ለምን አልሰለምኩም?
3K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
ኢስላም መለኮታዊ ሃይማኖት ነውን???

⚡️መፅሓፉ ሌሎች መጽሓፍቶቻችንን ተቀላቅሏል⚡️

➡️በቅርብ ቀን ጠብቁን
@Jesuscrucified
@Jesuscrucified
👍1
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Beltshazar)
መሐመድና ጥቁር ሴት
የዘረኛ ሰው የህልም ትርጓሜ

መሐመድ ለጥቁሮች ከፍተኛ ንቀት እንደነበረውና የዘረኝነት አንድምታ ያላቸውን ንግግሮች መናገሩን እንዲሁም አድሏዊ ተግባራትን መፈፀሙን ከዚህ ቀደም ተመልክተናል፡፡ በዚህ አጭር ጽሑፍ ይህንኑ የሚያጠናክር ተጨማሪ ማስረጃ እናስነብባችኋለን፡፡ ተከታዮቹ ዘገባዎች ሙስሊሞች ከቁርአን ቀጥሎ ከፍተኛ ቦታ በሚሰጡት ሳሂህ አል-ቡኻሪ በተሰኘው የሐዲስ ስብስብ ውስጥ የሚገኙ ናቸው (“ሳሂህ” ማለት የታመነ ወይም ትክክለኛ ማለት ነው)፡-

አብደላህ እንዳወራው ነቢዩ እንዲህ አሉ፣ “(በህልም) አንዲት ፀጉሯ ያልተበጠረ ጥቁር ሴት ከመዲና በመውጣት በመሐኢዓ ማለትም በአል-ጁፋ ስትቀመጥ አየሁ፡፡ የመዲና የበሽታ ወረርሽኝ ወደዚያ ቦታ (አል-ጁፋ) መዛመቱ ነው ብዬ ተረጎምኩት፡፡” (ሳሂህ አል-ቡኻሪ ቅፅ 9፣ መጽሐፍ 87፣ ቁጥር 161)

ነቢዩ በመዲና ሆነው ስላዩት ህልም አብዱላህ ቢን ዑመር እንዳወራው፤ ነቢዩ እንዲህ አሉ “(በህልም) አንዲት ፀጉሯ ያልተበጠረ ጥቁር ሴት ከመዲና በመውጣት በመሐኢዓ ስትቀመጥ አየሁ፡፡ የመዲና የበሽታ ወረርሽኝ ወደ መሐኢዓ ማለትም ወደ አል-ጁፋ የመዛመቱ ምልክት ነው ብዬ ተረጎምኩት፡፡” (ሳሂህ አል-ቡኻሪ ቅፅ 9፣ መጽሐፍ 87፣ ቁጥር 162)

ተመሳሳይ ዘገባ ሳሂህ አል-ቡኻሪ ቅፅ 9፣ መጽሐፍ 87፣ ቁጥር 163 ላይ ይገኛል፡፡

እንዲህ ያለ ንግግር በአንድ ተራ ሰው ቢነገር አቅልሎ ማለፍ ይቻላል፡፡ ነገር ግን ከፈጣሪ ዘንድ የተላከ እንደሆነ በተነገረለት “ነቢይ” መነገሩና በመንፈሳዊ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፎ መገኘቱ ጉዳዩን በቸልታ እንዳናልፈው ያስገድደናል፡፡ የዘረኝነት ምስል ከሳች የሆኑ መሰል ንግግሮች በቢሊዮኖች በሚቆጠሩ ሰዎች ሲደመጡና ለክፍለ ዘመናት ሲነገሩ የሚያሰርፁት ዘረኛ አመለካከት በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡ ይህንን ንግግር የሰማና አምኖ የተቀበለ ሰው ፀጉሯ የተንጨባረረ ምስኪን ጥቁር ሴት ሲመለከት የሚፈጠርበትን መጥፎ ስሜት ማሰብ አያዳግትም፡፡ ፈጣሪ ጥበበኛና ሁሉን አዋቂ በመሆኑ እንዲህ ያለ አደገኛ መዘዝ ያለውን ሕልም አያሳይም፡፡ የበሽታ ወረርሽኝ ከአንዱ ወደ ሌላ ቦታ መዛመቱን “ለነቢዩ” ማሳየት ቢፈልግ የሆነ ዓይነት አስፈሪ አውሬ ወይም ዕብድ ውሻ ሊያሳየው እየቻለ ሴትን የመሰለች የከበረች ፍጥረት “ጥቁርና ፀጉሯ የተንጨባረረ” የሚል ዘረኛ መግለጫ አክሎ ማሳየት ለምን አስፈለገ? በዚህ ህልምና በፍቺው ውስጥ የመሐመድ ዘረኛ አመለካከት እንጂ የፈጣሪ ጥበብና ዕውቀት አይታይም!
http://www.ewnetlehulu.org/am/black-woman/
መፅሓፉ ገበያ ላይ ነው

መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያ የመጽሐፍት መሸጫ ሱቆች ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ሱቆቹን የሚገኙባቸው ቦታዎች፡-
1. ቦሌ ጌቱ ኮመርሻል ሕንጻ 1ኛ ፎቅ
2. ፒያሳ ትንሹ አራዳ ሕንጻ 1ኛ ፎቅ
3. መገናኛ ቤተልሔም ፕላዛ 1ኛ ፎቅ
4. መርካቶ አውቶብስ ተራ ፊት ለፊት እና ከዛው አቤኔም ሕንጻ ምድር ላይ
5. 5 ኪሎ መካነኢየሱስ ሕንጻ 1ኛ ፎቅ
6. ደብረዘይት የመካነ ኢየሱስ የመጽሐፍት መሸጫ ሱቅ ውስጥ
7. አዳማ የመካነ ኢየሱስ የመጽሐፍት መሸጫ ሱቅ
"ኢስላም መሎኮታዊ ሃይማኖት ነውን?" ገፅ 44-45

"ሳሂህ ሙስሊም 8:3371

የአል-አዝል (#የወንዱን_ብልት_ከሴቷ_ብልት_ውስጥ_የዘር_ፈሳሹ_ሳይረጭ_በማውጣት_ውጭ_ላይ_የማፍሰስ) ምእራፍ

አቡ ሱርማ አቡ ሰኢድ አል-ኽድሪን እንዲህ አለው:- አቡ ሰኢድ ሆይ የአላህ መልእክተኛ ስለ አዝል(#የወንዱን_ብልት_ከሴቷ_ብልት_ውስጥ_የዘር_ፈሳሹን_ሳይረጭ_በማውጣት_ውጭ_ላይ_ስለማፍሰስ) ሲናገሩ አልሰማህምን? እርሱም ሰምቻለው: ጨምሮም ከአላህ መልዕክተኛ ጋር ወደ ቤኑ አል ሙስታሊቅ ዘመቻ ሔድንና የተወሰኑ እጅግ ቆንጆ የሆኑ የአረብ ሴቶችን ማረክን:: በሚስቶቻችን አለመኖር በጣም ተቸግረን ስለነበረ በእነርሱ ለመደሰት ፈለግን: በዛው ቅጽበት በገንዘብ የሚቤዣቸው ፈለግን (ለመሸጥ መሆኑ ነው):: ስለዚህም አዝል(#የወንዱን_ብልት_ከሴቷ_ብልት_ውስጥ_የዘር ፈሳሹን_ሳይረጭ_በማውጣት_ውጭ_ላይ_ማፍሰስ) በማድረግ በእነሱ ወሲባዊ ደስታን ለማግኘት ወሰንን:: ነገር ግን እንዲህ አልን:- የአላህ መልእክተኛ በመካከላችን እያሉ እንዲህ አይነት ተግባር እንፈጽማለን: ለምን እርሳቸውን አንጠይቅም? እኛም የአላህን መልእክተኛ ጠየቅናቸው:: እርሳቸውም እንዲህ አሉ:- ምንም አይደል: ካላደረጋችሁት አታድርጉት:: እስከ ትንሳኤ ድረስ የምትወለድ ማንኛውም ነፍስ ትወለዳለች"

ከመጽሓፉ የተቀነጨበ...


