ለምን አልሰለምኩም? via @like
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሙሐመድ የሰጠው ማስጠንቀቂያ
ብዙ ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እስልምናና ስለ ሙሐመድ ምን እንደሚል ቢጠየቁ የሚሰጡት ምላሽ ምናልባት “ምንም!” የሚል ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ይህ ምላሽ መጽሐፍ ቅዱስን ላጠና ሰው ስህተት መሆኑ በቀላሉ ይገባዋል፡፡ ለዚህም ምክንያቱ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስና በተከታዮቹ የተነገሩ ትንቢቶችና ማስጠንቀቂያዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በብዛት መገኘታቸው ነው፡፡ በርግጥ ስለ እስልምናና ስለ ሙሐመድ በቀጥታ ተጠቅሶ ማስጠንቀቂያ የተሰጠበት ቦታ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መኖሩ አከራካሪ ቢሆንም አጠቃላይ በሆነ መንገድ የተጠቀሱባቸውና ማስጠንቀቂያ የተሰጠባቸው ክፍሎች አያሌ ናቸው፡፡
ጌታ ኢየሱስ እንዲህ አለ፡-
“የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ። ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን? እንዲሁ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያደርጋል፥ ክፉም ዛፍ ክፉ ፍሬ ያደርጋል። መልካም ዛፍ ክፉ ፍሬ ማፍራት፥ ወይም ክፉ ዛፍ መልካም ፍሬ ማፍራት አይቻለውም። መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል ወደ እሳትም ይጣላል። ስለዚህም ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ።” (ማቴዎስ 7፡15-20)
በሌላ ቦታ ላይ ጌታ ኢየሱስ ስለ ዓለም ፍፃሜ ምልክቶች በተናገረበት ክፍል እንዲህ ብሏል፡-
“ብዙ ሐሰተኞች ነቢያትም ይነሣሉ ብዙዎችንም ያስታሉ” (ማቴዎስ 24፡11)
የክርስቶስን መስቀል በማስካድ ብዙዎችን እንደ ማሳቱ መጠን ከሙሐመድ በተሻለ ሁኔታ ከላይ የተጠቀሱት ትንቢቶች እውነት መሆናቸውን ሊያረጋግጥ የሚችል ነቢይ ነኝ ባይ ያለ አይመስለኝም፡፡ እስልምና በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ንፁሃንን ደም በማፍሰስና ዓለምን በሽብር በማስጨነቅ የሐሰተኛ ነቢይ አስተምሕሮ ፍሬ መሆኑን አረጋግጧል፡፡ ሙሐመድ የአንድን አምላክ ስም እየጠራ መምጣቱና ለእነርሱ የመጣውን መገለጥ እየተቃወመ ነገር ግነ በሙሴና በሌሎች ቅዱሳን ነቢያት አምላክና መንፈስ እንደተላከ መናገሩ በጎችን ለማወናበድ የተጠቀመበት ለምድ እንጂ እውነት እንዳልሆነ መታወቅ አለበት፡፡
“ይህም ድንቅ አይደለም፤ ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣልና። እንግዲህ አገልጋዮቹ ደግሞ የጽድቅን አገልጋዮች እንዲመስሉ ራሳቸውን ቢለውጡ ታላቅ ነገር አይደለም፤ ፍጻሜአቸውም እንደ ሥራቸው ይሆናል።” (2ቆሮ. 11፡14-15)
እስልምና የእውነተኛ ነቢያት መመዘኛ የለውም፡፡ ሙስሊሞች የሙሐመድን እውነተኛ ነቢይነት ለማረጋገጥ ለሚደረግ ምርመራ ትዕግስት የላቸውም፡፡ ከሙሐመድ በኋላ ብዙ ነቢያት ነን ባዮች የተነሱ ቢሆንም እነዚህን ወገኖች ላለመቀበል ብቸኛው መመዘኛቸው ሙሐመድ የመጨረሻው ነቢይ እንደሆነ ማመናቸው ብቻ ነው፡፡
በቁርአን ውስጥ ነቢያትን ማመንና መቀበል እንደሚያስፈልግ በተደጋጋሚና በአፅንዖት ተነግሯል (4:150-151፣ 2:285፣ 3:161፣ ወዘተ.)፡፡ ነገር ግን ሁሉንም ነቢያት ማመንና መቀበል እንደሚገባ አሰልቺ በሆነ ድግግሞሽና በማስፈራርያዎች በታጀበ ሁኔታ የተነገረ ቢሆንም ስለ ሐሰተኛ ነቢያት የተሰጠ የረባ ማስጠንቀቂያ አለመኖሩ አስገራሚ ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ግን እውነተኛ ነቢያትን ማመንና መቀበል እንደሚገባ የተነገረውን ያህል ከሐሰተኞች ነቢያትም መጠንቀቅ እንደሚያስፈልግ በተደጋጋሚና በአፅንዖት ተነግሯል ዘዳ. 13, 18:20-22፣ ኤር. 5:31፣ 14:14፣ ኤር. 23:9-40፣ ኤር. 28፣ ሕዝ. 13፣ ማቴ. 24:11፣ 1ቆሮ. 14:29፣ 2ጢሞ 4:3፣ 2ጴጥ. 2:1፣ ራዕይ 2:20፣ 16:13፣ ወዘተ.)፡፡
ይህ ማስጠንቀቂያ በቀደሙት መገለጦች ውስጥ በተደጋጋሚ የተነገረ ሆኖ ሳለ የቁርአን ደራሲ በዚህ ጉዳይ ላይ ዝምታን መምረጡ ጥርጣሬን ያጭራል፡፡ ከቀደሙት ቅዱሳት መጻሕፍት ጋር እምብዛም ትውውቅ ያልነበራቸው ተከታዮቹ ስለ ሐሰተኞች ነቢያት መኖር ማወቃቸው የእርሱን ሁኔታ በንቃት መከታተልና መመዘን እንዲጀምሩ እንደሚያደርግ ሙሐመድ አስተውሏል፡፡ የሐሰተኞች ነቢያት መኖርን ከስሌቱ ውጪ በማድረግ በሁሉም ነቢያት የማመንን አስፈላጊነት በተደጋጋሚ በመናገር በእርሱ ነቢይነት ማመን ግዴታ እንደሆነ በማስመሰል ተከታዮቹ አዙረው እንዳያስቡ አድርጓቸዋል፡፡
አንዳንድ ጊዜ ዝምታ ራሱ ንግግር ነው፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ ነቢያት በተጻራሪ ሙሐመድ ስለ ሐሰተኞች ነቢያት ዝምታን መምረጡ የሚያስተላልፈው ግልፅ መልእክት አለ፤ ሙሐመድ እውነተኛ የእግዚአብሔር ነቢይ አይደለም! http://www.ewnetlehulu.org/am/muhammad/bible-warning-about-muhammad/

ኢየሱስ አምልኮ የተገባው አምላክ ነው!
