ለምን አልሰለምኩም?
3.01K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
"ሁለቱ ማንነቶች"
ክፍል ፭
👉 በእስካሁኑ ጉዞችን ሙሐመድ እንዴት አምልኩኝ እንዳለ አላህም እንዴት ራሱን ከመሐመድ ጋር ተጋሪ አድርጎ በመፅሐፉ እንዳቀረበ ቃኝተናል። በዛሬው ክፍል ፭ ቅኝታችንም ሙሐመድ እንዴት ከአምልኩኝ ጥያቄ ባለፈ መልኩ በእስልምና መዛግብት እንደተሳለ #እንደተመለከም እናያለን።
👉በሱረቱል አል ፈትህ(48) ቁጥር ዘጠኝ ላይ አንድ ለሙስሊም ወገኖች ሁሉ አስደንጋጭና በዘመናት ለማስተካከል ቢሞክሩም ያልተሳካላቸውን አያ እንመለከታለን። ይህንን #ከሻኪር ቁርአን ላይ በእንግሊዝ አፍ ያለውን ለማሳያ ተጠቅሜአለሁ፦
Surah Al-Fath, Verse 9:
لِّتُؤْمِنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ وَتُعَزِّرُوهُ وَتُوَقِّرُوهُ وَتُسَبِّحُوهُ بُكْرَةً وَأَصِيلًا

That you may believe in Allah and His Apostle and may aid him and revere him; and (that) you may declare His glory, morning and evening.
(English - Shakir)
እንግዲህ በዝህች አንድ ጥቅስ ውስጥ አላህ እንዲህ ይላል "በአላህና በመልእክተኛው እመኑ እርዱትም፤ ፍሩትም ክብሩንም ሌት ተቀን አውጁ!" ይህ ትርጉም ነው እንግዲ አጨቃጫቂው።
ይህን ሙግት የሚያነብ ሰው ሁሉ ልብ ይለው ዘንድ እሚገባው አረብኛ አለማወቅ ወይም ማወቅ ለዚህ አያ ቀጥተኛ ትርጉም ምንነት ግድ አለመሆኑን ነው። ለምን ቢባል ከላይ የሰጠሁት ትርጉም የኔ ፈጠራ አለመሆኑን ስተነትን ግልጥ ይሆናል። እንግዲ እንደተለመደው አላህንና መልእክተኛውን #እመኑ በሚል ትእዛዝ ይጀምርና #እርዱትም(Tu'azziruh በአረብኛው)፣ #ፍሩትም(Tuwaqqiruh) እና ክብሩን ሁሌም #አውጁ (አምልኩትም, Tusabbihuh) ይላል። የሻኪር ቁርአን ይህንን ነው ቃል በቃል አለምንም ጭማሬ ቁጭ ያደረገው። ሌሎቹ ግን (አማረኛውንም ጨምሮ) #የሌለውን በመጨረሻው ትእዛዝ ላይ "አላህን" የሚል ይጨምሩበታል።
ጥያቄ 🤔ለምንድነው ሻኪር ቀጥታ የተረጎመው? ለምንድነውስ ሌሎቹ ይህንን የጨመሩበት?(ሲያስቡት ስለማያዋጣ ነው ወይስ እውን ስላለ?)
🤔የመጀመሪያው ትእዛዝ ሙሐመድን ያማከለ ከሆነ አለምንም ማስረጃ ሦስተኛው እርሱን አይደለም ማለት ምን ማለት ነው?
ለማንቻውም ይህ አያ ላይ ያሉ ሦስቱም ትእዛዛት ለሙሐመድ እንደሚውሉና እንደዋሉ ለማሳየት 📚የኢብን #አባስን ተፍሲር ማየት በቂ ነው። ኢብን አባስ በተፍሲራቸው ፍሩትንና ክብርን ስጡትን በቀጥታ ከእርዱት ቀጥሎ በማስገባት ቀጥሎም ወደ አላህ ቀንና ለሊት ፀልዮ በሚል ፍቺ ያሳርጉታል።
በእውነቱ ሦስቱም ለአንድ ማንነት መጠቀም እማይመስል ሆኖ የታያቸው ሰዎች ይህንን ለማስታረቅ ነው የመጀመሪያ ሁለቱን ለሙሐመድ ከሰጡ በኋላ ክብር ስጡ እሚለው ጋር ሲደርሱ ለአላህ ያሉት። ሦስቱም ለአላህ እንዳይሆን ደሞ መቼም አላህ በሰይፍ እሚጠብቀው እና እሚረዳው አያስፈልግም። ስለዚ ያው በቅድሙ መንገድ መሄድን መረጡ። ግን በምን ማስረጃ እና ከምን ተነስተው ይህንን አፀደቁ?
💡 እውነታው ግን ኢብኑ አባስ እንደፈሰሩት ሻኪርም እንደ ተረጎመው ሶስቱም ትዕዛዛት ያማከሉት ሙሐመድን ነው።ለዚነው ከሰዋስዋዊ ሙግት በዘለለ ለሙሐመድ ክብር መስጠት #ቁርአናዊ ነው የምንለው። አያችሁ እንዴት አላህ እንኳ ሙሐመድ ክብር እንደሚገባው ሲመሰክር?
ይቀጥላል......
.................//................
" እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው።"
(የዮሐንስ ወንጌል 8:32)
🙏አርነት በእውነት ይሆንላችሁ ዘንድ ፀሎቴ ነው!🙏🙏🙏