ሐዲሶች የታመኑ የኢስላም ሊቃውንት ያሚያምኑባቸውንና በመጽሐፎቻቸው የከተቧቸውንና ሙስሊሙ በአላህ ዘንድ የተዘጋጁላቸውን ተስፋዎች እንዲያውቁ ያደረጉባቸውን ሐዲሶች እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ እንኳን የሐዲስ ይቅርና የቁርአን ሰሂህ የለም፡፡ ለትክክለኛነቱ አስረጅ ሊቀርብለት የሚችል አንድም ኢስላማዊ ሰነድ አለመኖሩ ሊታወቅ ይገባል፡፡ ማስረጃ አለን የሚል ካለ በዚህም ላይ መነጋገር የሚቻል መሆኑን ላሳስብ እወዳለሁ፡፡

ስጠቀልለው በኢስላም ጀነት ያለው ዝሙት ሳይሆን ከሱ የከፋው ግብረ ሰዶማዊነት ነው፡፡ ይህ ነው "በጀነት ዝሙት እንዴት ሊኖር ቻለ?" ለሚለው ጥያቄ መነሻ የሆነው፡፡ የአምላካችን የእግዚአብሔር ቃል እንደሚነግረን ይህ ክፉ ተግባር እንኳን በገነት ሊኖር ይቅርና በምድር ይለማመዱ የነበሩ ትውልዶች ከሰማይ በዘነበ እሳት ዝክራቸው ከምደር ተደምስሷል፡፡ ስለዚህ ተስፋው ጉም ነው፤ የለም፡፡

የኢስላም ጀነት "ላም አለኝ በሰማይ ወተቷንም አላይ"!

የተጨበጠ አስተማማኝ የዘላለም ሕይወትን መንገድ ትፈልጋለህ? ትፈልጊያለሽ?

የዮሐንስ ወንጌል 14 ፡ 6
ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።

በዚህ መንገድ ለሚጓዙና ሕይወቱን ለተቀበሉ እርግጠኛ እንዲሆኑ እንዲህ የሚል ተጽፎላቸዋል፡-
የኢስላም_ጀነት_ላም_አለኝ_በሰማይ_ወተቷንም_አላይ.pdf
420.2 KB
እውን በጀነት ዝሙት አለን? ለሚለው የኡስታዝ አቡ ይደርና የየሕያ ኢብኑ ኑሕ ዲስኩር ተከፋፍሎ ተሰጥቶ የነበረውን ምላሽ ጠቅለል አድርጌ እነሆኝ ብያለሁ
ሰላም ሰላም ውድ ጓደኞቼ እንዴት አላችሁልኝ? እኔ በጣም ሰላም ነኝ! እስካሁን እኔ ይጠቅማችኋል ያልኩትን ሳካፍላችሁ ቆይቻለሁ፡፡ አሁን እስኪ ለእናንተ እድል ልስጣችሁና ኢስላምን በተመለከተ ስለምን ማወቅ ትፈልጋላችሁ? ይኸኛው ጥያቄ ሆኖብኛል የምትሉትን፣ ግራ ያጋባችሁን አምጡት እኔ የማውቀውን እኔው ከእኔ እልፍ ያለውን ደግሞ መጽሐፍትን አማክሬ እመልስላችኋለሁ፡፡ ስለዚህ በመልእክት ማስቀመጫው በኩል ላኩት ይደርሰኛል፡፡ እወዳችኋለሁ! የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምና ፀጋ ይብዛላችሁ ይጠብቃችሁ!!!!
Forwarded from Good news
የነቢዩ ሙሐመድ ምስክሮች.pdf
1.3 MB
ውድ ክርስቲያን ሙስሊም ጓደኞቼ እንዴት አላችሁልኝ? ሰላማችሁን የሰላሙ ልዑል እንዲያበዛላችሁ እመኛለሁ! ቀደም ብዬ ባቀረብኩት ሐሳብ መሠረት የተወሰኑ ወንድሞች ጥያቄዎቻቸውን ልከውልኛል፡፡ አመሰግናለሁ! በቅርብ መልሶቻቸውን ለዚህ በሚመጥን መልኩ ይዤ ብቅ እላለሁ፡፡ እስከዛው ግን አንዲት በጌታ እርዳታ የጻፍኳት ጥሩ መጽሐፍ አለችኝ፡፡ ከታተመች ትንሽ ቆየት ብላለች፡፡ ከዚህ የተነሳ አሁን ማሻሻያ እያደረግኩባት ነው፡፡ በቅርብ ቀናት ውስጥ እጨርሳለሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ የተሸሻለውን እንዴት ማግኘት እንደምትችሉ ወደ ፊት የምንነጋገርበት ቢሆንም እስከዛው እባካችሁ የሚታረምና የሚስተካከል ያላት ቢሆንም የመጀመሪያዋን ጽሑፍ ተቃመሱልኝ ብያለሁ!!
መንፈስ ቅዱስ ሁሉን አዋቂ መለኮት ነው!
ለሙስሊም ሰባኪያን ስሁት ሙግት የተሰጠ ምላሽ

