ዓይን ያወጣ፣ እውቀት የጎደለው ፣ በ ጆሮ ጠገብ ብቻ የተዳሰሰ የ ወሒድ ዑመር ውሸት! #ክፍል 2#
የ ወሒድ ሁለተኛ ነጥብ እንዲህ ይላል
"ሁለተኛ በ 60-135 AD ይኖር የነበረው በርናባስ የበርናባስን ወንጌል፣ የበርናባስን መልእክት እና የበርናባስ ሥራ በ 100–131 AD አዘጋጅቷል፤ በሳይናቲከስ ኮዴክስ ላይ ፓሊካርፕ ለፊሊጵስዩስ በጻፈው ፓሊላርፕ 1፥1 ቀጥሎ የበርናባስ መልእክት 5፥7 ይቀጥልል። እዚህ ወንጌል ላይ፦ "ኢየሱስ ሳይሰቀል ወደ ሰማይ እንዳረገ እና እርሱን እንሰቅላለን ብለው የአስቆሮቱ ይሁዳ እንደሰቀሉት ይናገራል።"
መልስ፦ በዚህች አጭር አንቀጽ ውስጥ ወሒድ ብዙ ስህተትቶችን ( ቅጥፈቶችን) ፅፏል። አብዛኛው ስህተቱ ከ አላዋቂነቱ ነው ብንል አልተሳሳትንም። ስህተታቹን ቀጥዬ በመዘርዘር ማብራርያ እሰጣለሁ።
1. ከ ጳውሎስ ጋር " ሓዋሪያ" የተባለው በርናባስ ( የ ሓዋሪያት ስራ 14:14) ይኖር የነበረው ከ 60-135 አይደለም። በርናባስ የተወለደበት ዓ.ም አይታወቅም። የሞተው ግን በ 73 A.D ነው( Fox's Book of Martyrs Chapter 1- History of Christian Martyrs to the First General Persecutions Under Nero, No XVII.)።
2. " በርናባስ የበርናባስን ወንጌል፣ የበርናባስን መልእክት እና የበርናባስ ሥራ በ 100–131 AD አዘጋጅቷል" ብሎ ወሒድ ጽፏል።
መልስ፦ ሲጀመር በርናባስ ከነኚ ሁሉ መጽሓፍቶች አንዱንም አልጻፈም።
ሀ. የ በርናባስ ወንጌል የተባለው ጭራሹን በ 15ኛ century ( 1500 አመት ከ ክርስቶስ ልደት በኊላ) የተፃፈ መፅሃፍ መሆኑ የተደረሰበት እውነታ ነው። እንዲያውም አንዳንድ ምሁራን ይህ መፅሃፍ በ ሙስሊሞች የተጻፈ መሆኑን ይናገራሉ( መጽሓፉ ሙሓመድን ' መሲህ' ይላል። በተጨማሪም ብዙ ስለ ሙሓመድ እንዲያወራ ተደርጎ የተፃፈ ነው።) ስለዚ ከ በርናባስ ጋር የሚያገናኘው ምንም ነገር የለም።
የ በርናባስ ወንጌል የ 15th century ስራ ለመሆኑ ማስረጃውቻችን።
I. የ ዕደ ኪታባት ማስረጀ ( manuscript evidence)፦ የ በርናባስ ወንጌል ተብሎ ዛሬ ላይ ለሚጠራው መፅሃፍ ማስረጃ ሊሆነው የሚችልው ( oldest) ማኑስክሪፕት ከ 15ኛ century ብቻ ነው። እሱም ተጽፎ የሚገኘው በ #ጣሊያንኛ እና በ #ስፓኒሽ ቁንቊ ነው። ልብ በሉ፣ ይህ መጽሓፍ በ ታሪክ ውስጥ የትም ቦታ ተጠቅሶ አያውቅም። 2000 አመታትን ያስቆጠሩ የ መጽሓፍ ቅዱስ እደ ኪታባት፣ ግሪክም ይሁን ኮፕቲክ ወይም ሲሪያክ፣ውስጥም የለም። ድንገት ከ ክርስቶስ ልደት ከ 1500 አመት በኊላ ብቅ ያለ የ ሙስሊሞች ፕሮፖጋንዳን የሚያከሒድ መፅሃፍ ነው።
II. Internal evidence( መጽሓፉ ውስጥ የሚገኙ ማስረጃዎች)
1. ታሪካዊ ማስረጃ፦ መጽሓፉ (የ በርናባስ ወንጌል) በ 3ኛ ምዕራፍ ላይ " ጲላጦስና ሔሮድ በተመሳሳይ ጊዜ ላይ ይሁዳን እየገዙ እንደነበር ይናገራል (chap.3: There reigned at that time in Judaea Herod, by decree of Caesar Augustus, and Pilate was governor)
ይህ ግልጽ የሆነ ስህተት ነው። ሔሮድ (ሔሮዶስ) ይሁዳን የገዛው ብቻውን ከ 37 B.C -4 A.D ሲሆን ጲላጦስ ደግሞ ከ 26-36 A.D ነው። በ ፍጹም አይገናኙም። በርናባስ ይህን መፅሃፍ ጽፎ ቢሆን ይህንን ይሚያክል ስህተት አይሰራም። ምክንያቱም በርናባስ በዚያ ዘመን ይኖር የነበረ ሰው ስለሆነ። ስለዚህ መፅሃፉ የተጻፈው ዘመኑን በማያውቅ ሰው ነው።
