ለምን አልሰለምኩም?
3K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
3. ከ ሳምንታት እስከ አመታት በኋላ የሚመጡ ችግሮች። Long term Effect
የረጅም ጊዜ ውጤቶቹ ብዙ ቢሆኑም አሁን የምናየው አንዱን ብቻ ነው።
በ ኦርጋኖፎስፌት የሆነ ጊዜ ላይ  ተመርዞው ግን በ ሕይዎት የቆዩ ሰዎች ከ #ሶስት እስከ #አምስት አመት ጊዜ በሚሆኑ ጊዜ ውስጥ "ኮሮነሪ አርቴሪያል ዲዚዝ"(Coronary artery disease) ማለትም "የ ልብ ደም ስሮች በሽታ"  በ ተሰኙ በሽታዎች የመያዝ እደሉ እጅጉን ከፍ ያለ እንደሆነ የማያከራክር የ ጥናት ውጤት ነው። ይሄም "Long term effect of organophosphate poisoning" ይባላል።

ማስረጃ፦ Dong-Zong Hung, Hao-Jan Yang,  and Sally C. W. Tai; The long term effect of organophosphate poisoning as a risk factor of CVD;(ሙሉ ሶይቴሽን ግርጌ ይመልከቱ

ከነኚህ በሽታዎች ዋናው " ማዮካርዲያል ኢንፍራክሽን" (mayocardial infraction) ይባላል። ምልክቶቹም ቀጥሎ ያሉት ይሆናል።
1.በ ልባችን ላይ ከፍተኛ የሆነ ሕመም። ሕመምተኞቹ ሲገልፁት ልክ በ ቢላ ልቡ ላይ እንደተወጋ ሰው ወይም ልቡ ተጨምድዶ እንደተያዘ ሰው ይሰማቸዋል
2. አንዳንዴ ሕመሙ ወደ ትክሻ ወደ እጅም ይሔዳል..ወዘተ

ነብዩ ሙሓመድ ይህንን የሚመስል ምልክት አሳይቷልን?? ቅድም ካነበብነው ሓዲዝ እንዲህ ብሏል፦
"..ኦ አይሻ! እስከዛሬ ቀን ድረስ በ ኽይበር ከበላሁት ምግብ የሚሰማኝ የሕመም ስሜት አለኝ፤ ከበላሁትም መርዝ አሁን ትልቁ #የልብ #የደም #ቱቦዬ (AORTA) #እየተቆረጠ እንዳለ አይነት ስሜት ይሰማኛል!!"

ልብ በሉ፣ ነብዩ ልባቸው ላይ የተሰማቸውን ሕመም ልክ ከተመረዘ ከ አመታት በኋላ በ ኮሮነሪ አርቴሪያል ድዚዝ እንደተጠቃ ሰው አገላለፅ ገልጿል።

መደምደሚያ

1. የ ቢሽር አሟሟት የ ኦርጋኖፎስፌት የ ቅጽበት ምልክቶችን ይገልፃል
2. የ ነብዩ አሟሟት የ ኦርጋኖፎስፌት የረጅም ጊዜ ውጤት ምልክቶችን ይገልፃል
3. ስለዚህ ነብዩ (most likely) ከ ኦርጋኖፎስፌት ሞቷል

ስለዚህ "እንዴት ሰው ተመርዞ ከዛው መርዝ ከ 3 አመታት በኋላ ሊሞት ይችላል??" ለምትሉ ሙስሊም ምስኪኖች በቂ መልስ ነው። አከተመ!!!

ዋቢ መጻሕፍት፤

1.Stapczynski, J. S., & Tintinalli, J. E. (2016). Tintinalli's emergency medicine: A comprehensive study guide (8th ed.). New York, N.Y.: McGraw-Hill Education LLC. PP 1318-1326

2. UpToDate 21.2

3. Hung D-Z, Yang H-J, Li Y-F, Lin C-L, Chang S-Y, Sung F-C, et al. (2015) The Long-Term Effects of Organophosphates Poisoning as a Risk Factor of CVDs: A Nationwide Population-Based Cohort Study. PLoS ONE 10(9): e0137632. doi:10.1371/journal. pone.0137632

@Jesuscrucified
@Jesuscrucified