በዳንኤል ላይ የተጠቀሰውን “የሰው ልጅ” በተመለከተ ለሙስሊም ሰባኪያን የተሳሳተ ትርጓሜ የተሰጠ እርማት
ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምልኮ የተገባው አምላክ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በበርካታ ቦታዎች ላይ ይናገራል፡፡ ከእነዚህ መካከል አንዱ በትንቢተ ዳንኤል 7፡13-14 ላይ የሚገኝ ሲሆን ለሐሰት አስተማሪዎች የራስ ምታት ከሆኑት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃዎች መካከል ቀዳሚው ነው፡፡ ይህ ጥቅስ በብሉይ ኪዳን ውስጥ መገኘቱና ከመሲሁ መምጣት በፊት የተነገረ መሆኑ የኢየሱስ አምላክነት ከእርገቱ በኋላ የተፈጠረ አስተምህሮ ሳይሆን የነቢያት አስተምህሮ መሆኑን በማረጋገጥ እስልምናን የሚያሸማቅቅ በመሆኑ ሙስሊም ሰባኪያን ለጥቅሱ የተለየ ትርጉም ለመስጠት የተለያዩ ጥረቶችን አድርገዋል፡፡ ነገር ግን ከረበናተ አይሁድና ከተለያዩ የኑፋቄ ቡድኖች የተቀዱ አሮጌ ሙግቶችን ከማቅረብ በዘለለ ቀደም ሲል ክርስቲያኖች መልስ ያልሰጡበትን አዲስ ሐሳብ አቅርበው አያውቁም፡፡ በዚህ ጽሑፍ አንድ አብዱል ከዚያም ከዚህም የቃረማቸውን ሙግቶች ያቀረበበትን ጽሑፍ እንፈትሻለን፡፡ ሙስሊም ወገኖቻችን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምልኮ የተገባው ዘላለማዊ ንጉሥ መሆኑን በመረዳት ተገቢውን ክብር እንዲሰጡት መንፈስ ቅዱስ ይህንን ጽሑፍ ይጠቀም ዘንድ ጸሎታችን ነው፡፡ ሙሉ ጽሑፉን ለማንበብ ሊንኩን ይከተሉ 👇 http://www.ewnetlehulu.org/am/son-of-man

ኢየሱስ የሰናፍጭ ቅንጣት ከምድር ዘር ሁሉ እንደምታንስ መናገሩ ስህተት ነውን?
አንድ ሙስሊም ሰባኪ የወንጌሉ ኢየሱስ ግብርናን በተመለከተ “ስህተቶችን ሠርቷል” የሚል ጽሑፍ አስነብቦናል፡፡ የመጀመርያው ውንጀላ ኢየሱስ በለሲቱ ፍሬ እንዳላትና እንደሌላት “አለማወቁ” የሚል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከሰናፍጭ ቅንጣት ያነሱ አዝዕርት በምድር ላይ መኖራቸውን “አለማወቁ” የሚል ነው፡፡ የመጀመርየውን ከዚህ ቀደም ምላሽ ስለሰጠንበት ራሳችንን መድገም አያሻንም፡፡ በዚህ ጽሑፍ ሁለተኛውን ጥያቄ እንመልሳለን፡- 👇
http://www.ewnetlehulu.org/am/mustard-seed

የሙሐመድ ኩረጃ
ሙሐመድ እውነተኛ ነቢይ እንዳልሆነ ከሚያሳዩ ማስረጃዎች መካከል አንዱ በዙርያው ከነበሩ ባሕሎችና ሃይማኖታት የተለያዩ ሐሳቦችን በመቅዳት ከሰማይ የመጣለት መገለጥ አስመስሎ ማቅረቡ ነው፡፡ የእስልምና ጀማሪ የሆነው ሙሐመድ ምንም ዓይነት ኦሪጅናል መልእክት ያላመጣ ሲሆን ከተለያዩ ምንጮች የቃረማቸውን ነባር አስተምህሮዎች፣ ታኮችና ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች መለኮታዊ መገለጥ በማስመሰል ሲያስተምር ነበር፡፡ በዘመኑ የነበሩት አረቦች እንኳ ይህንን እውነታ በመገንዘብ የሙሐመድን ትምህርት “…የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች ናቸው” ይሉ እንደነበር በቁርአን ውስጥ በተደጋጋሚ ተጽፏል (ሱራ 83፡13፣ 68፡15፣ 46፡17)፡፡ ይህንን የሙሐመድ የመቅዳት ተግባር እስላማዊ ምንጮች እንዲህ ሲሉ ይናዘዛሉ፡- 👇
http://www.ewnetlehulu.org/am/muhammad-plagiarism/

ጌታችን ኢየሱስ “የፍጥረት በኩር” ተብሎ መጠራቱ የሚያሳየው ፈጣሪነቱን ወይንስ ፍጡርነቱን?
