ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ለባለ ልደቷ (የልቤ ሰው )
🎂🎂🎂


መወለድ በብርሃናማ ገፁ የተገለጠባት ኪነት.... ፍቅር በእያንዳንዷ ህዋሳቷ ሰርፆ ሰው
የመሆንን ዜማ የተቀኘችልን ጥዑም ልሳን..... ሳምሶን ያልተሰናከለባት ደሊላዊ ጥፍጥና.....
እስራኤላውያን ያላመፁባት ሲጳራዊት ንቃት..... ግብፃውያን ያላስመረሯት ራሔላዊት
ቅንነት..... ፍርኦነች ያላሳደዷት ማሪያማዊት ብፅእና.... እነኋት የቅን መንገድ።


ሰላማዊቷ ርግብ..... የፍቅር እጣነ ሞገር..... የውበት ሸማ ፈታይ..... ጥዑም ፈትለ ወርቅ
ዜማ..... ጂጂ ነፍሴ ....ልባሟ ወለተ ፃድቅ.... እዝን ማርካ፥ አንጀትን ፈልፍላ በልብ
የነገሰች የንጋት ትፍስህት!! ከመወለዷ አብራክ ፀንሳ የወለደችኝ አማልክቴ!!! አፈቅርሻለሁ
የኔ እመቤት።አንቺ በእያንዳንዷ ቅፅበት በልብ ሰማይ ላይ የምትወለጅ የማትጠልቂ ፀሓይ
ነሽ።እንኳንም ተወለድሽልኝ!!!
በአንቺ መወለድ
የፈገግታን ጣእም.... የህይወትን አይጠገቤ ገፅ አጣጣምንና እንኳንም ተወለድን አልን!!!!
------------------------------------------------

በመኪናው መንገድ በተወለወለው ፤
በሎንችን አውቶብስ ነይ ድረሽ በሚለው ፤
ታዲያ ይኸ ቀልቤ፤
ምን አይቶ መስሎህ ነው የሚንጦለጦለው ፤
አልገባህ አለ እንጂ ፤
አንተን አይደል እንዴ ልቤ የከጀለው።


ዘለቀ ይሉኛል ያ ባለጎፈሬው ያ ባለድምድሙ ፤
ኧረ ድረሱልኝ ፤
ጎፈሬው ጋረደኝ ሊጠፋኝ ነው ስሙ ።
አባይን በዋና ወጥቼው ላይደክመኝ ፤
ጣናን በታንኳየ ዋኝቼው ላይገርመኝ ፤
ሌት ከቤትህ መጣሁ እኔ ደግሞ አያርመኝ ።


እዚያ ማዶ ጋራ ያለሽው ጋጋኔ ፤
የናፍቆት ሊጋባ የፍቅር ምስለኔ፤
ውሃ ከዳኝ ብለሽ ፤ ከፍቶሻል እንደኔ ።
ውሃ ከዳኝ ብሎ ሰው ለምን ይቆጣል ፤
ቁልቁለት ካገኘ ፤
ውሃ ዝቅዝቅ እንጅ መች ሽቅብ ይወጣል ።


አያና ደማሙ ያባይ ዳሩ ቃንቄ የሰከላው ዳገት ፤
ምንድር ይሆን መላው ፤
ምን ይሆን መሻሪያው ፤ ውሃ የከዳለት ።
አሁንም ዘለቀ ፤
ያንን ሸጋ ይዞ ፤
ረጅሙ አውቶብስ አለፈ ነጎደ ሄደ ወደፊት፤
መሆኑን ቢያውቅ ነው ፤
መዋያው ዳንግላ ማደሪያው ዳሞት ፤
አወይ አጨካከን ፤
ምነው ጥሎኝ ሄደ ፤ እኔ እንዲህ ስሞት ።


አባ አለም ለምኔ አባ አለም ለምኔ ፤
እንኳንስ ሰውና ፤
ማልመድ አይጠፋኝም ወፍና ቀጭኔ ።
የራያውን ቀሚስ ሸብ አድርጌዋለሁ ፤
መልጎም ብር አምባሩን በጄ ሰክቻለሁ ፤
በተረከዜ ላይ አልቦ ገጥሜያለሁ ፤
ባለ አልቦ ባል አልቦ ቢለኝ መንገደኛ ፤
እንዴት እንዴት እንዴት ፤
ባል አልቦይቱ ልጅ ባል አልቦ ልተኛ ??
የመልከፄዴቅ ልጅ ጦቢያ ላይ ስትዘልቅ ፤
እኔ ግብር ላግባ እጣንና ወርቅ ፤
በጉባኤ ቃና በአጀብ ልራቀቅ ፤
ቢጠጡት አይጠግቡት ቅኔና መረቅ ።

#እማፈቅርሽዋ መልካም ልደት!🎂

@getem
@getem
@balmbaras
👍1