ለምን አልሰለምኩም?
3K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
በቁርዐኑ ምዕራፍ 17:79 ላይ
وَمِنَ ٱلَّيْلِ فَتَهَجَّدْ بِهِۦ نَافِلَةًۭ لَّكَ عَسَىٰٓ أَن يَبْعَثَكَ رَبُّكَ مَقَامًۭا مَّحْمُودًۭا
"ከሌሊትም ላንተ ተጨማሪ የኾነችን ሶላት በእርሱ (በቁርኣን) ስገድ፡፡ ጌታህ #ምስጉን_በኾነ_ስፍራ በእርግጥ ያቆምሃል፡፡" 17:79

👉በዚህ አንቀፅ ላይ አላህ ሙሐመድን ምስጉን በኾነ ስፍራ እንደሚያስቀምጠው ይናገራል። ይህ ምስጉን የሆነ ስፍራም ብዙ ሙፈሲሮች በመጨረሻ ቀን አላህ #የማማለድን_የላቀን ቦታ ይሰጠዋል ማለት እንደሆነ ይናገራሉ። ይህ ከሁሉም የላቀ የማማለድ ስፍራን እንዴት አድርጎ አላህ እንደሚያጎናፅፈው ግን የሚነግረን አል ታባሪ በታሪኩ በቅፅ 1 ገፅ 149-151 ላይ ባሰፈረው ከፊል የ17:79 ተፍሲ ር ትርጉም በተሰኘው ክፍል ላይ ነው።(The history of Al-Tabari- General introduction and from creation to flood, translated by Franz Rosenthal[state university of New York press(SUNY), Albany 1989]
✍️ በዘገባው ላይ የ #maqaman_mahmudan ትክክለኛ ትርጓሜ #አላህ_ሙሐመድን_በዙፍኑ_ላይ(በራሱ ዙፋን ላይ) ያስቀምጠዋል የሚል ነው። ይህን ትርጓሜ ለክርክር እንኳ የማይቀርብ ትክክል የሆነ መሆኑን እራሱ ያስረግጥልናል። ስለዚ በለተ ትንሳኤ ሙሐመድ #ማማለዱን የሚተገብረው አላህ ዙፋን ላይ ተቀምጦ 😮 እንደሆነ ምንም አያጠያይቅም። ጥያቄው ሙሐመድ አብሮ ከአላህ ጋር ይቀመጣል ወይስ አይቀመጥም የሚል ይሆናል። ይህንን ነው አል ታብሪ አከራካሪ እንደሆነና እንዲህ ነው እንዲያ የሚሉ #ሶስት አመለካከቶችም አሉበት የሚለው። እኛ ወደዚህ ሐተታ እንኳ ሳንገባ በቀላሉ(በራሱ ብዙ ጥያቄዎችን ያስነሳል) ምን ማለት እንደሆነ ብናይ ይበቃናል።