ሙስሊም ሰባኪያን ከይሖዋ ምስክሮች በመቅዳት በማሕበራዊ ገፆች ላይ ከሚያስጮኋቸው ሙግቶች መካከል አንዱ በቆላስያስ 1:15 ላይ የሚገኘውን ቃል መሠረት ያደረገ ሲሆን “ኢየሱስ የፍጥረት በኩር” መባሉ ፍጡር መሆኑን ያሳያል ይሉናል፡፡ እውን እነርሱ እንደሚሉት ይህ ጥቅስ ኢየሱስ ፍጡር መሆኑን ያሳይ ይሆን? በዚህ ጽሑፍ ይህንን ሙግት እንፈትሻለን፡፡ 👇
http://www.ewnetlehulu.org/am/prototokos

አንድ አብዱል እንዲህ ሲል ጠይቋል:- ትንቢት ሆሴዕ 1፡2 “እግዚያብሔር በሆሴዕ መናገር በጀመረ ጊዜ፣ እግዚአብሔር “ምድሪቱ ከእግዚአብሔር ተለይታ ታላቅ ምንዝርና እያደረገች ስለ ሆነ፣ ሄደህ አመንዝራ ሴት አግባ፤ የምንዝርና ልጆችንም ለራስህ ውሰድ” አለው ይላል፡፡ አምላክ በአመንዝራነት ያዛልን? በዝሙት ላይ የፈጣሪ አቋም ይህ ነውን?
-----
መልስ:-
እግዚአብሔር የሆሴዕን ሕይወት ለእስራኤል ማስተማርያ ለማድረግ ስለፈለገ አመንዝራ ሴት እንዲያገባ አዘዘው እንጂ አመንዝር አላለውም፡፡ ሆሴዕ ያገባት ሴት አመንዝራና ምግባረ ብልሹ ብትሆንም እርሷን የሚወድበትና የሚታገስበትን ፀጋ ሰጥቶታል፡፡ ዛሬም በማሕበረሰባችን ውስጥ ከእንደዚህ ዓይነት ሴቶች ጋር በመጋባት የሚኖሩ ወገኖች አሉ፡፡ ይህ የግለሰቦቹን ጥንካሬና ታጋሽነት የሚያሳይ እንጂ በፍፁም የሚያስወቅስ አይደለም፡፡ የሆሴዕ ታሪክ እስራኤላውያን በእግዚአብሔር ላይ በማመፅ ሌሎች አማልክትን ቢያመልኩም እንደታገሳቸውና እንደወደዳቸው የሚያሳይ ትዕምርታው ትንቢት ነው፡፡ ታሪኩ ዘይቤያዊ እንጂ በተግባር የተፈፀመ እንዳልሆነም የሚናገሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት ብዙዎች ናቸው፡፡

Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Balthazar)
ምድር ዝርግ ናት?
የምድርን ቅርፅ በተመለከተ ቁርአን እንዲህ ይላል፡-
“(እርሱ) ያ ለናንተ ምድርን ምንጣፍ ሰማይንም ጣራ ያደረገ ነው፤ ከሰማይም (ከደመና) ውሃን ያወረደ በርሱም ከፍሬዎች ለናንተ ሲሳይን ያወጣ ነው፡፡” (ሱራ 2፡22)
“እርሱም ያ ምድርን የዘረጋ በሷም ተራራዎችንና ወንዞችን ያደረገ በውስጧም ከፍሬዎች ሁሉ ሁለት ሁለት ዓይነቶችን ያደረገ ነው፡፡ ሌሊትን በቀን ይሸፍናል፡፡” (ሱራ 13፡3)
“ምድርንም ዘረጋናት፡፡ በውስጧም ኮረብታዎችን ጣልናባት፡፡ በውስጧም (የተለካን) በቃይ ሁሉ አበቀልንባት፡፡” (ሱራ 15፡19)
“(እርሱ) ያ ምድርን ለእናንተ ምንጣፍ ያደረገላችሁ፣ በእርሷም ውስጥ ለእናንተ መንገድን ያገራላችሁ” (ሱራ 20፡53)
“ወደ ምድርም እንዴ እንደተዘረጋች (አይመለከቱምን?)” (ሱራ 88፡20)
——-
እነዚህ ጥቅሶች ምድር ዝርግ መሆኗን በማያሻማ ቃል ይናገራሉ፡፡ ኡስታዝ ሐሰን ታጁ ለዚህ ጥያቄ እንዲህ በማለት መልስ ሰጥተዋል፡-
በዚህ አንቀጽ ምድር ዝርግ (ጠፍጣፋ) መባሏ ከሳይንስ እውነታ ጋር ይጋጫልን? በእርግጥ አይጋጭም፡፡ ቁርአን ሁለቱንም አገላለጽ ተጠቅሟል፡፡
ምድር ክብና እንቁላል ቅርጽ መሆኗን በተከታዩ አንቀጽ ይገልጻል፡-
وَالْأَرْضَ بَعْدَ ذَٰلِكَ دَحَاهَا
“ምድርንም ከዚህ በኋላ ዘረጋት፡፡” (አል ናዚአት፣ 30)
‹‹ደሃ›› የሚለው የአረብኛ ቃል ሙሉ ክብ ያልሆነ፣ በአንድ ወገኑ የረዘመ (ልክ እንቁላል ቅርጽ) ክብ ማለት ነው፡፡ በአማርኛው የቅዱስ ቁርአን ትርጉም ‹ዘረጋ› ተብሎ መተርጎሙ የቃሉን መንታ መልእክት መያዝ ያመለክታል፡፡
በእርግጥም እውነተኛው የመሬት ቅርጽም እንቁላል መሳይ ነው፡፡ ይህ ግን ሳይንስን ለተረዱ ሰዎች የሚገባ ነው፡፡ አብዛኛው ሰው ግን በአይኑ ሲያያት ዝርግ ትመስላለች፡፡ ቁርአን ይህንንም አልዘነጋም፡፡ የሚያናግረው የሳይንስ ምሁራንን ወይም የ20ኛው ክፍለ ዘማን ሰዎችን ብቻ ሳይሆን በየትኛውም ዘመንና ቦታ የሚኖሩ የሰው ልጆችን ነው፡፡ እናም ‹‹ምድርን በመዘርጋት ለኑሮ እንድትመች እንዳደረግና አስተውሉ›› አለ፡፡ ማንም ሰው ሊገባው በሚችል ቋንቋ፡፡ እግረ መንገዱን ግን ክብነቷን በመናገር ሳይንሳዊ ተአምር ቋጠረ፡፡ ተከታዩን አንቀጽ እንመልከት፡-
يُكَوِّرُ اللَّيْلَ عَلَى النَّهَارِ وَيُكَوِّرُ النَّهَارَ عَلَى اللَّيْلِ وَسَخَّرَ الشَّمْسَ وَالْقَمَرَ
“ሌሊትን በቀን ላይ ይጠቀልላል፡፡ ቀንንም በሌሊት ላይ ይጠቀልላል፡፡” (አል ዙመር 5)
‹መጠቅለል› (ተክዊር) የሚለው ቃል ክብ ለሆነ ነገር እንጅ ለዝርግ ነገር አይደለም፡፡ ይህም አንቀጽ የመሬትን ክብነት ይገልጻል፡፡ (ገፅ 186-187)
———-
እስቲ ይህንን ሐተታ ጠጋ ብለን እንመልከት፡፡ እውን ኡስታዙ እንዳሉት ቁርአን የመሬትን ክብ መሆን ይናገር ይሆን?
