ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
****የባላባቶች ወግ****

አንዲት ምስኪን ሃገር -ዘወትር ጠዋት ማታ
ቁራሽ እንዲሰጣት - አምላኳን ስትለምን - እጆቿን ዘርግታ
መስጠት ማይሰለቸው - ቸር የሆነው አምላክ
ዘወትር ይሰጣታል የለት እንጀራዋን - እጆቿን በመላክ
መቼም!
"ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል" በሚባለው ተረት
ተቀባይ ባይኖርም የሚል የመሰረት
ጥቂት ባላባቶች "ሆድ ካገር ይሰፋል" እየተባባሉ
ከሃገር እጅ ላይ እንጀራ እየበሉ
እንጀራ ሰጪውን አምላክ ይከሳሉ አምላክ ይወቅሳሉ
እንዲህ ይላሉ!
ዘወትር ተቀብሎ ዘወትር መዘርጋት ነው የዚች ሃገር እጣ
ታዲያ እንዴት ተብሎ ሁሌ ከመቀበል ከልመና ትውጣ
ምነካው ፈጣሪ!
በገዛ ሃገራችን ሁልግዜ እየሰጠ ክንዱን የሚያለፋው
ድህነት ለማጥፋት ቆርጠን ስንነሳ ልመና ሚያስፋፋው
እረ አሰዳቢ ሃገር ነች ሁልግዜም አልቃሻ
ስራ የማትወድ ጉልበትዋን ቆጥባ ልመና ምትሻ
ይህው በኛ ጥረት ስንት ዲጂት አደጋ
እስከመቼ ድረስ እጆቿን ትዘርጋ!?
እግዜር አይናገር እግዜር አይጋገር
ዝም ነው ጭጭ ነው
ደሞ እንዲህ ይላሉ
እግዚሐሩስ ቢሆን እንባ ፈልጎ እንጂ ሁልግዜም ሮሮ
የለት እንጀራዋን ሚስጣት ቆንጥሮ
ካዘነላትማ የእውነት ከወደዳት
ቁጭ ብላ እንድትባል ነዳጅ ለምን ከዳት!
አየህ አደል እግዜር
እንዲህ ነው ቋንቋቸው በዘመን ድፍረት ጡርን የማይፈሩ
ኬት ይመጣል ነዳጅ አለ ባሉት ስፍራ ተግተው ካልቆፈሩ
እግዜር አይናገር እግዜር አይጋገር
ዝም ነው ጭጭ ነው
እረባክህ እግዜር ይህን ሁሉ ነገር
አንድ ቃል አውጣና ቼ ብለህ ተናገር
እረባክህ እግዜር
እኛ ፈረሶች ነን ንጉስ ሚጋልበን ንጉስ የሚነዳን
ክንድ ባይኖረንም አንተን እንድንለምን እባክህን እርዳን
እረባክህ እግዜር
ከጥያቄው በፊት ታውቃዋለህ መልሱን
ማሮጥ ብቻ ሳይሆን መሮጥ ያስተማረን "ቼ” በለው ንጉሱን
እረባክህ እግዜር እረባክህ አምላክ
ከመከራ ቋጥኝ ከሣት የሚያወጣን ገብርኤልህን ላክ
እረባክህ አላህ
እኛ ቢላሎች ነን መሳቅ የናፈቀን ደስታን የተቀማን
መሀመድ የታለ አንተን የሚያሳየን ወዳንተ የሚያሰማን
እኛ ቢላሎች ነን ደስታን የተቀማን
እኛ በሬዎች ነን
የገረፈን ጅራፍ ከሁዋላ እየፈራን
በስንዴ መስክ ላይ እንክርዳድ ያፈራን
እኛ በሬዎች ነን
ግን በዚህ ሁሉ መሀል
አንዲት ምስኪን ሀገር ዘወትር ጠዋት ማታ
ቁራሽ እንዲሰጣት አምላኳን ስትለምን እጆቿን ዘርግታ
መስጠት ማይሰለቸው ቸር የሆነው አምላክ
ዘወትር ይሰጣታል የለት እንጀራዋን እጆቿን በመላክ
ኢትዮጵያን
እግዚአብሔር
ይባርክ


#አስታዎሰኝ_እረጋሳ


@getem
@getem
@getem