ለምን አልሰለምኩም?
3.01K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
📌አምላክ እንዴት አምላክ ይኖረዋል?📌

ሙሓመዳውያን ስለ እየሱስ አምላክነት ሲጠይቁን ውሃ ከማይቋጥሩ ሙግታቸው መካከል አንዱ "እየሱስ እራሱ እግዚያብሔር አብን አምላኬ ብሏል፤ታድያ እናንተ እየሱስን አምላክ የምትሉት ከዬት አምጥታችሁት ነው?? አምላክስ አምላክ ሊኖረው ይችላልን??" የሚል ነው።

በመጀመሪያ ደረጃ እኛ እግዚያብሔር አብ የ እየሱስ አምላክ ("የሰውነት ማንነቱ") መሆኑን ጠንቅቀን እናውቃለን።  እየሱስም ወደ ምድር ሲመጣ በ አምላክነት ማንነቱ የ ሰውነት ማንነተ ስለተዋሃደ  ጠቅልለን "የ እየሱስ ክርስቶስ አባትና አምላክ" እንላለን።

ሙግት አንድ

እየሱስ መጽሓፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚያብሔር አብን "አምላኬ" ብሎ ጠርቶታል (ማቴዎስ 27:46)፤ ጳውሎስም "የእየሱስ ክርስቶስ አባትና አምላክ" ብሏል።
" በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ።" (ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1:3)። እየሱስ ካረገ በኋላም "አምላኬ" ብሏል። (ራእይ 3:2)


ታድያ እየሱስ አማላክ ከሆነ እንዴት አምላክ ይኖረዋል??

" እነሆ፥ እኔ የሥጋ ለባሽ ሁሉ አምላክ  "יְהוָ֔ה" እግዚአብሔር "אֱלֹהֵ֖י" ነኝ"(ትንቢተ ኤርምያስ 32:27)
"27 Behold, I [am] the LORD ""  , the God of all flesh: is there any thing too hard for me?"
(Jeremiah 32:27)

በዚህ በክፍል ላይ እግዚአብሔር ያህዌ #የስጋ #ለባሽ ሁሉ አምላክ እንደሆነ ግልፅ ነው። እየሱስ ደግሞ ወደ ምድር ሲመጣ ስጋን ለብሷል። ልበ በል "ማንነቱን (essence) ቀየረ" ሳይሆን፤ ሌላ ማንነትን (ሰውነትን) ጨመረ ማለት ነው። ስለዚህ እየሱስ ሁለት ማንነት በ አንድ አካል (one person) ሆኖ ተገልጧል ማለት ነው። ስለዚህ እየሱስን በ አረፍተ ነገር ውስጥ ስናመለክት ሁለቱ ማንነቶች የተለያዩ ቢሆኑም ለይተን አንጠራም ማለት ነው። ስለዚህ እየሱስ የሰውነት ማንነት(human nature) ስላለው፣ በ ኤርሚያስ 32:27 መሰረት፣ ስጋ ያልለበሰውን እግዚያብሔር አብን "አምላኬ" ብሎ መጥራት ነበረበት። ስለዚህ እየሱስ እግዚያብሔር አብን አምላኬ ስላለ እየሱስ አምላክ አይደለም ማለት አይደለም። ምክኒያቱም በአምላክነት ማነቱ ለዘለአለም ከ አብ ገር " አንድ ማንነት (one being)" ኖሮት ይኖር ስለነበረ። 

" #አሁንም፥ አባት ሆይ፥ #ዓለም #ሳይፈጠር በአንተ ዘንድ #በነበረኝ #ክብር አንተ በራስህ ዘንድ አክብረኝ።"(የዮሐንስ ወንጌል 17:5)፤  

(የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 1)
----------
1፤ በመጀመሪያው ቃል ነበረ( En arche(ልብ በል "ኤጌኔቶ" አይልም) en o logos)፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።

2፤ ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ።

(የዚህን ክፍል ጥልቅ ማብራሪያ በ ግሪክ ሰዋስውና ፊሎሶፊ በቅርብ ቀን እናያለን።)

ስለዚህ እየሱስ እግዚያብሔር አብን "አምላኬ" ብሎ እንዲጠራው ያደረገው የሰውነት ባህሪይ ነው እንጂ ፍጡር ስለሆነ #አይደለም

ሙግት ሁለት፦ ካረገ በኋላስ??

እየሱስ ካረገ በኋላም በሁለቱ ማንነቶቹ ይኖራል። ሲጀመር የትንሳኤ ሃሳብ እራሱ የስጋ ማንነትን "pre suppose"  ያደረገ ነው።(ሉቃስ 24:39)
ለዚያም ነው ጳውሎስ ሲናገር "አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤"(1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:5) ብሎ የሰውነት ማንነቱን ብቻ የ ገለፀው። የ እየሱስ ክርስቶስ መካከለኛነት በ ስጋዊ ባህሪው (በመሞት) የተፈፀመ ስለሆን "ሰው የሆነው" ብሎም ተናግሯል። ልብ በሉ "ሰው ብቻ" አላለም። ከሁለቱ ማንነቱ አንዱን በ አውዱ (መካከለኛ መሆን) መርጦ ተናግሯል። ጳውሎስም በ ኤፌሶን 1፡3 "የ እየሱስ አባትና አምላክ" ያለው አሁንም እየሱስ በ ሁለት ማንነቱ ስላለ ነው።

ሙግት ሶስት፦ አንተ ብቻ እውነተኛ አምላክ

" እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።"(የዮሐንስ ወንጌል 17:3)
"3 And this is life eternal, that they might know thee the only true God, and Jesus Christ, whom thou hast sent."(John 17:3)

እግዚያብሔር አብ ብቻ እውነተኛ አምላክ ከተባለ እየሱስ እንዴት እምላክ ይሆናል??

መልሱ " ስላሴ ውስጥ ነው። ሎጂኩን ላሳያቹ

1. ስላሴ ብቻ እውነተኛ አምላክ ነው
2 ስላሴ በ አንድ አምለክ ማንነት ( in only one being=God) ሶስት አካል (person) ለዘለአለም በአምላክነት ባህሪያቸው እኩልና አንድ የሆኑ አብ፣ወልድና መንፈስ ቅዱስ አሉ። ስለዚህ እያንዳንዱ የስላሴ አካል በ ነጠላም ብቸኛ እውነተኛ አምላክ ነው

መደምደሚያ። አብ ብቸኛ እውነተኛ አምላክ ነው፤ ወልድ ብቸኛ እውነተኛ አምላክ ነው፣ መንፈስ ቅዱስ ብቸኛ እውነተኛ አምላክ ነው። ልብ በል፤ "እውነተኘ አምላክ" አንድ "essence" ነው፤ "አካል" (person) አይደለም። ሶስቱ ደግሞ "አካል ናቸው"።

ስለዚህ በ ስላሴ አውድ "አብ ብቸኛ እውነተኛ አምላክ ነው" ማለት ወልድ #አይደለም ማለት አይደለም።

ይቀጥላል...
@Jesuscrucified
@Jesuscrucified
1👍1