የምድር ቅርፅ ከዕንቁላል ይልቅ ወደ ኳስ ቅርፅ የቀረበ መሆኑን ማንኛውም የጂኦግራፊ ተማሪ ያውቃል፡፡ የምድር ቅርፅ እንደ ዕንቁላል ሞላላ አይደለም፡፡ ሁለቱ ዋልታዎች የጠፍጣፋነት መልክ ሲኖራቸው በስፋት ረገድ ከምድር ወገብ ጋር ያላቸው ልዩነት በጣም ኢምንት ነው፡፡ ስለዚህ ይህንን ትርጓሜ ከሳይንስ አንጻር ስንመዝነው ተቀባይነት የለውም፡፡ ቁርአን የፈጣሪ መገለጥ ነው ከተባለ ወደ እውነት በከፊል የተጠጋ ሐሳብ ሳይሆን ፍፁም እውነትን መናገር መቻል አለበት፡፡
‹ደሃሃ› የሚለው የአረብኛ ቃል ትርጉም፡
ሱራ 79፡30
وَالْأَرْضَ بَعْدَ ذَٰلِكَ دَحَاهَا ‹‹ወል ዐርደ በዐዳ ዛሊከ ደሃሃ››
በአማርኛ ቁርአን “ምድርንም ከዚህ በኋላ ዘረጋት” ተብሎ ተተርጉሟል፡፡ ብዙ የእንግሊዘኛ ትርጉሞችም ምድር ዝርግ መሆኗን በሚያመለክት ሁኔታ ተርጉመውታል፡፡ ለምሳሌ፡-
* And after that He spread the earth. (Sahih International)
* And the earth, moreover, hath He extended (to a wide expanse); (Yusuf Ali)
* And afterwards stretched forth the earth, (J M Rodwell)
* And after that He spread the earth, (Pickthall)
* And the earth - after that He spread it out, (Arberry)
* And the earth, He expanded it after that. (Shakir)
አንዳንድ ሙስሊሞች ‹ደሃ› የሚለው ቃል ‹ዕንቁላል› የሚል ትርጉም ካለው ‹ዱሂያ› ከሚለው ቃል ጋር ስለሚመሳሰል ‹የዕንቁላል ቅርፅ› ተብሎ መተርጎም እንዳለበት ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን ትክክለኛው ትርጉም ‹መዘርጋት› የሚል ነው፡፡ ከጥንት ጀምሮ ሙስሊም ሊቃውንት ቃሉን በዚሁ መንገድ ሲተረጉሙት ኖረዋል፡፡ የቃሉ ትክክለኛ ትርጉም አቶ ሐሰን እንዳሉት ቢሆን ኖሮ እነዚህ ሙስሊም ሊቃውንት ሳይንሳዊ የሆነውን የቃሉን ትክክለኛ ትርጉም በመተው ኢ-ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ስለምን ይተረጉሙት ነበር?