http://www.ewnetlehulu.org/am/holy-spirit-omniscient/
Channel photo updated
እውን የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ እና የቁርአኑ ኢሣ አንድ ናቸውን?

በምን ሐሳብ ላይ እንድንወያይ ይፈልጋሉ ብዬ መጠየቄን ታስታውሳላችሁ፡፡ ታዲያ አንድ ወዳጄ "እውን የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ እና የቁርአኑ ኢሣ አንድ ናቸውን?" በማለት ምላሽ እንድሰጥበት ያቀበለኝ ጥያቄ ነው፡፡ ታዲያ ይህንን ጥያቄ በሁለት መንገድ ምላሽ እንዲሰጥበት ቁርአን ይጋብዛል፡፡ የመጀመሪያው ከራሱ ከቁርአን ተልእኮ አንጻር የሚታይ ሲሆን ሁለተኛው ቁርአን ሁለቱን አንድ አድርጎ የሚተርክበት አውድ ስላለ በዛው መነጽር የሚታይ ነው፡፡

1. "እውን የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ እና የቁርአኑ ኢሣ አንድ ናቸውን?" በቁርአን ተልእኮ መነጽር

ቁርአን ጥርት ያለ ተልእኮ ባይኖረውም ተልእኮ ተብለው ከተዘረዘሩት መካከል አንዱ፡-

ሱረቱል ዩኑስ 10 ፡ 37
ይህም ቁርኣን ከአላህ ሌላ (ከሆነ ፍጡር) የተቀጠፈ ሊሆን አይገባውም፡፡ ግን ያንን ከእርሱ በፊት ያለውን (መጽሐፍ) የሚያረጋግጥና በመጽሐፉ ውስጥ ያለውን የሚዘረዝር በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲሆን ከዓለማት ጌታ (የተወረደ) ነው፡፡

وَمَا كَانَ هَٰذَا الْقُرْآنُ أَن يُفْتَرَىٰ مِن دُونِ اللَّهِ وَلَٰكِن تَصْدِيقَ الَّذِي بَيْنَ يَدَيْهِ وَتَفْصِيلَ الْكِتَابِ لَا رَيْبَ فِيهِ مِن رَّبِّ الْعَالَمِينَ [١٠:٣٧]

ሱረቱል አሊ-ዒምራን 3 ፡ 3
ከርሱ በፊት ያሉትን መጻሕፍት የሚያረጋግጥ ሲኾን መጽሐፉን (ቁርኣንን) ባንተ ላይ ከፋፍሎ በእውነት አወረደ፡፡ ተውራትንና ኢንጂልንም አውርዷል፡፡

نَزَّلَ عَلَيْكَ الْكِتَابَ بِالْحَقِّ مُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ وَأَنزَلَ التَّوْرَاةَ وَالْإِنجِيلَ [٣:٣]

