ለምን አልሰለምኩም?
3.01K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
ብዙ ሚስት በባይብል??

"፤ የጌታህንም ቤት ሰጠሁህ፥ የጌታህንም #ሚስቶች በብብትህ ጣልሁልህ፤ የእስራኤልንና የይሁዳን ቤት ሰጠሁህ፤ ይህም አንሶ ቢሆን ኖሮ ከዚህ የበለጠ እጨምርልህ ነበር።"
(መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ 12: 8)

አንዳንድ ንቀን የተውናቸው ሙሓመዳውያን ስናፍጭ በምታክለው ጭንቅላታቸው መፅሓፍ ቅዱስን ወደ እራሳቸው የወረደ ደረጃ ሲጎትቱና በየ ቻነሎቻቸው የወደቀ ትርጉም ሲፈላሰፉለት እያየን ነው። ከላይ ያነበብነውን የመፅሓፍ ቅዱስ ክፍል፣አንዱ እንዲህ ብሎ ትርጉም ሰጥቶታል። እስኪ የሱን ትርጉም ላስነብባቹ፤

"........አንዳንድ ክርስቲያን ወገኖች የዳዊትና የልጁ ሰለሞንን ከመጠን ያለፈ የሚስት ብዛት ለማስተባበል የሚጠቀሙት ቃል "እግዚአብሄር ሳያዛቸው በፍቃዳቸው የሰሩት ነው በዚህም ተወቅሰዋል" የሚል ነው። በመጀመሪያ ነገር በሚስት ማብዛታቸው ምክንያት ተቀጡ የሚል የለም። ሲቀጥል መጀመሪያውኑ እግዚአብሄር አይደል እንዴ በጅምላ እንዲያገቡ ያመቻቸው?...." ብሎ 2ሳሙኤል 12:8 ጠቅሷል።እስኪ ክፍሉን እናጥናው፤

1. #የጌታህንም_ሚስቶች your master's wives

ለዳዊት ጌታው(master) የነበረው #ሳኦል ነው። በመጀመሪያ ደረጃ፣ሳኦል ብዙ ሚስት አለው የሚል መፅሓፍ ቅዱስ ውስጥ የለም። ሳኦል #አንድ_ሚስት(1ሳም 14:49-50) እና "ሪጽፋን" የምትባል አንድ #ቁባት(concubine)(2ሳም 3:6-7)ብቻ ነበረው። "ሚስቶች" የተባለውም እሷን ጨምሮ ነው።በ ኢስራኤልም ሆነ በ ድሮ ምስራቃዉያን አለም፣ የ አንድ ንጉስ ሚስትም ሆነ ቁባት፣ ንጉሱ ከሞተ፣ የቀጣዩ ንጉስ ይሆናሉ። ንጉሱ ሊያገባትም ላያገባትም ይችላል። ብቻ እጣ ፈንታቸውን የሚወስነው ቀጣዩ ንጉስ ነው ማለት ነው።  የሚገርመው ነገር፣ መፅሓፍ ቅዱስን ከ ጫፍ እስከ ጫፍ ብታነብ፣ ዳዊት የሳኦልን ሚስት እንዳገባ የሚናገር #አንድም_ማስረጃ_የለም። ሌላው አስገራሚው ነገር ደግሞ፣ የሳኦልን ቁባት የወሰደው ዳዊት ሳይሆን #አበኔርም የሚባል ሰው ነው(2ሳም 3:7)። የቀረችው አንድ የሳኦል ሚስት ናት፤እሷንም ዳዊት እንዳገባት የሚናገር ጥቅሥም ማስረጃም የለም። ታዲያ ሙስሊሞች የሚሉት 'የትኞቹን የሳኦል ሚስቶች ናቸው ዳዊት ያገባው??'
ይልቁንስ ክፍሉ ላይ '... የጌታህንም #ሚስቶች በብብትህ ጣልሁልህ፤..' ለሚለው  ተቀባይነት ያለው ትርጉም "በራሱ በሳኦል ሚስቶች ላይ መብት ሰጠሁ፤" ይሄ ማለት የፈለገውን ማግባት ይችላል ነው እንጂ 'ሁሉንም ማግባት ይችላል'  ማለተም አይደለም። ለዳዊት ይሄ መብት ተሰቶታል ማለት ግን "አግብቷል" ማለት #አይደለም። ማስረጃም የለም። ስለዚህ በ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ 'እግዚያብሔር  ወንዶች ብዙ ሚስቶችን እንዲያገቡ ፈቅዷል' የሚል ሙግት ውድቅ ይሆናል ማለት ነው።

2. "..ከዚህ የበለጠ እጨምርልህ ነበር.."

ሙሓመዳውያን በዚህኛው ደግሞ እጅግ የሚያስቅ ሙግት ሰርቷል። ሙግታቸውም "..ለዳዊት አንሶት ቢሆን ኖሮ እግዚያብሔር ለዳዊት ብዙ ሚስቶችንም ይጨምርለት ነበር.." የሚል ነው። አንድ ፊደል የቆጠረ ሰው ይሄንን ክፍል መረዳት ያቅተዋል ብዬ አላስብም ነበር( apparently i was wrong 😂)።

በዚህ ክፍል ላይ፣እግዚያብሔር ለዳዊት የሰጠውን ነገር በዝርዝር እያስቀመጠ ነው ያለው፤ እንመልከት
1. የጌታህንም ቤት..
2. የጌታህንም ሚስቶች..
3.የእስራኤልንና የይሁዳን ቤት..
 ሰጠሁህ፤
..ይህም አንሶ ቢሆን ኖሮ ከዚህ የበለጠ እጨምርልህ ነበር።"
ስለዚህ፣ እግዚያብሔር "እጨምራለው" እያለ ያለው፣ ዝርዝሩን (e.g 4.ብር፣ 5.ወርቅ ወ ዘ ተ) እንጂ  #ሚስቶችን ወይም የተጠቀሱ ነገሮችን 'በብዛት' እጨምራለው' ማለት አይደለም።

ይልቁንስ፣ ቀጥለን በምናነበው ክፍል ላይ እግዚያብሔር በግልጽ #የትኛውም የእስራኤል ንጉስ ብዙ ሚስት እንዳያገባ ከልክሎ እናገኛለን። ስለዚህ ዳዊትም ሆነ ሶሎሞን ብዙ ሚስት ቢያገቡም እግዚያብሔር ፈቅዷል ማለት አይደለም።



(ኦሪት ዘዳግም ምዕራፍ 17)
----------
15፤ አምላክህ እግዚአብሔር የመረጠውን በላይህ ታነግሣለህ፤ ከወንድሞችህ መካከል የሆነውን በአንተ ላይ ንጉሥ ታነግሣለህ፤ ወንድምህ ያልሆነውን ከሌላ ወገን ሰው በላይህ ንጉሥ ታደርግ ዘንድ አይገባህም።

16፤ ነገር ግን ለእርሱ ፈረሶችን አያበዛም፤ እግዚአብሔር። በዚያ መንገድ ደግማችሁ አትመለሱም ብሎአችኋልና ፈረሶችን ለማብዛት ሕዝቡን ወደ ግብፅ አይመልስም።

17፤ ልቡም እንዳይስት #ሚስቶችን_ለእርሱ_አያበዛም፤ ወርቅና ብርም ለእርሱ እጅግ አያበዛም።

"17 Neither shall he multiply wives to himself, that his heart turn not away: neither shall he greatly multiply to himself silver and gold."

የኢስልምና አፖሎጂስቶችን ሎጂክ እናስተምር እንዴ?
@Jesuscrucified
@Jesuscrucified