"Coitus Interruptus" ladies and gentlemen😎

@Jesuscrucified
@Jesuscrucified
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Beltshazar)
ክርስትና፣ እስልምናና ባርነት
የክርስትናው ዓለም በባርነት ውስጥ የተሳተፈበት ዘመን ነበር፡፡ ይህ በአትላንቲክ ላይ ሲደረግ በነበረው የባርያ ንግድ ሊገለፅ ይችላል፡፡ ይሁንና የክርስቲያኑ ዓለም ይህንን ወንጀል በማመን የባርያ ንግድን አስቀርቷል፡፡ የእስልምናው ዓለም ግን ሰፊ የባርነት ንግድ ታሪክ ያለው ሲሆን ንግዱ እንዳይወገድም ተቃውሞ አሰምቷል፡፡
ባርነት አብሶም የጥቁር ባርነት በእስልምና ዋና ተቋማት ተቀባይነት ያለውና በተማሩ ሙስሊሞችና የሕግ ሊቃውንት እንዲሁም መልካም በተባሉት አማኞች ዘንድ ዕውቅናና የተቸረው ነው፡፡ ግብፅ በአረቦች ከተወረረች በኋላ በ639 እና 642 ዓ.ም. ቢላድ አል-ሱዳን ወይም “የጥቁሮች ምድር” ለሙስሊሙ ዓለም የባርያ ምንጭ ሆኖ ነበር፡፡ የባርያ ፈንጋዮች ዋና ዋና ምንጮች ጦርነት (ጂሃድ)፣ ድንገተኛ ጥቃት፣ ገባርነት፣ ግዢ እና ጠለፋ ነበሩ፡፡ (John Alembillah Azumah, The Legacy of Arab-Islam in Africa, Oxford, England: One World, 2001, p. 141.)
የሰለመውን አፍሪካ አብዛኛውን ክፍል በተመለከተ ግን አውሮፓውያን ከመምጣታቸው ከብዙ ክፍለ ዘመናት በፊት የባርያ ንግድ የተቀናጀና ተቋማዊ ይዘት የነበረው ነው፡፡ (Azumah, p. 117)
የእስልምና ቅድስት ከተማ የሆነችው መካ “የዓለም የባርያ ንግድ ማዕከል” ሆና እስከ ሃያኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ያገለገለች ሲሆን ከምስራቅ አፍሪካና ከሱዳን የመጡ ባርያዎች ወደ መላው አረብያና የሙስሊም ዓለም ይሰራጩ ነበር፡፡ (Azumah, p. 146)
የእስልምናው ዓለም ድል የነሳቸውንና በግዛቱ ወሰን ላይ የሚገኙትን ብዙ ሕዝቦች ለ1000 ዓመታት ያሀል ባርያ አድርጓል፡፡ Hugh Kennedy, The Great Arab Conquests, U.S.A: Da Capo Press, 2007, pp. 222- 223, 323, 367; Bernard Lewis, pp. 11, 26, 85-89)
የባርያ ንግድ እንዲቀር ሲወሰን የተቃወመ ሲሆን መጨረሻ ላይ በምዕራባውያን ተፅዕኖ ምክንያት ለመተው ተገድዷ፤ ሆኖም ይህ ታሪክ እምብዛም አይታወቅም፡፡
ይህንን መጽሐፍ የምትፈልጉ ወገኖች christopherdgm@gmail.com ብላችሁ ለደራሲው መጻፍ ትችላላችሁ፡፡
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Beltshazar)
ይህችን ጽሑፍ ፕሪንት አድርጋችሁ ለሙስሊም ወዳጃችሁ አቀብሉት 👇👉👇 http://www.ewnetlehulu.org/am/what-is-the-bible/
ስለ ስቅለት እስላማዊ ብዥታዎች
ለያሕያ ኢብኑ ኑህ 42 የኩረጃ ጥያቄዎች የተሰጠ ምላሽ
ክፍል 1
👇👆
ሰላም ወንድሞችና እህቶች ባለፈው ለያሕያ መልስ እስከ ጥያቄ ቁጥር 20 ድረስ መላኬ ይታወሳል፡፡ ይኸኛው ፒ ዲ ኤፍ ከጥያቄ 21-42 የሚገኙትን ጨምሮ ሙሉ መጽሐፉን የያዘ ነው፡፡ አንብቡት፤ ለሌሎችም አስተላልፉ፡፡ 👇👆👇
የቁርአን ግጭቶች - ክፍል 1
<unknown>
(በወንድም ዳንኤል)
Audio
(በወንድም ዳንኤል - 11 የቁርአን ግጭቶች)
ለአብዱል_ጀሊል_አሊ_ካሳ_ናሙስን_እንደ_ዲያብሎስ_ነቢዩን.pdf
612.2 KB
ለ"የነፍሴ ጥያቄዎች" መፅሓፍ ተሰጠ የተባለውን pseudoመልስ ስንፈትሸው

ሳሂህ ኢማን

ክፍል 1

@Jesuscrucified
@Jesuscrucified