مُصَدِّقًا (ሙሰዲቀን) ሌላውን በንግግሩ ወይም በያዘው መረጃ ማመን መቀበል፣ ለእውነትነቱ ምስክርም መሆን ማለት ነው፡፡ (An Arabic-English Lexicon by Edward William Lane ገጽ 1667)

ታዲያ እንዴት ነው የሚያረጋግጠውና የሚመሰክረው? በምንድን ነው ማመኑንና መቀበሉን የሚያሳየው? ስንል አንዱ ተመሳሳይ መልእክቶችን በመያዝና በአንዱ አምላካዊ ጎዳና በማጠብጠብ ነው፡፡ እንዲህ ስለሆነ ነው ቁርአን እንዲህ የሚለውን አንቀጽ በውስጡ ሊያቅፍ የቻለው፡-

ሱረቱል አል-ኒሳዕ 4 ፡ 26
አላህ (የሃይማኖታችሁን ሕግጋት) ሊያብራራላችሁ ከእናንተ በፊትም የነበሩትን ነቢያት ደንቦች ሊመራችሁ በእናንተም ላይ ጸጸትን ሊቀበል ይሻል፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡

ሱረቱል አል-አንአም 6 ፡ 89-92 እንዲሁም ሌላኛው መርህ ሆኖ ሊያገለግለን ይችላል፡፡ ሱራ 5 ፡ 15 ተጨማሪን ፍንጭ ይዟል፡፡ እንዲህ ከሆነ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስና የቁርአኑ ኢሣ አንድ ናቸው ማለት ካለብን በሁለቱም መጽሐፍት ውስጥ በተመሳሳይ መግለጫዎች እና መልእክቶች ተወክለው ልናገኛቸው ይገባል፡፡ ይህንን ፍለጋ በዚህ ሚዛን ላይ ስናወጣቸው የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ እና የቁርአኑ ኢሣ አንድ አለመሆናቸውን እንመለከታለን፡፡

የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ፡-

ከስሙ እንጀምር፤ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ ስሙ ስም ብቻ ሳይሆን ተልእኮውን ገላጭም ነበር፡፡ ኢየሱስ ማለት እግዚአብሔር ያድናል፣ ይረዳል ማለት ነው፡፡ መልአኩ ገብርኤልም ለዮሴፍ "በሕልም የሕፃኑን ስም ኢየሱስ ትለዋለህ" ሲለው ትርጉሙንና አገልግሎቱን እንዲህ በማለት ነበር የገለጸው፡-

ማቴ 1 ፡ 21
ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።

ይህ ክፍል የብዙ ቀደምት ነቢያት ትንቢታዊ መልእክት ድጋፍ ያለው መሆኑን ሳላሳስብ አላልፍም፡፡ ወንጌላዊው ዮሐንስም ይህንኑ በሚያደምቅ መልኩ የተልእኮውን ዓላማ እንዲህ ሲል አስፍሮታል፡-

ዮሐ 3 ፡ 16-17
በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና።

የቁርአኑ ኢሣ ግን እንዲህ አይደለም፡፡ የመጀመሪያው የቁርአንን አውደ ጥበብ ያዘጋጁ ሊቃውንት ኢሣ የመጽሐፍ ቅዱሱን ኢየሱስ የስም ትርጓሜ እንደ ሌለው ሲናገሩ፡- "Īsā, the qurānic form of his name, has no such connotations" (Encyclopedia of Quran, vol 3 page 11) ብለዋል፡፡ ኢሣ ማለት ምን ማለት ነው ለሚለው ይኸው የቁርአን አውደ ጥበብ የነቢዩ ሙሐመድን ቃል ዋቢ በማድረግ የመልኩን ቀለም የሚገልጽ ሆኖ "ነጣ ያለ ቀይ" (a reddish whiteness) ማለት እንደሆነ ይናገራል፡፡ ይህም ስለ አንድ አካል እየተናገረ ያለ ላለመሆኑ ጉልህ ማሳያ ነው፡፡

የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ ማንነቱ፡-

የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ ማንነት ከሙሴ የጀመረ እስከ አብረውት እስከ ወጡ እስከ ገቡ ሐዋርያት ድረስ፣ መላእክትንም ጨምሮ ተርከውለታል፡፡ ሰዎች እየሰሙ አብ ከሰማይ ተናግሮለታል፡፡ ለተገለጠውና የለመሰከረለት ማንነቱም ሰዎች ሕይወታቸውን እስከሞት ድረስ አሳልፈው ሰጥተዋል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ብቻ ሳይሆን ፍጹምም አምላክ ነው፡፡ ለዚህ ለቁጥር የሚያታክቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ማቅረብ ይቻላል፤ ይሁንና ለአብነት የሚሆኑ ከተለመዱትና ከምታውቋቸው የተወሰኑትን ላስነብባችሁ፡-

ትንቢተ ኢሳይያስ 9 ፡ 6
ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።

ሐዋርያው ዮሐንስም በወንጌሉ እንዲሁም በመልእክቶቹ አምላክነቱን አብስሯል፡-

ዮሐ 1 ፡ 1-3
በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ። ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ። ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።

1ኛ ዮሐ 5 ፡ 20
… እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።

ሌላው ጌታ ኢየሱስ ክርሰቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው፡፡ ለዚህም ከእግዚአብሔር ቃል አስረጅዎቼን እነሆኝ፡፡ መለአኩ ገብርኤል ከተናገረው ልጀምር፡-

ሉቃ 1 ፡ 35
መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፦ መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።

ቅዱስ እግዚአብሔር አምላክም ስለ ልጁ በተደጋጋሚ ሰው በጀሮው እየሰማ ልጄ ብሎ መስክሮለታል፡-

ሉቃ 3 ፡ 22
መንፈስ ቅዱስም በአካል መልክ እንደ ርግብ በእርሱ ላይ ወረደ፤ የምወድህ ልጄ አንተ ነህ፥ በአንተ ደስ ይለኛል የሚል ድምፅም ከሰማይ መጣ።

ለመስቀል ሞት ያበቃው ይኸው የእግዚአብሔር ልጅነቱ አልነበረምን?

ማቴ 26 ፡ 63-66
ኢየሱስ ግን ዝም አለ፦ ሊቀ ካህናቱም፦ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ የሆንህ እንደ ሆነ እንድትነግረን በሕያው እግዚአብሔር አምልሃለሁ አለው። ኢየሱስም፦ አንተ አልህ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ከእንግዲህ ወዲህ የሰው ልጅ በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ አለው። በዚያን ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ልብሱን ቀዶ፦ ተሳድቦአል እንግዲህ ወዲህ ምስክሮች ስለ ምን ያስፈልገናል? እነሆ፥ ስድቡን አሁን ሰምታችኋል፤ ምን ይመስላችኋል? አለ። እርሱም፦ ሞት ይገባዋል ብለው መለሱ።
ነቢዩ ሙሐመድና አላህ ይህንን ታሪክ መለኮታዊ መገለጥ ይበሉት እንጂ ከላይ በአንቀጹ እንደ ተመለከተው በዙሪያቸው ከነበሩ ክርስቲያን ተብለው ከሚጠሩ ሰዎች በጀሮ ጠገብ የሰሙት የዛ ዘመን ተረት ነው፡፡ የዚህ ታሪክ ምንጭ አሁንም የአዲስ ኪዳን አዋልድ መጽሐፍ ነው፡፡ ታሪኩ በ "ቶማስ ወንጌል (The Gospel of Tomas)" የኢየሱስ የልጅነት ታሪክ ተብሎ ተጽፎ የሚገኝ ነው፡፡ በነቢዩ ዘመን የነበሩ የመካ ክርስቲያኖች ያወሩት የነበር ታሪክ ነው፡፡ ከዚህ የምንረዳው በፊትም እንደገለጽኩት ቁርአን መለኮታዊ መገለጥ ሳይሆን ጀሮ ሰምቶ ከሞላው እየተቀዳ የተጻፈ የተረቶች ስብስብ ነው፡፡

