#የታሰረ ልብ#
በመዳፍህ ጥበብ፥በማዳንህ መክሊት
በመዉደድህ ድርሳን፥በፈገግታህ ዳዊት
ገላየን አሽረህ፥ በለኮስከዉ እሳት
ከዳዊት ጠንክረህ፥ከሰለሞን ልቀህ
ከተራራ ገዝፈህ፥ከሃሳብ ረቀህ
የልቤን ከረጢት፥እንደ ክርታስ ለብሰህ
በስጋ በደሜ፥እንደስኳር ቀልጠህ
ፍቅርን ከወለላዉ፥ከመረቁ ጨልፈህ
ለነገ ሳትሰስት፥ለዛሬ ችረኸኝ
ምነዉ ፥በጥዋት ጠፋህ፥ከጉም ጋር አሰረኸኝ
እንዳልሄድ፥እንዳልቀር፥እንዳልተኛ አርገኸኝ።
ልብ የሌለዉ ደረት፥ታቦት አልባ መቅደስ
የደረቀ ሎሚ፥ ያልተቋጨ ቀሚስ
የነቃ ብርሌ፥ ክር የሌለዉ ፍኑስ
ክንፍ የሌላት ገዴ፥ወላዋይ አረከኝ
በትዝታህ ገመድ፥የኋሊት አስረኸኝ።
ብጠራህ አትሰማኝ፥ብሮጥ አልደርስብህ
ብጠቅስህ አታይ፥ብሸሽህ አልርቅህ
በቆምኩበት ሮጨ፥ባይኔ ስከተልህ
ድንገት ብትሰወር፥ተራራዉ ጋር'ዶህ
ደርበዉ ኩታህን ፥በሩቅ ይጥራኝ ወዝህ
ካይኔ እንኳ ብትጠፋ፥እሽትቼ እንድሸኝህ።
በተኛንበት ሜዳ፥ በመስኩ ላይ፥ ልንከራተት
የቁም ቅዠቴን ልዋዥ፥ሞቴን በሞትህ ላትት
ሳቅህ፥ፋኑስ ይሁነኝ፥ዳናህን ልጥባ በሌሊት
ምስልህን፥አሽዋዉ ላይ፥እወንዙ ዳር ልሳልህ
ልግባ፥ ከፍቅርህ ሙዳይ፥አቤት ልበል በስምህ።
በለስላሳ ጣትህ፥አቅፈህ ባጎረስከኝ
በትዝታህ ሸማ፥ ፈትለህ ባለበስከኝ
ዉሉን ባፍህ ነክሰህ፥ከጉም ጋር አስረኸኝ
ከትናንት አቅርበህ፥ከዛሬ አርቀኸኝ
እንዳልወጣ ፥እንዳልወርድ፥አየር ላይ ሰቀልከኝ።
@getem
@getem
@gebriel_19
በመዳፍህ ጥበብ፥በማዳንህ መክሊት
በመዉደድህ ድርሳን፥በፈገግታህ ዳዊት
ገላየን አሽረህ፥ በለኮስከዉ እሳት
ከዳዊት ጠንክረህ፥ከሰለሞን ልቀህ
ከተራራ ገዝፈህ፥ከሃሳብ ረቀህ
የልቤን ከረጢት፥እንደ ክርታስ ለብሰህ
በስጋ በደሜ፥እንደስኳር ቀልጠህ
ፍቅርን ከወለላዉ፥ከመረቁ ጨልፈህ
ለነገ ሳትሰስት፥ለዛሬ ችረኸኝ
ምነዉ ፥በጥዋት ጠፋህ፥ከጉም ጋር አሰረኸኝ
እንዳልሄድ፥እንዳልቀር፥እንዳልተኛ አርገኸኝ።
ልብ የሌለዉ ደረት፥ታቦት አልባ መቅደስ
የደረቀ ሎሚ፥ ያልተቋጨ ቀሚስ
የነቃ ብርሌ፥ ክር የሌለዉ ፍኑስ
ክንፍ የሌላት ገዴ፥ወላዋይ አረከኝ
በትዝታህ ገመድ፥የኋሊት አስረኸኝ።
ብጠራህ አትሰማኝ፥ብሮጥ አልደርስብህ
ብጠቅስህ አታይ፥ብሸሽህ አልርቅህ
በቆምኩበት ሮጨ፥ባይኔ ስከተልህ
ድንገት ብትሰወር፥ተራራዉ ጋር'ዶህ
ደርበዉ ኩታህን ፥በሩቅ ይጥራኝ ወዝህ
ካይኔ እንኳ ብትጠፋ፥እሽትቼ እንድሸኝህ።
በተኛንበት ሜዳ፥ በመስኩ ላይ፥ ልንከራተት
የቁም ቅዠቴን ልዋዥ፥ሞቴን በሞትህ ላትት
ሳቅህ፥ፋኑስ ይሁነኝ፥ዳናህን ልጥባ በሌሊት
ምስልህን፥አሽዋዉ ላይ፥እወንዙ ዳር ልሳልህ
ልግባ፥ ከፍቅርህ ሙዳይ፥አቤት ልበል በስምህ።
በለስላሳ ጣትህ፥አቅፈህ ባጎረስከኝ
በትዝታህ ሸማ፥ ፈትለህ ባለበስከኝ
ዉሉን ባፍህ ነክሰህ፥ከጉም ጋር አስረኸኝ
ከትናንት አቅርበህ፥ከዛሬ አርቀኸኝ
እንዳልወጣ ፥እንዳልወርድ፥አየር ላይ ሰቀልከኝ።
@getem
@getem
@gebriel_19
👍1