ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ቀለም_ቀቢ_ትውልድ
.
.
አንዲት ግርግዳ ነበረች ፥ ስሟን "ሀገር" የሚሏት
ከድሮ በፊት የኖሩ፣ የጥንት ሰዎች የሰሯት
-
የሆነ ትውልድ እጆች ፣ ሊያጌጧት ቢያስቡ
እርቃን ሰውነቷን ፣ አንዳች ቀለም ቀቡ!
-
በሌላ ዘመን ደ’ሞ ፣ ሌሎች ልጆቿ መጡ
"ይህ ነው የሚሻል" ብለው ፣ ሌላ ቀለም ለወጡ!
.
እንዲህ እንዲያ እያለ…..
አዲሶች ሲመጡ፣ ነባሮች ሲሄዱ
አመታት ነጎዱ!!
.
ባለ ብሩሽ ሁሉ --
ምስኪን ገላዋ ላይ ፣ መልኩን እየሳለ
ለጌጥ ያሉት ቀለም --
ያለቅጥ ወፍሮ ፣ ግርግዳ አከለ!
.
እናም ይህች "ሀገር"…
በእረፍት አልባ ብሩሽ ፣ በሁለት በኩል ታንቃ
በቀለም ግግር ውስጥ ፣ አለች ተደብቃ!
-
ወጪና ወራጁ
መዋቅሩን ትቶ ፣ ሲጨነቅ ለውበት
(ያስተዋለ የለም... )
የግርግዳው ስሪት --
ድንጋይ ይሁን ጭቃ
ብረት ይሁን እንጨት።
--------------//-----------
( በርናባስ ከበደ )
[ከ"ፊደልና ቅኔ" የግጥም መድብል]

@getem
@getem
@getem
👍1😁1