ስለዚህ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ እና የቁርአኑ ኢሣ አንድ ሊሆኑ አይችሉም፡፡ ኢሣ ተረት ሲሆች ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ሕያው ነው፡፡ ነቢዩ ሙሐመድና ቁርአን ከእውነተኛው አምላክ የተላኩ የመዳን መንገዶች አይደሉም የምንልበት አንዱ ምክንያት ይህ ነው፡፡ በሌሎቹ ጥያቄዎች ተመልሸ እመጣለሁ፡፡

ሳሂህ ኢማን ነኝ፤ ሰላም!!!!
ቁርአን ኢሣ የሚባለው አካል ግን ፍጡር ነው፡፡

ሱራ 4 ፡ 171
… የመርየም ልጅ አልመሲሕ ዒሳ የአላህ መልክተኛ ወደ መርየም የጣላት «የኹን» ቃሉም ከእርሱ የኾነ መንፈስም ብቻ ነው፡፡ …

ሱረቱል አሊ-ዒምራን 3 ፡ 59
አላህ ዘንድ የዒሳ ምሳሌ እንደ አዳም ብጤ ነው፡፡ ከዐፈር ፈጠረው፡፡ ከዚያም ለርሱ (ሰው) «ኹን» አለው፤ ኾነም፡፡

ሱረቱል አሊ-ዒምራን 3 ፡ 47
ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል᐀ አለች፡፡ ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ አንዳችን በሻ ጊዜ ለርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል አላት፡፡

ሱረቱል አል-በቀራ 2 ፡ 117
ሰማያትንና ምድርን ያለብጤ ፈጣሪ ነው፤ ነገርንም (ማስገኘት) በሻ ጊዜ ለርሱ የሚለው፡- «ኹን ነው፤» ወዲያውም ይኾናል፡፡

ጌታ ኢየሱስ ስቅለቱና ሞቱ፡-

የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ስሙ ሰዎችን ከኃጢአታቸው ለማዳን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ቤዛ መሆኑና መሞቱ በብዙ ምስክሮች የተጣበበ እውነት ነው፡፡ አይሁዶች፣ አይሁድም ክርስቲያንም ያልሆኑ ወገኖች፣ ክርስቲያኖች፣ ወንጌላውያን፣ ሐዋርያት፣ ወዘተ… ለዚህ እማኝ ናቸው፡፡

ማር 15 ፡ 22-37
ትርጓሜውም የራስ ቅል ስፍራ ወደሚሆን ጎልጎታ ወደተባለ ስፍራ ወሰዱት። ከርቤም የተቀላቀለበትን የወይን ጠጅ እንዲጠጣ ሰጡት፤ እርሱ ግን አልተቀበለም። ሰቀሉትም፥ ልብሱንም ማን ማን እንዲወስድ ዕጣ ተጣጥለው ተካፈሉ። በሰቀሉትም ጊዜ ሦስት ሰዓት ነበረ። … ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኸ ነፍሱንም ሰጠ።

ሞቶ ብቻ አልቀረም፡፡ በሦስተውም ቀን ሞትን ድል ነስቶ ተነስቷል፡፡ ይህም በምስክሮች የተጣበበ እውነት ነው፡-

ማቴ 28 ፡ 2-6
እነሆም፥ የጌታ መልአክ ከሰማይ ስለ ወረደ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ቀርቦም ድንጋዩን አንከባሎ በላዩ ተቀመጠ። መልኩም እንደ መብረቅ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበረ። ጠባቆቹም እርሱን ከመፍራት የተነሣ ተናወጡ እንደ ሞቱም ሆኑ። መልአኩም መልሶ ሴቶቹን አላቸው። እናንተስ አትፍሩ የተሰቀለውን ኢየሱስን እንድትሹ አውቃለሁና፤ እንደ ተናገረ ተነሥቶአልና በዚህ የለም፤ የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ።

