#የታለ_ሰንደቅሽ?
የብዙ ሺ አመታት... የታሪክ አዝመራ
የጥበብ የፍቅር ...የሰላም ጎተራ
የሃይማኖት ትጋት ፀሎት ከበዛበት
በምግባር ትሩፋት ስብዕና ካ'በበት
ሳባ ወእስራኤል ከሆነ ነገድሽ
የጦቢያ ደምግባት ካለ በፊት ገፅሽ.....
ጥማትሽን ማርኪያ ውሀ 'ምትቀጂው
ፈለገ ጊዮን ከሆነ 'ምትጎነጪው
ገዳማት ሀሰሳ ጣና ኃይቅን ቀዝፈሽ
ማዕበሉን ካልፈሽ በረከትን ሽተሽ
ጥበብን ለማድነቅ በአንድም በሌላ
እግሮችሽ ካቀኑ ወደ ላሊበላ......
ጠዋት በማለዳ እርሱን ለማመስገን
ከገሰገሽ ፈጥነሽ ወደ አክሱም ጽዮን
ወደ ታላቁ ረመዳን
የአበው ደመቻው ዛሬ አንቺን ከሠራ
ኣንግሶ ካኖረሽ በዙፋኑ ስፍራ
የማንነት ኪዳን የጦቢያዊነትሽ
ከዙፋኑ በላይ የታለ ሰንደቅሽ ???
✍መኳስ✍
@getem
@getem
@getem
የብዙ ሺ አመታት... የታሪክ አዝመራ
የጥበብ የፍቅር ...የሰላም ጎተራ
የሃይማኖት ትጋት ፀሎት ከበዛበት
በምግባር ትሩፋት ስብዕና ካ'በበት
ሳባ ወእስራኤል ከሆነ ነገድሽ
የጦቢያ ደምግባት ካለ በፊት ገፅሽ.....
ጥማትሽን ማርኪያ ውሀ 'ምትቀጂው
ፈለገ ጊዮን ከሆነ 'ምትጎነጪው
ገዳማት ሀሰሳ ጣና ኃይቅን ቀዝፈሽ
ማዕበሉን ካልፈሽ በረከትን ሽተሽ
ጥበብን ለማድነቅ በአንድም በሌላ
እግሮችሽ ካቀኑ ወደ ላሊበላ......
ጠዋት በማለዳ እርሱን ለማመስገን
ከገሰገሽ ፈጥነሽ ወደ አክሱም ጽዮን
ወደ ታላቁ ረመዳን
የአበው ደመቻው ዛሬ አንቺን ከሠራ
ኣንግሶ ካኖረሽ በዙፋኑ ስፍራ
የማንነት ኪዳን የጦቢያዊነትሽ
ከዙፋኑ በላይ የታለ ሰንደቅሽ ???
✍መኳስ✍
@getem
@getem
@getem