ለምን አልሰለምኩም?
3.01K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
የዮሓኒስ ወንጌል 1:1፦ክፍል 1

በዘመናችን ያሉ እውቀት አልባ ሙስሊሞች ልክ ባዶ እቃ ሲመታ እንደሙዚቃ መሳሪያ እንደሚጮህ ሁሉ አንድ አንድ አስተማሪ ነን ባይ ኡስታዝ ተብዬዎች የተናገሩትን የወረደ "ማብራሪያ" ከጫፍ እስከጫፍ ተቀባብለው ሲያዜሙት እንታደማለን። በጣም የሚገርመው ነገር  ካልጠፋ ጥቅስ የዮሓኒስ ወንጌል 1:1ን ለራሳቸው እንደሚመች አድርገው ግሪኩን በ 1ኛ ክፍል የግሪክ ቋንቋ ያውም በጆሮ ጠገብ እንጂ በ እውቀት ባልሆነ ትርጉማቸው ሲተረጓግሙት ሰምተናል። "Little knowledge is dangerous" የተባለውም ለዚህ መሆኑ ግልጽ በሆነ መንገድ ተረድተናል።

ክፍሉን እስኪ አንድ በ አንድ እንመልከት

ዮሓኒስ 1:1-2
Ἐν ἀρχῇ ἦν ὁ Λόγος, καὶ ὁ Λόγος ἦν πρὸς τὸν Θεόν, καὶ Θεὸς ἦν ὁ Λόγος.
Οὗτος ἦν ἐν ἀρχῇ πρὸς τὸν Θεόν.

(የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 1)
----------
1፤ በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።

2፤ ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ።

#Ἐν_ἀρχῇ_(En_arche)_'በመጀመሪያ'

ዮሓኒስ ይህንን ክፍል ሲጽፍ የተጠቀመባቸውን ቃላት በጥንቃቄ እየመረጠ ነው።  በዚህ ክፍል፣ #Ἐν "En-' የምትለው ቃል መጀመሪያን ለመግለፅ እንደሆነ ይታወቃል። መጠየቅ ያለብን ጥያቄ፣ " መጀመሪያ ማለት ምን ማለት ነው?" ወይም "የትኛው መጀመሪያ" የሚል ሲሆን፣ ለዚህ መልስ የሚሰጠን ከላይ ያነበብነው Ἐν_ἀρχῇ የሚለው ቃል ነው። ይሄን ቃል የምንጠቀመው፣ "መጀመሪያ_የሌለው_'መጀመሪያ'" "timeless_beginning' ለመግለፅ ነው። ይሄ ማለት፣ አንድ ሰው መጀመሪያ ብሎ የሚያስበውን "ጊዜ" እንደፈለግ በ ቢሊየን በሚቆጠሩ ዘመናትን ወደ ኋላ ገፍቶ "ይሄ መጀመሪያ" ነው ብሎ ቢያስብ፣ ያኔ እየሱስ (ሎጎስ)  #ነበር ማለት ነው። ሌላም ሰው መጀመሪያ የሚለውን ጊዜ ወደ ኋላ ጨምሮ ቢገፋው ያኔም እየሱስ ነበር ማለት ነው። በ አጭር ቃል " ዘላለማዊ" ማለት ነው። ዮሓኒስ ይህንን ቃል የተጠቀመውም እኛ ሰዎች በ ጊዜ እና ስፔስ (Time and Space) ተገድበን ስላለን ነው። ግን በዚህ አላበቃም። በዚህ "መጀመሪያ" ተብሎ በተጠቀሰው ጊዜ በተመሳሳይ ጊዜ ቃሉ"ሎጎስ" #ከእግዘብሔር_ጋር_ነበር ይላል። ይሄ ማለት አንድ ሰው 'መጀመሪያ ብሎ የሚያስበውን ጊዜ (specific time) የፈለገ ያህል ወደ ኋላ ቢገፋው already በዛ ጊዜ እየሱስ (ቃሉ ወይም #ሎጎስ) ከ እግዚያብሔር(አብ) ጋር በሕብረት ነበር ማለት ነው( Logos eternally co-existed with the Father)። በ አጭር ቋንቋ ይሄ #ሎጎስ  ከዘላለም ጀምሮ ነበር ማለት ነው።

ልብ በሉ፣ ዮሓኒስ ሲፅፍ፣ "በ መጀመሪያ ቃል ተገኘ" ወይም ሎጎስ የ እግዚያብሔር አብ #የይሁን_ቃል ነው #አላለም። 'ይህ ሎጎስ፣ የሆነ ጊዜ ላይ ተገኘ' ማለት ቢፈልግ ኖሮ " en arche" የሚለውን ቃል ሳይሆን "egeneto" የሚል ቃል በተጠቀመ ነበር።  አሁን ግን አልተጠቀመም።

ታላቁ የ ግሪክ ቋንቋ ምሁር  አርኪባልድ ቶማስ ሮበርትሰን፣ 'Word Pictures in the New Testament, vol 5' በተሰኘው መፅሓፋቸው ውስጥ ሲጽፉ እንዲህ ብሏል፤ " ዮሓኒስ በዚህች አረፍተ ነገር ውስጥ 3 ጊዜ 'En' የምትለውን ቃል ተጠቅሟል። ይሄም የሚያሳየው "እግዚያብሔርም(እግዚያብሔር አብም)"  "ሎጎስም(ወልድም)" መጀመሪያ እንደሌላቸው ወይም ደግሞ ዘላለማዊነታቸውን "Continous Existence" የሚያሳይ ነው።"