የቁርአኑ ኢሣ ግን አልሞተም አልተሰቀለም፡፡ ሰዎችን ከኃጢአታቸው ለማዳን የሠራው ምንም ዐይነት የቤዛነት ሥራ የለም፡፡

ሱረቱል አል ኒሳዕ 4 ፡ 157
«እኛ የአላህን መልክተኛ የመርየምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን» በማለታቸውም (ረገምናቸው)፡፡ አልገደሉትም አልሰቀሉትምም፡፡ ግን ለእነሱ (የተገደለው ሰው በዒሳ) ተመሰለ፡፡ …

ሱረቱል አሊ-ዒምራን 3 ፡ 55
አላህም ባለ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ ዒሳ ሆይ! እኔ ወሳጂህ ወደ እኔም አንሺህ ነኝ፡፡ ከነዚያም ከካዱት ሰዎች አጥሪህ ነኝ እነዚያንም የተከተሉህን እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ ከነዚያ ከካዱት በላይ አድራጊ ነኝ፡፡ ከዚያም መመለሻችሁ ወደእኔ ነው፡፡ በርሱ ትለያዩበትም በነበራችሁት ነገር በመካከላችሁ እፈርዳለሁ፡፡

ስለዚህ በዚህ ሚዛን እና መነጽር የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ ክርስቶስ እና የቁርአኑ ኢሣ አንድ አይደሉም ወደሚል መደምደሚያ ያደርሰናል፡፡ ምንም የሚያመሳስላቸውና የጋራ ውክልና የሌላቸው የተለያዩ አካላት ናቸው፡፡ ይህ ደግሞ ቁርአን መለኮታዊ መጽሐፍ ነቢዩም ሙሐመድም የእውነተኛው አምላክ መልእክተኛ አለመሆናቸውን አጋልጧል፡፡

2. "እውን የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ እና የቁርአኑ ኢሣ አንድ ናቸውን?" አንድ ናቸው በሚለው የቁርአን መነጽር

በዚህኛው መነጽር ቁርአን የመጽሐፍ ቅዱሱን ኢየሱስ እና የቁርአኑን ኢሣ አንድ ለማስመሰል ብዙ ጥሯል፡፡ አልተሳካም እንጂ፡፡ ከጽንሰቱ ጀምሮ ያለውን ታሪክ እግር በእግር እየተከታተለ ለማስመሰል ትርክቶችን አንድ ሁለት ብሎ ተይቧል፡፡ እነዚህም ቢሆኑ ቁርአንን ከማጥ አያወጡትም፤ ቁርአን ውስጥ ስለ ኢሣ የተጻፉት ታሪኮች ሁሉም መለኮታዊ መገለጦች ሳይሆኑ ከተለያዩ የእምነት ተቋማት መጽሐፍት በጀሮ ጠገብ ተለቅመው በራስ አባባል ተቀነባብረው የተሰደሩ ታሪኮች ናቸው፡፡ የትኛው ከየትኛው የሃይማኖት መጽሐፍ እንደተወሰደ መዘርዘር በጣም ቀላል ሥራ ነው፡፡ ይሁንና ከጌታ ኢየሱስ ታሪክ ጋር ከተዘረዘሩ ታሪኮች የተወሰነውን ብቻ ለናሙና አስነብባችኋለሁ፡-

