ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#የላይ ሰፈር ስሌት!
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።
የጨመቅነው እንባ ፥ ከምድር ወረደ
ጠሀይ ስትበረታ.. .
ዳግም ለመዳመን ወደ ሰማይ ሄደ
ላስለቀሰን በዳይ...
ቀዝቃዛ ውሀ ሆኖ ፥ ገላውን አበረደ።
ይሄ የኛ በዳይ..
መርዝ እየጋተን ፥ ወተት እየሰጠ
ላስቲክ ለመለጠፍ ፥ ቆዳ እየላጠ
ህመም ሲሆንብን ፥ ኪኒን እየሸጠ
አመፁ ለማለት ራሱ እያመፀ
ቀብሮ ባፈረሰው...
የስጋችን አፈር ፥ ጎጆውን አነፀ።

@getem
@getem
@paappii