ጀለላይን የተሰኙ ሁለት ሙስሊም ሊቃውንት ይህንን ጥቅስ ሲያብራሩት እንዲህ ብለዋል፡-
“ምድርንም ከዚህ በኋላ ዘረጋት” ማለት ዝርግ አደረጋት ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም የተፈጠረችው ከሰማይ በፊት ነበር፣ ነገር ግን አልተዘረጋችም ነበር፡፡
የመጀመርያዎቹ ሙስሊሞች ምድር ዝርግ ሆና ‹ኑን› በተባለ ዓሣ ነባሪ ጀርባ ላይ እንደተቀመጠች ያምኑ ነበር፡፡ ይህንን በተመለከተ ኢብን ከሢር የተሰኘ ሙስሊም ሊቅ እንዲህ ሲል ጽፏል፡-
…ኢብን አባስ እንዳስተላለፈው […] ከዚያም አላህ ‹ኑን› የተባለውን ከፈጠረ በኋላ ሰማይ የተፈጠረበት ጭስ እንዲወጣ አደረገ፡፡ ከዚያም ምድር በኑን ጀርባ ላይ ተዘረጋች፡፡ ከዚያም ኑን ስለደነበረ ምድር ማረግረግ ጀመረች፤ ነገር ግን (አላህ) ምድርን እንዳትንቀሳቀስ አድርጎ በተራሮች ቸከላት… Tafseer Ibn Katheer; Online Edition: http://altafsir.com/Tafasir.asp?tMadhNo=0&tTafsirNo=74&tSoraNo=79&tAyahNo=30&tDisplay=yes&UserProfile=0
ኢብን አቡ ኑጃኢህ እንደተናገረው ኢብን አቡ በኪር በሙጃሂድ እንዲህ ተብሎ ተነግሮት ነበር፣ “ኑን ከሰባቱ መሬቶች በታች የሚገኝ ታላቁ አሣ እንደሆነ ይነገራል፡፡” በተጨማሪም አል ባግሃዊ (አላህ ነፍሱን ያሳርፋትና) እንዲሁም ሌሎች ሐታቾች እንደተናገሩት በዚህ ዓሣ ጀርባ ላይ ውፍረቱ ከሰማይና ከምድር የሚበልጥ ትልቅ ዓለት አለ፡፡ ከዚህ ዓለት በላይ ደግሞ አርባ ሺህ ቀንዶች ያሉት ኮርማ ቆሟል፡፡ በዚህ ኮርማ ላይ ሰባቱ መሬቶችና በውስጣቸው የሚገኙት ሁሉ ተቀምጠዋል፡፡ Tafseer Ibn Katheer; Online Edition: http://quran.al-islam.com/Tafseer/DispTafsser.asp?l=arb&taf=KATHEER&nType=1&nSora=68&nAya=1
———
ከነዚህ ሊቃውንት በተጨማሪ አል-ጠበሪና አል-ቁርጡቢን የመሳሰሉት ሌሎች ሙስሊም ሊቃውንት ተመሳሳይ ዘገባዎችን አስተላልፈዋል፡፡ በዘመናች የሚገኙ የቁርአንን ሐሳብ በሚገባ የተገነዘቡ ሙስሊም ሊቃውንት ምድር ዝርግ መሆኗን በአፅንዖት ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡ ለምሳሌ ያህል የሳዑዲ አረብያ ዋና ሙስሊም ሊቅ ሼኽ አብደል-አዚዝ ኢብን ባዝ እንዲህ ማለታቸውን ኒውዮርክ ታይምስ ዘግቧል፡-

“ምድር ዝርግ ናት፡፡ ክብ መሆኗን የሚናገር ማንኛውም ሰው ቅጣት የሚገባው አምላክ-የለሽ ነው፡፡” Yousef M. Ibrahim, "Muslim Edicts take on New Force", The New York Times, February 12, 1995, p. A-14.
———
ከላይ የሰጠናቸው ማስረጃዎች እንዳሉ ሆነው ቁርአን ምድር ክብ መሆኗን በመናገር ከዘመናዊው ሳይንስ ጋር ተስማምቶ ቢገኝ እንኳ ተዓምራዊ ሊሆን የማይችልበት አንድ ትልቅ ምክንያት አለ፡፡ እርሱም ምድር ዝርግ አለመሆኗና ክብ መሆኗ መሐመድ ከመወለዳቸው ከብዙ ክፍለ ዘመናት በፊት የታወቀ መሆኑ ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል ፓይታጎረስ የተሰኘው ግሪካዊ የሒሳብ ሊቅ (ሕይወቱ ያለፈው 497 ዓ.ዓ. ነው) መሬት፣ ጨረቃና ሌሎች የሕዋ አካላት ክብ መሆናቸውን ያምን ነበር፡፡ ከርሱ ቀጥሎ በነበረው ክፍለ ዘመን የኖረው ፊሎላውስ የተሰኘ ሌላ ግሪካዊ ሊቅ ተመሳሳይ እምነት ነበረው፡፡ በተጨማሪም አርስጣጣሊስ (አርስቶትል) የተሰኘው ዝነኛ ግሪካዊ ፈላስፋ (384-322 ዓ.ዓ.) ምድር ክብ መሆኗን በማስረጃዎች አስደግፎ አስተምሮ ነበር፡፡ ይህ እንግዲህ መሐመድ ከመወለዳቸው ቢያንስ ከ900 ዓመታት በፊት ነው፡፡ ነገር ግን ከእነርሱ የሚቀድም የምድርን ክብ መሆን የሚናገር ሌላ ምንጭ አለ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡-
“እርሱ በምድር ክበብ ላይ ይቀመጣል፥ በእርስዋም የሚኖሩት እንደ አንበጣ ናቸው፤ ሰማያትን እንደ መጋረጃ የሚዘረጋቸው እንደ ድንኳንም ለመኖርያ የሚዘረጋቸው…” (በኢሳይያስ 40፡22)
“ሰማዮችን በዘረጋ ጊዜ አብሬ ነበርሁ፥ በቀላያት ፊት ክበብን በደነገገ ጊዜ…” (ምሳሌ 8፡27)
“ሰሜንን በባዶ ስፍራ ላይ ይዘረጋል፥ ምድሪቱንም በታችዋ አንዳች አልባ ያንጠለጥላል፡፡” (ኢዮብ 26፡7)
የተጠቀሱት ሦስቱም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ግሪካውያኑ ፈላስፎች ከኖሩበት ዘመን የቀደሙ ናቸው፡፡

🔥1
ይድረስ ለወሒድ ዑመር
ለ… በፍየል የተበላ ቁርአን አለን? የተሰጠ ምላሽ