የማርያምና የጽንሰት ታሪክ፡-

ሱረቱል አሊ-ዒምራን ውስጥ የጽንሰትና የአስተዳደግ ትርክት ሰፍሯል፡፡ ይህ ከሌላ የተኮረጀ ስለመሆኑ የመጀመሪያውን ፍንጭ የሚሰጠው "የኢምራን ቤተሰብ" የሚለው የቁርአን ምዕራፍ ነው፡፡ እንደ ቁርአን ኢምራን የኢየሱስ እናት የማርያም አባት እንደሆነ ተገልጿል፡፡ (ሱራ 3 ፡ 33-37) ኢምራን ተብሎ የተጠራው የነ ሙሴ አባት አምራም ነው፡፡ ነቢዩ የትኛዋን ማርያም እየጠቃቀሱ እንዳሉ አሁን ግልጽ ነው፡፡ የአምራም ልጅ የሆነችውንና የነ ሙሴ እህት የሆነችውን ማርያም ነው፡፡ ለዚህም ነው በሱረቱል መርየም 19 ፡ 28 ነቢዩ በአላህ ስም እንዲህ ያሉት፡-

"የሃሩን እኅት ሆይ! አባትሽ መጥፎ ሰው አልነበረም፡፡ እናትሽም አመንዝራ አልነበረችም» አሏት፡፡"

ነቢዩ ሙሐመድና አላህ ከ 1500 ዓመታት በላይ ልዩነት ባለው ዘመን ያሉ የሁለት ሰዎችን ታሪክ በዚህ መልኩ ቀላቅለው ያዋቀሩት እንዴት ነው?

ነቢዩ ታሪኮቹን ያወቁት በጀሮ ጠገብ ነበር፡፡ በጊዜው ስለ ማርያምና ስለ ተወለደው መሲህ የራሳቸው ትርክት የነበራቸው ሁለት ሃይማኖቶች ነበሩ፡፡ እናም ከሁለቱ ሃይማኖት ተከታዮች አንድ የሚመስል ግን የተለያየ ይዘት ያለውን ትርክትን ሰምተዋል፡፡ ከዛም እርሳቸው ይህንን ሁለት ግን አንድ የሚመስል ትርክት በመቀላቀል መለኮታዊ ራዕይ እንደ ወረደላቸው አድርገው ለተከታዮቻቸው አበሰሩት፡፡ ነቢዩ ትርክቱን የሰሙት የአዲስ ኪዳን አዋልድ መጽሐፍትን ይጠቀሙ ከነበሩ ክርስቲያን ነን ከሚሉ ወገኖችና የሳቢያን ሃይማኖት ተከታዮች ከነበሩ ሰዎች ነበር፡፡ ይህን ታሪክ ዛሬም በሃይማኖቶቹ መጽሐፍት ውስጥ ሰፍሮ ታገኙታላችሁ፡፡ የአዲስ ኪዳኑ አዋልዱ "የማርያም የልደት ወንጌል (The Gospel of the birth of Mary)" እና የሳቢያኖቹ ደግሞ "የሃራን-ገወኢታ (Haran-Gawaita)" ይሰኛል፡፡ ይህም ቁርአን የተረታ ተረቶች ስብስብ እንጂ መለኮታዊ መገለጥ ያለመሆኑ አንዱ ማሳያ ነው፡፡

ከኢሣ ታሪክ አንድ ልጨምርላችሁ፡፡ ሱረቱል አሊ-ዒምራን 3 ፡ 49፡-

"ወደ እስራኤልም ልጆች መልክተኛ ያደርገዋል፡፡ (ይላልም)፡- «እኔ ከጌታዬ ዘንድ በተዓምር ወደ እናንተ መጣሁ፡፡ እኔ ለናንተ ከጭቃ እንደ ወፍ ቅርፅ እፈጥራለሁ፡፡ በርሱም እተነፍስበታለሁ፡፡ በአላህም ፈቃድ ወፍ ይኾናል፡፡"

ነቢዩ ይህንን ታሪክ ከየት ነው ያመጡት?

ሱረቱል አል-ነሕል 16 ፡ 103
እነርሱም «እርሱን (ቁርኣንን) የሚያስተምረው ሰው ብቻ ነው» ማለታቸውን በእርግጥ እናውቃለን፡፡ የዚያ ወደርሱ የሚያስጠጉበት ሰው ቋንቋ ዐጀም ነው፡፡ ይህ (ቁርአን) ግን ግልጽ ዐረብኛ ቋንቋ ነው፡፡