'Ev' "En" የሚለው ቃል የ "εἰμί" (Eimi) imperfect ቃል ሲሆን ዘላለማዊነትን (timeless existence) የሚያሳይ ነው። ይህንን ቃል እየሱስ በ ዮሓኒስ 8:58 ላይ ተጠቅሞ እናገኛለን።
εἶπεν αὐτοῖς Ἰησοῦς Ἀμὴν ἀμὴν λέγω ὑμῖν, πρὶν Ἀβραὰμ γενέσθαι #ἐγὼ_εἰμί.
" ኢየሱስም። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብርሃም ሳይወለድ #እኔ_አለሁ አላቸው።"
(የዮሐንስ ወንጌል 8:58)
ይሄም የሚያሳየው እየሲስ ዘላለማዊ መሆኑንን እንደሆነ ትላልቅ የ ግሪክ ምሁራን (ሮበርትሰንን ጨምሮ) አረጋግጧል።


#ታዲያ_ሎጎስ_Λόγος_ምንድነው?

Λόγος ሎጎስ ወይም "ቃል" እኛ በ 21ኛው ም.አ ውስጥ ሆነን እንደምናስበው ዝም ብሎ የንግግር ቃል አይደለም። LOGOS ገና ዮሓኒስ ወንጌሉን ሳይፅፍ በቢዙ ግሪክ ፊሎሶፊና እምነቶች ውስጥ ጥቅም ላይ ነበር። ትርጉሙም ሰፊ ነው።

1. ሔራቅሊጦስ (Heraclitus) 535 B.C-475 B.C ከ ሶቅራጦስ በፊት የነበረ በ ኤፌሶንም ይኖር የነበረ የግሪክ ፊሎሶፈር ነው። እሱም ሎጎስ 'Logos'  የሚለውን ቃል "The principle which controls the Universe"(ጠፈሮችን የሚቆጣጠር ፕሪንሲፕል" ብሎ ያስተምር ነበር።

2. #እስቶይክስ የሚባሉ የፊሎሶፊ ግንዶች ደግሞ #ሎጎስን "Anima Mundi" ብለው ይጠቀሙ ነበር። ይህ ማለት "የአለማችን ሕይወት ወይም የ ሕይወት ምንጭ" (Soul of the World) ማለት ነው።

3. ማርቆስ አውራሊየስ (Marcus Aurelius) ከ121 A.D-180 A.D ይኖር የነበረ የሮም ገዢ እንዲውም ፊሎሶፈር ነበር። Spermatikos Logos የሚል ፕሪንሲፕል ይጠቀም ነበር። ይህም "ሎጎስ" የ አለማችንን የመፍጠርና የመራባትን ሕግ የሚቆጣጠር (Generative principle of the Universe)፣ በ ሌላ ቋንቋ ወይም ፍልስፍና ባልሆነ ቋንቋ ሲታይ "አምላክን" የሚወክል ማለት ነው።

4. በ ኢብራይስጥ ቋንቋ "Memra" "ሜምራ" ማለት ሲሆን ኢብራውያን ለ "አምላክ" ተጠቅመውበታል። ለምሳሌ በ ታርጉማቸው ውስጥ ስለ ኦሪት ዘዳግም 26:17-18 ሲፅፉ " Ye have appointed The MEMRA (logos) a king over you this day, that #he may be YOUR #GOD" (ሎጎስን በራስህ ላይ ንጉስ አድርገህ ሹመኃል፤ ይህም #አምላክ እንዲሆንህ ነው።)

#ታድያ_ሎጎስ_የሚለውን_ቃል_ለምን_መረጠ?

ዮሓኒስ ይህንን ወንጌል ሲፅፍ "GNOSTICS" ኖስቲክስ የሚባሉ ግሩፖች  እንዲዩም "Dicipline of Valentinus' (ዲሲፕሊን ኦፍ ቫሌንቲነስ) የተሰኘ አስተምህሮ ተነስቶ ነበር። እነኚህ ማህበረሰብ "ሎጎስ የሚባል አካል "Aeions" ከሚባሉ የመጀመሪያ ፍጡሮች አንዱ ሲሆን "ዞዪ"(Zoe) ከምትባል ሌላ "ኤዎን" ጋር በመሆን ሌሎች ፍጡሮችን ማስገኘት እንደጀመረ ይናገራሉ። እንኚህ ግሩፖች የመፅሓፍ ቅዱስን አስተምህሮ በማዛባትና ከነሱ በፊት የነበረውን የሎጎስ ትርጉሞች ተጠቅመው የራሳቸውን ሓሰተኛ ወንጌል መስበክ በጀመሩ ጊዜ ነው ዮሓኒስ መፃፍ የጀመረው። ታዲያ ዮሓኒስ "የሎጎስን" ፍልስፍና በሚያውቅ ሕብረተሰብ ውስጥ ነው ይህንን ስያሜ ለእየሱስ የተጠቀመው። ይህን ቃል ሲጠቀም ግን የነሱ ትርጉም ትክክል ነው ብሎ እንደወረደ አልተጠቀመም። ይልቁንስ ሎጎስ የተፈጠረ አምላክ ሳይሆን እራሱ ዘላለማዊና ፈጣሪ መሆኑን ለማሳየት En Arche ብሎ ጀመረው። ከዛም "ቃሉም በመጀመሪያ ከ እግዚያብሔር ጋር ነበር" በማለት "ተፈጠረ" የሚለውን ቃል አፈረሰ፣ውድቅ አርገ እንጂ።
#ይቀጥላል...
Ref.
1.Barnes note on John 1:1
2.Iraneus Against Heresies Bk 1,Ch 1
@Jesuscrucified