"ረምላ ነኝ የረሱል ወዳጅ" በሚለው የFB መጠሪያው ሰሞኑን "በፍየል የተበላ ቁርአን አለን?" በሚል ርዕስ የለጠፈውን ጽሑፍ አነበብኩ፡፡ አበው እንደ ወሂድ አይነቷን ‘ይሉሽን ብትሰሚ ገበያ ባልወጣሽ’ ያሏትን ብሂል አስታወሰኝ፡፡ ሰው አዋቂ ነው ስለተባለ ብቻ እንደ ወተት ዝንብ ጥልቅ እያለ ስለሁሉም መናገር ተገቢ አይደለም፡፡ አንዳንዴም ዝም ይባላል፡፡ ሁሉም ሊታወቅ ስለማይቻል ብቻ ሳይሆን እንደገና ሊያስተኩስ ስለሚችልም፡፡ ከተናገረም ቅን ልብ ይዞ እውነት ላይ በመቆም በእውቀት ጨፍ ብሎ ቢሆን ደግሞ መልካም ይሆናል፡፡ እርሱ ግን ስለ ሁሉም እንደ አዋቂ ለመናገር ሲሞክር ቡጉር ያለውን አጠራለሁ ብሎ ኢስላም በቁንጭር ቁስል መመታቱን ለአንባቢዎቹ ፍንትው አድርጎት አረፈው፡፡ አወቅሽ አወቅሽ ቢሏት አሉ! ደግሞም የጽሑፉን መሪ ቃል አላህ ላያደርገው ወይም ያላደረገውን እንዲሁ ዝም ብሎ የተናገረውን እንዲሁም ከወሂድ ቀደም ያሉት ደጋግመው በኩራት የሚጠቅሷትን ሱራ 15 ፡ 9ን አድርጓል፡፡ እንግዲህ ሽምጥጥ አድርገህ የምትክደው ቢሆንም ለትውልድ በጤና መተላለፍ ያልቻለው ይኸው አላህ ይጠብቀዋል ብለህ የጠቀስክለት ቁርአን ብቻ መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ከሆነ መሰነባበቱን ታውቀዋለህ፡፡ ለማንኛዋም ብዕሬን እንዳነሳ ወደዳረገችኝ ወደ ፍየሏ ልመለስ፡-
ወሒድ ከአይሻ በተላለፈው ሐዲስ ላይ ተመስርቶ በቁርአን ጉድለት ላይ ለሚነሳው ሙግት መልስ ይሆንልኛል በማለት የጻፈውን አንብቤዋለሁ፡፡ ጽሑፉ ሙሉ በሙሉ በፍጹም ክህደት እና እውቀት አጠርነት የተጻፈ ለመሆኑ የእውቀት ባለቤቶች ሁሉ የሚያረጋግጡት ነው፤ እስኪ እንድ በአንድ እየነቀስን እንየው፡-
ክህደት አንድ፡-
የመጀመሪያው ክህደትና እውቀት አጠርነት ‘ሃዲስ ከመነሻው ደይፍ ضَعِيْف ማለትም ደካማ ከሚባሉት ነው’ ማለቱ ነው፡፡ ሐዲሱ ደኢፍ የተባለው በሐዲስ ሊቃውንት ሳይሆን በወሒድ ነው፡፡ ኢብን ማጃህን ጨምሮ ሁሉም የሐዲስ ሊቃውንት እንደተናገሩት የሐዲሱ ደረጃ ደህና (ሐሰን) የሚባል ነው፡፡
ሱና ኢብን ማጃሀ ቅጽ 3፣ ገጽ 114
ሁለተኛ ክህደት፡-
"ይህ ትረካ ላይ ሚሽነሪዎች የተምታታባቸው ስለ መውገርና አስር ማጥባት ጥቅስ መውረዱና መጻፉ ነው፣ ሲጀመር በነብያችን ላይ ሲወርድ የነበረውና ሲጻፍ የነበረው ቁርአን ብቻ ነው ማነው ያለው? ሃዲሰል ነበውይና ሃዲሰል ቁድስይስ ተንዚል አይደሉምን? ጥቅሱ ላይ ምንም ስለ ቁርአን አንቀጽ የተነገረ ነገር የለም፣ ታዲያ ስለምንድን ነው የሚናገረው? ከተባለ የመውገርና አስር ማጥባት ጥቅስ በነቢያችን የተነገረ የነቢያችን ሃዲስም ጭምር ነው፣"
በእርግጥ የተምታታበት ወይም ለማታታት የሞከረው ግልጽ ክህደትንም የፈጸመው ራሱ ወሒድ ነው፡፡ ለዚህ በርካታ ማስረጃዎችን አንድ ሁለት ማለት ይቻላል፡-
1. ነቢዩ በሕይወት በነበሩበት ዘመን ወረደና ተጻፈ ይባል የነበረውና የሚወርዱ የቁርአን አንቀጾች እንጂ ሐዲስ አልነበረም፡፡ ሐዲስን መጻፍ አለተጀመረም፡፡ አንድም የሐዲስ አሰባሳቢ በማሰባሰብ ሥራው ወቅት ከተጻፈ ነገር ላይ ሐዲሳትን እንዳገኘና እንደወሰደ የተናገረም የለም፡፡ ታዲያ ሐዲስ መጻፍ ባልተጀመረበት እንዴት የተጻፈው ሐዲስ ነው ሊባል ይችላል? ስለዚህ ሐዲሱ የሚናገረው ስለ ቁርአን አንቀጽ ብቻ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡
2. የሐዲስ ሊቃውንቱ ሐዲሱ ስለ ቁርአን አንቀጽ እንደሚናገርና እንደተሻረ እያመኑ እንዴት ሐዲስ ነው ሊባል ተቻለ? እውቀት ካላጠረ ወይም ለመካድ ካልታሰበ በስተቀር፡፡ ለማንኛውም በዚህ ምክንያት የቁርአን ፀሐፊዎች ቁርአን ውስጥ ሳያካትቱት እንደቀሩ ያስረዳሉ፡፡
Comments:
a. These are such Verses that their recitation has been abrogated, while the rule remained in force; therefore, the Companions did not write it in the copy of the Quran. (Sunan Ibn Majah vol 3, page 114)
3. ከሊፋ ኡመርም ቢሆን ወሒድ በጠቀሳቸው ሐዲሶችና በሌሎቹ የሐዲስ አሰባሳቢዎች የተላለፈው እንደሚያሳየው የቁርአኑ አካል እንደሆነ እንደሚያምን እንጂ ከአይሁድ መጽሐፍ ያገኘውን የቁርአን አካል ለማድረግ እንደሞከረ አይናገሩም፡-
ሙህታዛር ካንዝ አል-ኡማል ቅጽ 2 ገጽ 2፣ ሱና ማሊክ ሙዋታ 41 ፡ 8
ሁዘይፋህ ሲናገር፡- ኡመር በሱረቱል አል-አሕዛብ ውስጥ ስንት አንቀጾች ይገኛሉ? ብሎ ጠየቀኝ፡፡ እኔም ሰባ ሁለት ወይም ሰባ ሶስት አንቀጾች አልኩት፡፡ እርሱም ሱረቱል አል-አሕዛብ እንደ ሱረቱል አል-በቀራ 287 አንቀጾችን እንደያዘው እረጅም ነበር፤ በዛም ውስጥ አመንዝራን በድንጋይ በመውገር መቅጣትን የሚገልጸው አንቀጽ ነበር አለ፡፡
ክህደት ሦስት፡-
"ስለዚህ የውግራት አንቀጽ በአላህ ቅዱስ መጽሐፍ በቁርአን አለ፦ 4:15-16…"
ወሒድ ይህንን አንቀጽ ከቡኻሪ መጽሃፍ 82፣ ሃዲስ 816 ጋር አያይዞ ጠቅሷል፡፡ ከወሒድ በቀር እንዲህ ያደረገ ሌላ የለም፡፡ ይህ ደግሞ ሰውየው ቁርአኑን ይሁን ሐዲሱን እንደወደደ ለራሱ እንደሚመቸው የሚቀድ መሆኑን ያሳያል፡፡ እርሱ እንዳለው ይሁን ቢባል የቁርአን አንቀጹ ስለ መወገር የሚናገር ከሆነ የቁርአን ተንታኞች ለምን አንቀጹ በመወገር አንቀጽ እንደተሻረ ሊናገሩ ቻሉ? የመውገርን አንቀጽ በመውገር አንቀጽ መሻር ምን ማለት ይሆን? ማን ይታመን ወሒድ ወይስ ኢብን አባስ? ወሒድ ወይስ ኢብን ካሲር?
