ለምን አልሰለምኩም?
3.01K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
📌ከ እስልምና በፊት ከነበሩት እምነቶች ይተኮረጁ📌
👹የ ሙሓመድ ሸይጠኖች 2 👹

ከ መቀጠላችን በፊት ጂኒዎች የ ሰይጣን(ዲያብሎስ/ኢብሊስ) ጎሳ መሆናቸውን የሚገልጽ ሱራ እናንብብ
ሱረቱል ካፍ (18):50
"ለመላእክትም ለአደም ስገዱ፥ ባልናቸው ጊዜ (የሆነውን አስታውስ)። ወዲያውም ሰገዱ፤ ኢብሊስ ብቻ ሲቀር፤ ከጋኔን/ጂን (ጎሳ) ነበር፤ ከጌታውም ትእዛዝ ወጣ፤ እርሱንና ዘሮቹን እነሱ ለናንተ ጠላቶች ሲኾኑ፥ ከኔ ሌላ ረዳቶች አድርጋችሁ ትይዛላችሁን? ለበዳዮች ልዋጭነቱ ከፋ!" ....ስለዚህ ክፉ መናፍስት እንጅ ቁሳዊ እንዳልሆኑ ግልጽ ነው።

ክፍል አንድ ላይ ነ.ሙሓመድ ሰይጣኖች እንደሚበሉ አስተምረውናል። እንግዲህ ማንም ሰው ይህንን ትምህርት ከተማረ በኊላ የሚጠይቀው ጥያቄ ቢኖር "ጂኒዎቹ ምንድነው የሚበሉት??" የሚል ጥያቄ ይሆናል ብዬ አስባለው። እስኪ እሳቸው (ሙሓመድ) ምን ይላሉ??

Bukhari - Volume 5, Book 58, Number 200:
Narrated Abu Huraira:
 አንድ ወቅት ላይ አቡ ሁረይራ ለ ነብዩ ሙሓመድ  ሓፍረተ ስጋቸውን የሚታጠቡበት ውሃ (ከተጽዳዱ በኊላ የሚደረግ)  ይሸከምላቸው ነበር። አንድ ቀን እየተከተላቸው እያለ ነብዩ "ማን ነው" ብለው ይጠይቃሉ። እሱም "አቡ ሁረይራ ነኝ" ብሎ ይመልስላቸዋል። ሙሓመድም "ሒድና ብልቴን የማፀዳበትን #ድንጋይ አምጣልኝ። የ እንስሳን #ኩበት ወይም #አጥንት ግን እንዳታመጣ" አሉት። አቡ ሁረይራም ዘገባውን ቀጥሎ እንዲህ አለ " እኔም በ ጎን ኪሴ ድንጋይ አመጣሁለት።....ሲጨርሱም "ኩበትና አጥንት ለምን ተከለከለ??" ብዬ ጠየኩ። ነብዩም "እነኛ ሁለቱም የ #ጂኒዎች #ምግብ ናቸው፣ ብለው መለሱ።..." 

 ጃሚ አት ቲርሚዚ 3258

"...(በ ኩበት ወይም በ አጥንት)ብልቶቻቹን አታፅዱ።እነሱ ለ ጂን ወንድሞቻቹ ምግብ ናቸው።"

ጥያቄዎቻችን
1. ሙስሊሞች እነኚን የ ጂኒዎችን ምግብ እንዳይጠቀሙ ከታዘዙ ጂኒዎችን እየመገቡ ምሆኑ አይሆንምን?? ክፉ መናፍስት ልክ እንደሰው የሚመገቡ ከሆነ የሰው ጠላት (ሱራ 35:6) እስከሆኑ ድረስ የነሱን ምግብ እየተጽዳዳንበት በ ረሃብ ብንጨርሳቸው አይሻልምን??

ሙስሊሞች እንግዲህ እነኚን ጥቅሶች ስንስጣቸው.. "አይ! ሰይጣን እንደሰው ይበላል ማለት አይደለም..." እያሉ ለመግለፅ ይፍጨረጨራሉ። ችግሩ፣ አንድ ሙስሊም ተነስቶ የራሱን ፊቺ ለዬትኛውም የእስልምና መፅሓፍ ሊሰጥ አይችልም። ምክኒያቱም ቀደምት  የ እስልምና አዋቂዎች፣ ሙፈሲሮች ትርጉሞቹን በ መፅሓፍቶቻቸው አስቀምጦውልናል። ስለዚ ከላይ ያነበብናቸው ሓድዞች ትርጒሜያቸው ምን እንደሆነ ቀጥለን እናያለን

ኢብን ሓጀር፦ "ሰይጣን ይበላል የተባለው ምንም የማያከራክር ሓቅ ነው።ይሄን ለመቃወም የሚያስችለን ምንም የ አይምሮ ብቃት የለንም። ይህ ቃል የተረጋገጠ ስለሆነ ምንም ትርጉም አያስፈልገውም።" ይላል
And that Satan eats is a fact. It is not for our intellect to reject that, and it is already proven from the report with no need for interpretation. (Fath al-Bari 9/522)

ኢማም ነወዊም  ይህንን ሓሳብ ይጋራሉ (Sharh Sahih Muslim 13/204)

ወገኖቼ፣ የ እስልምና ሰይጣኖች ልክ እንደሰው የሚዳሰሱ የሚጨበጡ  ወ.ዘ.ተ  እንደሆነ ግልፅ ነው።
ለምሳሌ፦ሳሂህ አል-ቡኻሪ ቅጽ  4  መፅሓፍ 54 ቁጥር 495  ላይ አቡ ሁረይራ አንድን ሰይጣን ምግብ እየሰረቀ አግኝቶት እንደያዘውን ሰይጣኑም "ቸግሮኝ ነው ባክህ ልቀቀኝ" ብሎ ሲለምነው እንደለቀቀው ተጽፎ እናገኛለን።

ውድ አንባቢዋቼ፣ ነብዩ ሙሓመድ ይህንን የ "ስነ-ሰይጣን" አስተምህሮ ከዬት አምጥተውት ነው ብላቹ አስባቹ ይሆናል። መልሱ ሙስሊሞች እንደሚነግሩን ከ አላህ #አይደለም!!!"

መልሱ፣ነብዩ ሙሓመድ ይህንን ሁሉ (ስለ ሰይጣን መብላት፣መጠጣት፣መሽናት፣መጋባትና መራባት ወ.ዘ.ተ) ያስተማሩት ሙሉ ለ ሙሉ ከ ዕስልምና በፊት በ አራቢያ ውስጥ ከ ነበሩ እምነቶች ቀድተው ነው። ይህንን ለ መረዳት አንድ ሰው "The Evolution of the Concept of Jinn" የሚል በ Amira El-Zein
የተፃፈ መጽሓፍ ማንበብ ይጠበቅበታል!!
......ይቀጥላል
@Jesuscrucified
@Jesuscrucified