2. የ Geography ማስረጃ፦መጽሓፉ በ 20- 21 chapter " እየሱስ ከ ጉሊላ ወደ ናዝሬት በመሔድ በ ናዝሬት በሚገኘው የዓሳ አጥማጆች መንደር ደርሶ እዘ በ ዓሳ አጥማጆች ተቀባይነት አግኝቶ ለ ብዙ ሕዝቦችም ስለሱ እንደሰበኩ ይናገራል " እዚ ውስጥ ትላልቅ ስህተቶች አሉ። ናዝሬት የ ዓሳ አጥማጆችም ሆነ ዓሳ የሚጠመድበት ቦታ አይደለችም። እንዲያውም ከ ገሊላ ባሕር 14 ኪ.ሜ የሚርቅ ቦታ ነው። ሁለተኛ እየሱስ ሔደ የተባለው የ ዓሳ አጥማጆች መንደር ቅፍርናሆም ነው( ዮሓኒስ 6:16-24)።
3. የ 15ኛ century ለመሆኑ ማስረጃ።
የ "እዮቤልዩ" "Jubilee" በዓል በ ዘሌዋዊያን ምዕራፍ 25: 8-11 በየ 50 አመቱ እንዲያከብሩ እግዚየብሔር ለ እስራኤላውያን የሰጠው ሕግ ነው።
በ 1300A.D ግን ፖፕ ቦኒፌስ 8ኛ ( Pope Boniface VIII) ግን ይህ በዓል በ ክርስቲያኖች በየ 100 አመቱ እንዲከበር ትዕዛዝ ሰጡ። ግን ቀጥሎ የመጣው ፖፕ ኪሊመንት 6ኛው ምልሶ በየ 50 አመቱ እንዲሆን ትዕዛዝ ስለሰጠ በዓሉ በ 1350 ተከብሯል(100 አመቱ ሳይከበር)።
በሚገርም ሁኔታ የ በርናባስን ወንጌል የጻፉ ሰውች እንዲህ ብለው በ ወንጌሉ አስፍሯል። " አሁን በየ 100 አመቱ የሚከበረው እዩቤልዩ መሲሁ ሲመጣ በየ አመቱ ይከበራል so much that the year of Jubilee, which now comes every 100 years, shall by the Messiah be reduced to every year in every place (chap. 82) ... ልብ በሉ፣ ሲጀመር እዮበልዩ በ 100 አመት ተከብሮ አያውቅም። ግን ፖፑ አንዴ ትዕዛዝ ሰጥቶ ስለነበረ የ በርናባስ ወንጌል ፀሓፊዎችም መስሏቸው ፅፏል። ስለዚ ይህ መጽሓፍ በ ግልጽ የሆነ የ 14- 15 ኘ century መጽሓፍ ነው።
ብዙ ማስረጃዎዥን ማውራት ይቻላል ግን ለ አሁን በቂ ቢሆንም አንድ የእስልምና ምሁር ያለውን ላስነብባችሁ።
As regards the "Gospel of Barnabas" ( የ በርናባስን ወንጌል በተመለከተ) itself, there is no question that it is a medieval forgery( በ ሚድዣል ( ከ 10ኛ እስከ 15ኛ century አከባቢ) ጊዜ ይተቀናበረ ፎርጀሪ ስለመሆኑ ምንም ጥርጣሬ የለውም ... It contains anachronisms which can date only from the Middle Ages and not before, and shows a garbled comprehension of Islamic doctrines, calling the Prophet the "Messiah", which Islam does not claim for him. Besides it farcical notion of sacred history, stylistically it is a mediocre parody of the Gospels, as the writings of Baha Allah are of the Koran. (Cyril Glassé, The Concise Encyclopedia of Islam, San Francisco: Harper & Row, 1989, p. 65)
3ኛው ውሸት፦ ወሒድ እንደቀጠፈው የ በርናባስ "መልዕክትም" የተጻፍው በ በርናባስ ሳይሆን ሌላ ግለ ስብ በሱ ስም እንደፃፈው ስኮላሮች አረጋግጦውታል። አንድ ምክኒያት መስጠት ቢፈለግ ፤ በርናባስ የሞተው በ 73 A.D ነው መልዕክቱ ግን የተጻፈው በ 100-120 A.D ነው። ታድያ በርናባስ ከሞተ በኊላ ፃፎት ነው ሊባል ነው???
ስለዚ ይህ በ 15ኛ century የተፈበረከው የ በርናባስ ወንጌል የ ክርስቶስን ሞትና ትንሳኤ ለመዳኘት ስፍራም የለውም። ስኮላሮች ይህን የ ወሒድን ሙግት ቢሰሙ አመት እንደሚስቁበት ምንም ጥርጥር የለውም።