"Ibn `Abbas said, "The early ruling was confinement, until Allah sent down Surat An-Nur (chapter 24) which abrogated that ruling with the ruling of flogging (for fornication) or stoning to death (for adultery).'' (ተፍሲር ኢብን ከሲር ቅጽ 3፣ ገጽ 400-401)
"Imprisoning a free, married woman who commits fornication until she dies in prison was later abrogated by stoning." (ተፍሲር ኢብን አባስ ገጽ 34)
ይህ እውቀት አጠርነት ብቻ ሳይሆን ግልጽ ክህደትና አንባቢን የማጭበርበር ተግባር ነው፡፡ በዚህ ኢስላምን ከሞጋቾቹ የሚታደገው መስሎት ይሆን? በዚህስ በወሒድ የማጭበርበር ተግባር የሚደሰተውና የሚሸልመው አምላክ ምን ዓይነት ይሆን?
ለማንኛውም አመንዝራን በድንጋይ ወግሮ መግደልን በሚመለከት ቁርአን ውስጥ ሐሳቡ ያለው ወሒድ እንዳለው በሱራቱል አል-ኒሳዕ 4 ፡ 15-16 ሳይሆን ሁሉም የኢስላም ሊቃውንትና ሳሂህ የሆኑት ሐዲሳት የሚስማሙበት በሱረቱል አል-ማኢዳህ 5 ፡ 41-48 ባለው የቁርአን ክፍል ላይ ነው፡፡ ወሒድ የጠቀሰው የቡኻሪ ሐዲስ ራሱ የዚሁ የአል-ማኢዳህ ሐሳብ አስባብ ነው፡-
ሰሂሀል ቡሃሪ መጽሃፍ 23 ሃዲስ 413
Narrated ‘Abdullah bin ‘Umar : The Jew brought to the Prophet a man and a woman from amongst them who have committed illegal sexual intercourse. *He ordered both of them to be stoned to death*.
የዚህን የቁርአን ሐሳብ የወረደበትን አስባብ የጻፉ ሊቃውንትም እንዲህ በሚል አስፍረውታል፡-

👍1
Asbab Al-Nuzul [5:41-47]
“One day, the Messenger of Allah, Allah bless him and give him peace, passed by a Jewish man who had just been flogged and had his face darkened with coal. He summoned the Jews and asked them: 'Is this what your Scripture decrees as punishment for the adulterer?' 'Yes!' they replied. He then summoned one of their doctors and asked him: 'I implore you by Allah who has sent the Torah to Moses, is this what your Scripture decrees as punishment for the adulterer'. He said: 'No! And if you had not implored me by Allah, I would not tell you. Our Scripture rules that the punishment of the adulterer is stoning. But it became widespread among our notables. Initially, when one of the notables committed adultery, we left him unpunished while we applied stoning on the communality in cases of adultery. Then we decided to look for a punishment that was applied on both the notables and communality of people. And so we agreed on darkening the face with coal and flogging to replace stoning. The Messenger of Allah, Allah bless him and give him peace, said: 'O Allah! I am the first to reapply your command after they had suspended it'. And he ordered that the Jewish man be stoned.
