ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#መሄዴ ነው

ባር ባር አለ ሆዴ ፥ ልቤ መሬት ለቆ
ሊያከንፈኝ እንዳይሆን ፥ አለግብሩ መጥቆ
አለአስተዳደጉ ፥ አለባህሉ ወድቆ፡፡
ሽው እልም ሽው እልም ፥ ልቤ ወፌ-ይላላ
በመስተፋቅር ቀስት ፥ በሮሮ ምህላ
እንደደመና አክናፍ ፥እንደጮራው ጥላ
ሸው እልም ሽው እልም ፥ ሽው እልም ይላላ፡፡
ነሸጠው ፥ ሸፈጠ ፥ ሄደ ሸመጠጠ
በመስተፋቅር ጦር ፥ በሮሮ አመለጠ ፡፡

ብላቴን ጌታ ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን

@yeaseratfere

@getem
@getem
@getem