ቀለም እና እውነት!
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።።።።።።።።
በተዋበ ሳሎን ፥ በሰፊ አዳራሽ
በመቶ እቁባቶች ፥ በአፋሽ አከንፋሽ
ታጅቦ ሰለሞን ...
እንዲች ብሎ ሳይዋሽ
ሁሉም ከንቱ ከንቱ ፥ የከንቱ ከንቱ ነው
ብሎ ተናገረ
ይሄን ባለ ማግስት...
ፅድቁን አደላድሎ ፥ ነፍሱን አሻገረ ።
#ደግሞ ወዲህ ግድም.. .
ታብዮ ለስሙ ፥ ዝናን የሚያስቀድም
በጭብጨባ ብዛት.. .
ስጋውን አግዝፎ ፥ ነፍሱን የሚያለግም
አሳቢ ተብሎ ፥ ሙገሳ የደረሰው
ፈላስፋ ተነስቶ ፥ እግዜሩን ዘለፈው ።
ይሄን ባለ ማግስት...
ለዓለም ተሞሽሮ ፥ ህግን ጥሶ ሻረ
ሰለሞን እንዳለው ፥ ከንቱ ሆኖ ቀረ።
@getem
@getem
@getem
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።።።።።።።።
በተዋበ ሳሎን ፥ በሰፊ አዳራሽ
በመቶ እቁባቶች ፥ በአፋሽ አከንፋሽ
ታጅቦ ሰለሞን ...
እንዲች ብሎ ሳይዋሽ
ሁሉም ከንቱ ከንቱ ፥ የከንቱ ከንቱ ነው
ብሎ ተናገረ
ይሄን ባለ ማግስት...
ፅድቁን አደላድሎ ፥ ነፍሱን አሻገረ ።
#ደግሞ ወዲህ ግድም.. .
ታብዮ ለስሙ ፥ ዝናን የሚያስቀድም
በጭብጨባ ብዛት.. .
ስጋውን አግዝፎ ፥ ነፍሱን የሚያለግም
አሳቢ ተብሎ ፥ ሙገሳ የደረሰው
ፈላስፋ ተነስቶ ፥ እግዜሩን ዘለፈው ።
ይሄን ባለ ማግስት...
ለዓለም ተሞሽሮ ፥ ህግን ጥሶ ሻረ
ሰለሞን እንዳለው ፥ ከንቱ ሆኖ ቀረ።
@getem
@getem
@getem