ኢማም ሙስሊምም ታሪኩን እንዲህ ገልጸውታል፡-
ሳሂህ ሙስሊም ቅጽ 4፣ 4437
በዝሙት ኀጢአት የተከሰሱ አይሁድና አይሁዳዊት ወደ አላህ መልእክተኛ አቀረቡ፡፡ ነቢዩም እንዲህ ሲሉ ጠየቋቸው፤ በእናንተ በተወረደው በተውራቱ ለእንዲህ አይነት ኀጢአት የተወሰነው ቅጣት ምንድን ነው? ሲመልሱም ቀሳውስቶቻችን ቅጣቱን የገለጹልን ጥላሸት ፊታቸውን በመቀባት ማዋረድ ነው፤ አሉ፡፡ አብዱላ ኢብን ሰላማ "የአላህ መልእክተኛ ሆይ፤ ተውራቱን እንዲያመጡ ንገሯቸው" አለ፤ ተውራቱም መጣ፡፡ አንድ አይሁዳዊ በድንጋይ ተወግሮ እንዲገደል በሚያዘው የአምላክ ቃል ላይ በእጁ በመሸፈን ምን እንደሚል ከፊት ያለውንና ከኋላ የሚከተለውን ማንበብ ጀመረ፡፡ ያኔ ኢብን ሰላማ አይሁዳዊውን እጅህን አንሳ አለው፡፡ በድንጋይ በመወገር መቅጣት የሚያዘው የአላህ ቃል ከእጁ በታች እንደነበር አየ፡፡ የአላህ መልእክተኛም ሁለቱ ኀጢአተኞች በድንጋይ እንዲወገሩ አዘዙ፤ ተወገሩም፡፡ ኢብን ኡመርም በተጨማሪ ሁለቱ ሲወገሩ፣ እንኪሞቱ አይሁዳዊው አይሁዳዊቷን ሲሸፍናት አይቻለሁ አለ፡፡
ይህ ደግሞ ከላይ የተባሉትን ሁሉ ገደል የሚከትና ቁርአን መለኮታዊ ቃል አለመሆኑን እንዲሁም አንድም እውነት በውስጡ እንደሌለ ያሳየ ነው፡፡ ነቢዩ ሙሐመድ በአመንዝሮቹ ላይ የፈረዱት ተውራቱ ውስጥ በተገለጠው ትእዛዝ ሆኖ እያለ አይሻም ሆነች ኡመር ሌሎቹም የኢስላም ሊቃውንት ለነቢዩ በወረደ እንደሆነ ለማሳመን እንደሚጣጣሩ ያሳያል፡፡ ምን ይህ ብቻ፤ አላህም ለእርሳቸው ስለ መውገር አንድም አንቀጽ እንዳላወረደላቸው እያወቀ የነቢዩ ሐዲሳትም ያንን እያረጋገጡ ማኢዳ አንቀጽ 15 ላይ የሰፈረውን መልእክት ያወርዳል፡-
"የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! ከመጽሐፉ ትሸሽጉት ከነበራችሁት ነገር ብዙውን ለእናንተ የሚገልጽ ከብዙውም የሚተው ሲኾን መልክተኛችን (ሙሐመድ) በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ ከአላህ ዘንድ ብርሃንና ገላጭ መጽሐፍ በእርግጥ መጣላችሁ፡፡"
ይህ አንቀጽ የወረደበትን አስባብ የጻፉ ‘ትሸሽጉት’ የተባለው በድንጋይ ወግሮ ስለመግደል የሚያዘውን የተውራቱን መልእክት እንደሆነ ኢብን አባስ እንደሚከተለው ከትቦታል ኢብን ከሲርም ይህንን ሐሳብ በማብራሪያቸው መጥቀሳቸውን ይገልጻሉ፡-
Tafsir Ibn Abbas [5:15]
(O people of the Scripture! Now hath Our messenger) Muhammad (pbuh) (come unto you, expositing unto you much of that which ye used to hide in the Scripture) regarding the traits and description of the Prophet Muhammad (pbuh) and the legal ruling on stoning [married fornicators] as well as other things, (and forgiving much) and leave many other things, not mentioning them to you. (Now hath come unto you light) a messenger, i.e. Muhammad (from Allah and a plain Scripture) explaining the lawful and the unlawful,
በዚህ ሁሉ ግን አንድም መለኮታዊ መዓዛ አይሸትም፡፡
ማጠቃለያ፡-
ውድ ወሒድ አትጨነቅ እንዲሁ ነው የደከምከው፤ አመንዝራን በድንጋይ ወግሮ ስለመግደል የሚያዘው የአምላክ ትዕዛዝ ያለው ቶራው ውስጥ ነው፡፡ ይህ ሁሉ የሐዲስ እና የቁርአን አንቀጾች ጋጋታ እንደሚታወቀው ነቢዩ አንዲትን ሐሳብ ከሌላ ወገን ከኮረጁ በኋላ ለእርሳቸው እንደ ወረደና የነቢይነታቸው መገለጫ ለማድረግ የሚሔዱባት የተለመደች መንገድ ናት፡፡ ለዚህ የትየለሌ ማስረጃዎችን ማቅረብ እንደሚቻል ካንተ የተሰወረ አይደለም፤ ሽምጥጥ ታደርጋቸዋለህ እንጂ፡፡ ስለዚህ ስለ መውገር በፍየል የተበላ የቁርአን አንቀጽም ሆነ ሐዲስ የለም፤ ሁሉም ተረት ተረት ነው፡፡ ፍየሏም ብትሆን አንዲት ጦጣ ነበረች እንደሚባለው ዓይነት ናት፡፡ አንተም አፌን በዳቦ አብሱ ብለህ ዝጋው፡፡
አጭር ወንድማዊ ምክር ለወሒድ፡-
ወዳጀ የምትፈልገው ዝናና እውቅና ሰው ወረተኛ ስለሆነ ምናልባት ቢዘልቅ በሥጋ ባለህባቸው ወራት ብቻ ነው፡፡ ሁሉም ያልፋል፤ ከሥጋህ ስትለይ የምትጋፈጠው ግን ሌላ ነው፡፡ ከዚህ ተረት ተረት ጋር መቀጠል ውጤቱ ገሃነም ነው፡፡ ስለምታውቀው ላንተ ይህንን መንገር ተገቢ አይመስለኝም፡፡ ይሁንና ወንድማዊ ማሳሰቢያ ነውና ዛሬ ጊዜ እያለህ ወደ ምህረት ጌታ ብትመለስ ይሻልሃል፡፡ ንስሀ ብትገባና ብትመለስ ሊመልስህና ሊምርህ አያቅማማም፤ ታውቀዋለህ፡፡ የጠፋውን ልጅ ታሪክ አስታውስ!
ሰላም
ሳሂህ ኢማን ነኝ

የአዲስ ኪዳን ቀኖና አመጣጥ እውነታውና የሙስሊም ሰባኪያን ተረት (ክፍል 1)
<unknown>
በዩቲዩብ መከታተል ላልቻላችሁ በአነስተኛ መጠን የተዘጋጀ። Share!