ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
" #የሞራል_ብቃት ?"
-
መቼም ሰው ይስታል ፣ ዋናው መታረሙ
ህመም ሁሉ አይገልም፣ ዋናው መታከሙ፣
በሚል የሞራል ሕግ፣ የወል አስተሳሰብ
ያለማቆላለፍ ፣ ያለማወሳሰብ፣
ስለ አቋሙ ዝንፈት
ስለ ርምጃው ሽፈት
በተረዳኝ አቅም ባሽሙር ሳላነውር
ኮሶ ሁኖ ሚያሽር ሃሳብ ብወረውር፣
አለኝ ትንፍሽ አትበል ጩሆ በድንፋታ
ጫማዬን ሳታጠልቅ ሳትቆም በኔ ቦታ!
ወፈፍ አደረገው ...
ሊሰፍርብኝ ቃጣው ነቅንቆ ሊጥለኝ
ምናል ብረሳበት እግር እንደሌለኝ ፨
------------------///--------------
[በርናባስ ከበደ]

@getem
@getem
@gebrielAQL